MyDugsiStart learning

Surah Ya-Sin in Amharic: translation and audio

Surah 36 · يس · Ya Sin · 83 verses

Surah Ya-Sin verse by verse: the Arabic with a recitation you can repeat, the transliteration, and the Amharic translation by Sadiq and Sani. For the meaning of every word, see Surah Ya-Sin word by word in English.

Verse 1

يسٓ

Transliteration ya-seen

Amharic የ.ሰ.(ያ ሲን)

Verse 2

وَٱلْقُرْءَانِ ٱلْحَكِيمِ

Transliteration wal-qur'āni l-ḥakīmi

Amharic ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡

Verse 3

إِنَّكَ لَمِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ

Transliteration innaka lamina l-mur'salīna

Amharic አንተ በእርግጥ ከመልክተኞቹ ነህ፡፡

Verse 4

عَلَىٰ صِرَٰطٍ مُّسْتَقِيمٍ

Transliteration ʿalā ṣirāṭin mus'taqīmin

Amharic በቀጥታም መንገድ ላይ ነህ፡፡

Verse 5

تَنزِيلَ ٱلْعَزِيزِ ٱلرَّحِيمِ

Transliteration tanzīla l-ʿazīzi l-raḥīmi

Amharic አሸናፊ አዛኝ ከሆነው አምላክ መወረድን ተወረደ፡፡

Verse 6

لِتُنذِرَ قَوْمًا مَّآ أُنذِرَ ءَابَآؤُهُمْ فَهُمْ غَـٰفِلُونَ

Transliteration litundhira qawman mā undhira ābāuhum fahum ghāfilūna

Amharic አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት (ተወረደ)፡፡ እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና፡፡

Verse 7

لَقَدْ حَقَّ ٱلْقَوْلُ عَلَىٰٓ أَكْثَرِهِمْ فَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

Transliteration laqad ḥaqqa l-qawlu ʿalā aktharihim fahum lā yu'minūna

Amharic በአብዛኞቻቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ፡፡ ስለዚህ እነርሱ አያምኑም፡፡

Verse 8

إِنَّا جَعَلْنَا فِىٓ أَعْنَـٰقِهِمْ أَغْلَـٰلًا فَهِىَ إِلَى ٱلْأَذْقَانِ فَهُم مُّقْمَحُونَ

Transliteration innā jaʿalnā fī aʿnāqihim aghlālan fahiya ilā l-adhqāni fahum muq'maḥūna

Amharic እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን፡፡ እርሷም (እንዛዝላይቱ) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት፡፡ እነርሱም ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው፡፡

Verse 9

وَجَعَلْنَا مِنۢ بَيْنِ أَيْدِيهِمْ سَدًّا وَمِنْ خَلْفِهِمْ سَدًّا فَأَغْشَيْنَـٰهُمْ فَهُمْ لَا يُبْصِرُونَ

Transliteration wajaʿalnā min bayni aydīhim saddan wamin khalfihim saddan fa-aghshaynāhum fahum lā yub'ṣirūna

Amharic ከስተፊታቸውም ግርዶን ከስተኋላቸውም ግርዶን አደረግን፡፡ ሸፈንናቸውም፡፡ ስለዚህ እነሱ አያዩም፡፡

Verse 10

وَسَوَآءٌ عَلَيْهِمْ ءَأَنذَرْتَهُمْ أَمْ لَمْ تُنذِرْهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

Transliteration wasawāon ʿalayhim a-andhartahum am lam tundhir'hum lā yu'minūna

Amharic ብታሰጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፡፡ አያምኑም፡፡

Verse 11

إِنَّمَا تُنذِرُ مَنِ ٱتَّبَعَ ٱلذِّكْرَ وَخَشِىَ ٱلرَّحْمَـٰنَ بِٱلْغَيْبِ ۖ فَبَشِّرْهُ بِمَغْفِرَةٍ وَأَجْرٍ كَرِيمٍ

Transliteration innamā tundhiru mani ittabaʿa l-dhik'ra wakhashiya l-raḥmāna bil-ghaybi fabashir'hu bimaghfiratin wa-ajrin karīmin

Amharic የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው፡፡ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው፡፡

Verse 12

إِنَّا نَحْنُ نُحْىِ ٱلْمَوْتَىٰ وَنَكْتُبُ مَا قَدَّمُوا۟ وَءَاثَـٰرَهُمْ ۚ وَكُلَّ شَىْءٍ أَحْصَيْنَـٰهُ فِىٓ إِمَامٍ مُّبِينٍ

Transliteration innā naḥnu nuḥ'yī l-mawtā wanaktubu mā qaddamū waāthārahum wakulla shayin aḥṣaynāhu fī imāmin mubīnin

Amharic እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡

Verse 13

وَٱضْرِبْ لَهُم مَّثَلًا أَصْحَـٰبَ ٱلْقَرْيَةِ إِذْ جَآءَهَا ٱلْمُرْسَلُونَ

Transliteration wa-iḍ'rib lahum mathalan aṣḥāba l-qaryati idh jāahā l-mur'salūna

Amharic ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ (የኾነውን) ግለጽላቸው፡፡

Verse 14

إِذْ أَرْسَلْنَآ إِلَيْهِمُ ٱثْنَيْنِ فَكَذَّبُوهُمَا فَعَزَّزْنَا بِثَالِثٍ فَقَالُوٓا۟ إِنَّآ إِلَيْكُم مُّرْسَلُونَ

Transliteration idh arsalnā ilayhimu ith'nayni fakadhabūhumā faʿazzaznā bithālithin faqālū innā ilaykum mur'salūna

Amharic ወደእነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ (የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)፡፡

Verse 15

قَالُوا۟ مَآ أَنتُمْ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُنَا وَمَآ أَنزَلَ ٱلرَّحْمَـٰنُ مِن شَىْءٍ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا تَكْذِبُونَ

Transliteration qālū mā antum illā basharun mith'lunā wamā anzala l-raḥmānu min shayin in antum illā takdhibūna

Amharic እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡ አልረሕማንም ምንም ነገር አላወረደም፡፡ እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም አሉዋቸው፡፡

Verse 16

قَالُوا۟ رَبُّنَا يَعْلَمُ إِنَّآ إِلَيْكُمْ لَمُرْسَلُونَ

Transliteration qālū rabbunā yaʿlamu innā ilaykum lamur'salūna

Amharic (መልክተኞቹም) አሉ «ጌታችን ያውቃል፡፡ እኛ ወደእናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን፡፡

Verse 17

وَمَا عَلَيْنَآ إِلَّا ٱلْبَلَـٰغُ ٱلْمُبِينُ

Transliteration wamā ʿalaynā illā l-balāghu l-mubīnu

Amharic «በእኛ ላይም ግልጽ የኾነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም፡፡»

Verse 18

قَالُوٓا۟ إِنَّا تَطَيَّرْنَا بِكُمْ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهُوا۟ لَنَرْجُمَنَّكُمْ وَلَيَمَسَّنَّكُم مِّنَّا عَذَابٌ أَلِيمٌ

Transliteration qālū innā taṭayyarnā bikum la-in lam tantahū lanarjumannakum walayamassannakum minnā ʿadhābun alīmun

Amharic (ሕዝቦቹም) «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ኾን፡፡ ባትከለከሉ በእርግጥ እንወግራችኋለን፡፡ ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ፡፡

Verse 19

قَالُوا۟ طَـٰٓئِرُكُم مَّعَكُمْ ۚ أَئِن ذُكِّرْتُم ۚ بَلْ أَنتُمْ قَوْمٌ مُّسْرِفُونَ

Transliteration qālū ṭāirukum maʿakum a-in dhukkir'tum bal antum qawmun mus'rifūna

Amharic «ገደ ቢስነታችሁ ከእናንተው ጋር ነው፡፡ ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ» አሏቸው፡፡

Verse 20

وَجَآءَ مِنْ أَقْصَا ٱلْمَدِينَةِ رَجُلٌ يَسْعَىٰ قَالَ يَـٰقَوْمِ ٱتَّبِعُوا۟ ٱلْمُرْسَلِينَ

Transliteration wajāa min aqṣā l-madīnati rajulun yasʿā qāla yāqawmi ittabiʿū l-mur'salīna

Amharic ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣ፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! መልክተኞቹን ተከተሉ» አለ፡፡

Verse 21

ٱتَّبِعُوا۟ مَن لَّا يَسْـَٔلُكُمْ أَجْرًا وَهُم مُّهْتَدُونَ

Transliteration ittabiʿū man lā yasalukum ajran wahum muh'tadūna

Amharic «እነርሱ ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲኾኑ ዋጋን የማየጠይቁዋችሁን ሰዎች ተከተሉ» (አላቸው)፡፡

Verse 22

وَمَا لِىَ لَآ أَعْبُدُ ٱلَّذِى فَطَرَنِى وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

Transliteration wamā liya lā aʿbudu alladhī faṭaranī wa-ilayhi tur'jaʿūna

Amharic «ያንንም የፈጠረኝን፤ ወደርሱም የምትመለሱበትን (ጌታ) የማልገዛ ለእኔ ምን አለኝ?» (አለ)፡፡

Verse 23

ءَأَتَّخِذُ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً إِن يُرِدْنِ ٱلرَّحْمَـٰنُ بِضُرٍّ لَّا تُغْنِ عَنِّى شَفَـٰعَتُهُمْ شَيْـًٔا وَلَا يُنقِذُونِ

Transliteration a-attakhidhu min dūnihi ālihatan in yurid'ni l-raḥmānu biḍurrin lā tugh'ni ʿannī shafāʿatuhum shayan walā yunqidhūni

Amharic «ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም፤ አያድኑኝምም፡፡

Verse 24

إِنِّىٓ إِذًا لَّفِى ضَلَـٰلٍ مُّبِينٍ

Transliteration innī idhan lafī ḍalālin mubīnin

Amharic «እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ፡፡

Verse 25

إِنِّىٓ ءَامَنتُ بِرَبِّكُمْ فَٱسْمَعُونِ

Transliteration innī āmantu birabbikum fa-is'maʿūni

Amharic «እኔ በጌታችሁ አመንኩ፤ ስሙኝም፤» (አለ)፡፡

Verse 26

قِيلَ ٱدْخُلِ ٱلْجَنَّةَ ۖ قَالَ يَـٰلَيْتَ قَوْمِى يَعْلَمُونَ

Transliteration qīla ud'khuli l-janata qāla yālayta qawmī yaʿlamūna

Amharic «ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡

Verse 27

بِمَا غَفَرَ لِى رَبِّى وَجَعَلَنِى مِنَ ٱلْمُكْرَمِينَ

Transliteration bimā ghafara lī rabbī wajaʿalanī mina l-muk'ramīna

Amharic «ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»

Verse 28

۞ وَمَآ أَنزَلْنَا عَلَىٰ قَوْمِهِۦ مِنۢ بَعْدِهِۦ مِن جُندٍ مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَمَا كُنَّا مُنزِلِينَ

Transliteration wamā anzalnā ʿalā qawmihi min baʿdihi min jundin mina l-samāi wamā kunnā munzilīna

Amharic ከእርሱም በኋላ በሕዝቦቹ ላይ (ልናጠፋቸው) ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም፡፡ (በማንም ላይ) አወራጆችም አልነበርንም፡፡

Verse 29

إِن كَانَتْ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً فَإِذَا هُمْ خَـٰمِدُونَ

Transliteration in kānat illā ṣayḥatan wāḥidatan fa-idhā hum khāmidūna

Amharic (ቅጣታቸው) አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ኾኑ፡፡

Verse 30

يَـٰحَسْرَةً عَلَى ٱلْعِبَادِ ۚ مَا يَأْتِيهِم مِّن رَّسُولٍ إِلَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Transliteration yāḥasratan ʿalā l-ʿibādi mā yatīhim min rasūlin illā kānū bihi yastahziūna

Amharic በባሮቹ ላይ ዋ ቁልጭት! ከመልክተኛ አንድም አይመጣቸውም በእርሱ የሚሳለቁበት ቢኾኑ እንጅ፡፡

Verse 31

أَلَمْ يَرَوْا۟ كَمْ أَهْلَكْنَا قَبْلَهُم مِّنَ ٱلْقُرُونِ أَنَّهُمْ إِلَيْهِمْ لَا يَرْجِعُونَ

Transliteration alam yaraw kam ahlaknā qablahum mina l-qurūni annahum ilayhim lā yarjiʿūna

Amharic ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙዎችን ማጥፋታችንንና እነርሱ ወደነርሱ የማይመለሱ መኾናቸውን አላወቁምን?

Verse 32

وَإِن كُلٌّ لَّمَّا جَمِيعٌ لَّدَيْنَا مُحْضَرُونَ

Transliteration wa-in kullun lammā jamīʿun ladaynā muḥ'ḍarūna

Amharic ሁሉም እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀረቡ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡

Verse 33

وَءَايَةٌ لَّهُمُ ٱلْأَرْضُ ٱلْمَيْتَةُ أَحْيَيْنَـٰهَا وَأَخْرَجْنَا مِنْهَا حَبًّا فَمِنْهُ يَأْكُلُونَ

Transliteration waāyatun lahumu l-arḍu l-maytatu aḥyaynāhā wa-akhrajnā min'hā ḥabban famin'hu yakulūna

Amharic የሞተችውም ምድር ለእነርሱ ምልክት ናት! ሕያው አደረግናት፡፡ ከእርሷም ፍሬን አወጣን፤ ከርሱም ይበላሉ፡፡

Verse 34

وَجَعَلْنَا فِيهَا جَنَّـٰتٍ مِّن نَّخِيلٍ وَأَعْنَـٰبٍ وَفَجَّرْنَا فِيهَا مِنَ ٱلْعُيُونِ

Transliteration wajaʿalnā fīhā jannātin min nakhīlin wa-aʿnābin wafajjarnā fīhā mina l-ʿuyūni

Amharic በእርሷም ውሰጥ ከዘምበባዎችና ከወይኖች የኾኑ አትክልቶችን አደረግን፡፡ በእርሷም ውስጥ ምንጮችን አፈለቅን፡፡

Verse 35

لِيَأْكُلُوا۟ مِن ثَمَرِهِۦ وَمَا عَمِلَتْهُ أَيْدِيهِمْ ۖ أَفَلَا يَشْكُرُونَ

Transliteration liyakulū min thamarihi wamā ʿamilathu aydīhim afalā yashkurūna

Amharic ከፍሬውና እጆቻቸው ከሠሩትም ይበሉ ዘንድ (ይህን አደረግን)፤ አያመሰግኑምን?

Verse 36

سُبْحَـٰنَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَزْوَٰجَ كُلَّهَا مِمَّا تُنۢبِتُ ٱلْأَرْضُ وَمِنْ أَنفُسِهِمْ وَمِمَّا لَا يَعْلَمُونَ

Transliteration sub'ḥāna alladhī khalaqa l-azwāja kullahā mimmā tunbitu l-arḍu wamin anfusihim wamimmā lā yaʿlamūna

Amharic ያ ምድር ከምታበቅለው ከነፍሶቻቸውም ከማያውቁትም ነገር ዓይነቶችን ሁሏንም የፈጠረ (አምላክ) ጥራት ይገባው፡፡

Verse 37

وَءَايَةٌ لَّهُمُ ٱلَّيْلُ نَسْلَخُ مِنْهُ ٱلنَّهَارَ فَإِذَا هُم مُّظْلِمُونَ

Transliteration waāyatun lahumu al-laylu naslakhu min'hu l-nahāra fa-idhā hum muẓ'limūna

Amharic ሌሊቱም ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡ ከእርሱ ላይ ቀንን እንገፍፋለን፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ በጨለማ ውስጥ ይገባሉ፡፡

Verse 38

وَٱلشَّمْسُ تَجْرِى لِمُسْتَقَرٍّ لَّهَا ۚ ذَٰلِكَ تَقْدِيرُ ٱلْعَزِيزِ ٱلْعَلِيمِ

Transliteration wal-shamsu tajrī limus'taqarrin lahā dhālika taqdīru l-ʿazīzi l-ʿalīmi

Amharic ፀሐይም ለእርሷ ወደ ሆነው መርጊያ ትሮጣለች፡፡ ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው፡፡

Verse 39

وَٱلْقَمَرَ قَدَّرْنَـٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلْعُرْجُونِ ٱلْقَدِيمِ

Transliteration wal-qamara qaddarnāhu manāzila ḥattā ʿāda kal-ʿur'jūni l-qadīmi

Amharic ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲኾን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪኾን ድረስ (መኼዱን) ለካነው፡፡

Verse 40

لَا ٱلشَّمْسُ يَنۢبَغِى لَهَآ أَن تُدْرِكَ ٱلْقَمَرَ وَلَا ٱلَّيْلُ سَابِقُ ٱلنَّهَارِ ۚ وَكُلٌّ فِى فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

Transliteration lā l-shamsu yanbaghī lahā an tud'rika l-qamara walā al-laylu sābiqu l-nahāri wakullun fī falakin yasbaḥūna

Amharic ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፡፡ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ አይኾንም፡፡ ሁሉም በመዞሪያቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡

Verse 41

وَءَايَةٌ لَّهُمْ أَنَّا حَمَلْنَا ذُرِّيَّتَهُمْ فِى ٱلْفُلْكِ ٱلْمَشْحُونِ

Transliteration waāyatun lahum annā ḥamalnā dhurriyyatahum fī l-ful'ki l-mashḥūni

Amharic እኛም (የቀድሞ) ትውልዳቸውን በተሞላች መርከብ ውስጥ የጫን መኾናችን ለእነርሱ ምልክት ነው፡፡

Verse 42

وَخَلَقْنَا لَهُم مِّن مِّثْلِهِۦ مَا يَرْكَبُونَ

Transliteration wakhalaqnā lahum min mith'lihi mā yarkabūna

Amharic ከመሰሉም በእርሱ የሚሳፈሩበትን ለእነርሱ ፈጠርንላቸው፡፡

Verse 43

وَإِن نَّشَأْ نُغْرِقْهُمْ فَلَا صَرِيخَ لَهُمْ وَلَا هُمْ يُنقَذُونَ

Transliteration wa-in nasha nugh'riq'hum falā ṣarīkha lahum walā hum yunqadhūna

Amharic ብንሻም እናሰጥማቸዋለን፡፡ ለእነርሱም ረዳት የላቸውም፡፡ እነርሱም የሚድዳኑ አይደሉም፡፡

Verse 44

إِلَّا رَحْمَةً مِّنَّا وَمَتَـٰعًا إِلَىٰ حِينٍ

Transliteration illā raḥmatan minnā wamatāʿan ilā ḥīnin

Amharic ግን ከእኛ ለኾነው ችሮታና እስከ ጊዜ ሞታቸው ለማጣቀም (አዳንናቸው)፡፡

Verse 45

وَإِذَا قِيلَ لَهُمُ ٱتَّقُوا۟ مَا بَيْنَ أَيْدِيكُمْ وَمَا خَلْفَكُمْ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

Transliteration wa-idhā qīla lahumu ittaqū mā bayna aydīkum wamā khalfakum laʿallakum tur'ḥamūna

Amharic ለእነርሱም «በስተፊታችሁና በኋለችሁ ያለውን ነገር ተጠንቀቁ ይታዘንላችኋልና» በተባሉ ጊዜ (ፊታቸውን ያዞራሉ)፡፡

Verse 46

وَمَا تَأْتِيهِم مِّنْ ءَايَةٍ مِّنْ ءَايَـٰتِ رَبِّهِمْ إِلَّا كَانُوا۟ عَنْهَا مُعْرِضِينَ

Transliteration wamā tatīhim min āyatin min āyāti rabbihim illā kānū ʿanhā muʿ'riḍīna

Amharic ከጌታቸውም ተዓምራት ማንኛይቱም ተዓምር አትመጣላቸውም፤ ከእርሷ የሚሸሹ ቢኾኑ እንጅ፡፡

Verse 47

وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ أَنفِقُوا۟ مِمَّا رَزَقَكُمُ ٱللَّهُ قَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنُطْعِمُ مَن لَّوْ يَشَآءُ ٱللَّهُ أَطْعَمَهُۥٓ إِنْ أَنتُمْ إِلَّا فِى ضَلَـٰلٍ مُّبِينٍ

Transliteration wa-idhā qīla lahum anfiqū mimmā razaqakumu l-lahu qāla alladhīna kafarū lilladhīna āmanū anuṭ'ʿimu man law yashāu l-lahu aṭʿamahu in antum illā fī ḍalālin mubīnin

Amharic ለእነርሱም «አላህ ከሰጣችሁ ሲሳይ ለግሱ» በተባሉ ጊዜ እነዚያ የካዱት ለእነዚያ ላመኑት «አላህ ቢሻ ኖሮ የሚያበላውን ሰው እናበላለን? እናንተ በግልጽ ስህተት ውስጥ እንጂ በሌላ ላይ አይደላችሁም» ይላሉ፡፡

Verse 48

وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَـٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَـٰدِقِينَ

Transliteration wayaqūlūna matā hādhā l-waʿdu in kuntum ṣādiqīna

Amharic «እውነተኞችም እንደኾናችሁ ይህ ቀጠሮ መቼ ነው?» ይላሉ፡፡

Verse 49

مَا يَنظُرُونَ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً تَأْخُذُهُمْ وَهُمْ يَخِصِّمُونَ

Transliteration mā yanẓurūna illā ṣayḥatan wāḥidatan takhudhuhum wahum yakhiṣṣimūna

Amharic እነርሱ የሚከራከሩ ሲኾኑ በድንገት የምትይዛቸው የኾነችን አንዲትን ጩኸት እንጂ ሌላን አይጠባበቁም፡፡

Verse 50

فَلَا يَسْتَطِيعُونَ تَوْصِيَةً وَلَآ إِلَىٰٓ أَهْلِهِمْ يَرْجِعُونَ

Transliteration falā yastaṭīʿūna tawṣiyatan walā ilā ahlihim yarjiʿūna

Amharic (ያን ጊዜ) መናዘዝንም አይችሉም፡፡ ወደ ቤተሰቦቻቸወም አይመለሱም፡፡

Verse 51

وَنُفِخَ فِى ٱلصُّورِ فَإِذَا هُم مِّنَ ٱلْأَجْدَاثِ إِلَىٰ رَبِّهِمْ يَنسِلُونَ

Transliteration wanufikha fī l-ṣūri fa-idhā hum mina l-ajdāthi ilā rabbihim yansilūna

Amharic በቀንዱም ይነፋል፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ከመቃብሮቻቸው ወደ ጌታቸው በፍጥነት ይገሰግሳሉ፡፡

Verse 52

قَالُوا۟ يَـٰوَيْلَنَا مَنۢ بَعَثَنَا مِن مَّرْقَدِنَا ۜ ۗ هَـٰذَا مَا وَعَدَ ٱلرَّحْمَـٰنُ وَصَدَقَ ٱلْمُرْسَلُونَ

Transliteration qālū yāwaylanā man baʿathanā min marqadinā hādhā mā waʿada l-raḥmānu waṣadaqa l-mur'salūna

Amharic «ወይ ጥፋታችን! ከመኝታችን ማን ቀሰቀሰን? ይህ ያ አዛኙ ጌታ (በእርሱ) የቀጠረን መልክተኞቹም እውነትን የነገሩን ነው» ይላሉ፡፡

Verse 53

إِن كَانَتْ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً فَإِذَا هُمْ جَمِيعٌ لَّدَيْنَا مُحْضَرُونَ

Transliteration in kānat illā ṣayḥatan wāḥidatan fa-idhā hum jamīʿun ladaynā muḥ'ḍarūna

Amharic (እርሷ) አንዲት ጩኸት እንጂ አይደለችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ እኛ ዘንድ የሚሰበሰቡ የሚቀርቡ ናቸው፡፡

Verse 54

فَٱلْيَوْمَ لَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْـًٔا وَلَا تُجْزَوْنَ إِلَّا مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Transliteration fal-yawma lā tuẓ'lamu nafsun shayan walā tuj'zawna illā mā kuntum taʿmalūna

Amharic «ዛሬም ማንኛይቱም ነፍስ ምንም አትበደልም፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን እንጂ ሌላን አትመነዱም» (ይባላሉ)፡፡

Verse 55

إِنَّ أَصْحَـٰبَ ٱلْجَنَّةِ ٱلْيَوْمَ فِى شُغُلٍ فَـٰكِهُونَ

Transliteration inna aṣḥāba l-janati l-yawma fī shughulin fākihūna

Amharic የገነት ሰዎች ዛሬ በእርግጥ በሥራዎች ውስጥ ተደሳቾች ናቸው፡፡

Verse 56

هُمْ وَأَزْوَٰجُهُمْ فِى ظِلَـٰلٍ عَلَى ٱلْأَرَآئِكِ مُتَّكِـُٔونَ

Transliteration hum wa-azwājuhum fī ẓilālin ʿalā l-arāiki muttakiūna

Amharic እነርሱም ሚስቶቻቸውም በጥላዎች ውስጥ ናቸው፡፡ ባለ አጎበር አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ናቸው፡፡

Verse 57

لَهُمْ فِيهَا فَـٰكِهَةٌ وَلَهُم مَّا يَدَّعُونَ

Transliteration lahum fīhā fākihatun walahum mā yaddaʿūna

Amharic በውስጧ ለእነርሱ ፍራፍሬዎች አሏቸው፡፡ ለእነርሱም የሚፈልጉት ሁሉ አልላቸው፡፡

Verse 58

سَلَـٰمٌ قَوْلًا مِّن رَّبٍّ رَّحِيمٍ

Transliteration salāmun qawlan min rabbin raḥīmin

Amharic (ለእነርሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አላቸው።

Verse 59

وَٱمْتَـٰزُوا۟ ٱلْيَوْمَ أَيُّهَا ٱلْمُجْرِمُونَ

Transliteration wa-im'tāzū l-yawma ayyuhā l-muj'rimūna

Amharic (ይላልም) «እናንተ አመጸኞች ሆይ! ዛሬ (ከምእምናን) ተለዩ፡፡»

Verse 60

۞ أَلَمْ أَعْهَدْ إِلَيْكُمْ يَـٰبَنِىٓ ءَادَمَ أَن لَّا تَعْبُدُوا۟ ٱلشَّيْطَـٰنَ ۖ إِنَّهُۥ لَكُمْ عَدُوٌّ مُّبِينٌ

Transliteration alam aʿhad ilaykum yābanī ādama an lā taʿbudū l-shayṭāna innahu lakum ʿaduwwun mubīnun

Amharic የአደም ልጆች ሆይ! ሰይጣንን አትገዙ፤ እርሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና በማለት ወደእናንተ አላዘዝኩምን?

Verse 61

وَأَنِ ٱعْبُدُونِى ۚ هَـٰذَا صِرَٰطٌ مُّسْتَقِيمٌ

Transliteration wa-ani uʿ'budūnī hādhā ṣirāṭun mus'taqīmun

Amharic ተገዙኝም፤ ይህ ቀጥተኘ መንገድ ነው፤ (በማለትም)፡፡

Verse 62

وَلَقَدْ أَضَلَّ مِنكُمْ جِبِلًّا كَثِيرًا ۖ أَفَلَمْ تَكُونُوا۟ تَعْقِلُونَ

Transliteration walaqad aḍalla minkum jibillan kathīran afalam takūnū taʿqilūna

Amharic ከእናንተም ብዙን ፍጡር በእርግጥ አሳስቷል፡፡ የምታውቁም አልነበራችሁምን?

Verse 63

هَـٰذِهِۦ جَهَنَّمُ ٱلَّتِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ

Transliteration hādhihi jahannamu allatī kuntum tūʿadūna

Amharic ይህቺ ያቺ ትቀጠሩዋት የነበረችው ገሀነም ናት፡፡

Verse 64

ٱصْلَوْهَا ٱلْيَوْمَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

Transliteration iṣ'lawhā l-yawma bimā kuntum takfurūna

Amharic ትክዱ በነበራችሁት ምክንያት ዛሬ ግቧት (ይባላሉ)፡፡

Verse 65

ٱلْيَوْمَ نَخْتِمُ عَلَىٰٓ أَفْوَٰهِهِمْ وَتُكَلِّمُنَآ أَيْدِيهِمْ وَتَشْهَدُ أَرْجُلُهُم بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Transliteration al-yawma nakhtimu ʿalā afwāhihim watukallimunā aydīhim watashhadu arjuluhum bimā kānū yaksibūna

Amharic ዛሬ በአፎቻቸው ላይ እናትምና እጆቻቸው ያነጋግሩናል፡፡ እግሮቻቸውም ይሠሩት በነበሩት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡

Verse 66

وَلَوْ نَشَآءُ لَطَمَسْنَا عَلَىٰٓ أَعْيُنِهِمْ فَٱسْتَبَقُوا۟ ٱلصِّرَٰطَ فَأَنَّىٰ يُبْصِرُونَ

Transliteration walaw nashāu laṭamasnā ʿalā aʿyunihim fa-is'tabaqū l-ṣirāṭa fa-annā yub'ṣirūna

Amharic ብንሻም ኖሮ በዐይኖቻቸው ላይ በአበስን ነበር፡፡ መንገድንም (እንደ ልመዳቸው) በተሽቀዳደሙ ነበር፡፡ እንዴትም ያያሉ?

Verse 67

وَلَوْ نَشَآءُ لَمَسَخْنَـٰهُمْ عَلَىٰ مَكَانَتِهِمْ فَمَا ٱسْتَطَـٰعُوا۟ مُضِيًّا وَلَا يَرْجِعُونَ

Transliteration walaw nashāu lamasakhnāhum ʿalā makānatihim famā is'taṭāʿū muḍiyyan walā yarjiʿūna

Amharic ብንሻም ኖሮ በስፍራቸው ላይ እንዳሉ ወደ ሌላ ፍጥረት በለወጠናቸው ነበር፡፡ መኼድንም መመለስንም ባልቻሉም ነበር፡፡

Verse 68

وَمَن نُّعَمِّرْهُ نُنَكِّسْهُ فِى ٱلْخَلْقِ ۖ أَفَلَا يَعْقِلُونَ

Transliteration waman nuʿammir'hu nunakkis'hu fī l-khalqi afalā yaʿqilūna

Amharic ዕድሜውንም የምናረዝመውን ሰው በፍጥረቱ (ወደ ደካማነት) እንመልሰዋለን፤ አያውቁምን?

Verse 69

وَمَا عَلَّمْنَـٰهُ ٱلشِّعْرَ وَمَا يَنۢبَغِى لَهُۥٓ ۚ إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ وَقُرْءَانٌ مُّبِينٌ

Transliteration wamā ʿallamnāhu l-shiʿ'ra wamā yanbaghī lahu in huwa illā dhik'run waqur'ānun mubīnun

Amharic (ሙሐመድን) ቅኔንም አላስተማርነውም፡፡ ለእርሱም አይግገባውም፡፡ እርሱ (መጽሐፉ) መገሰጫና ገላጭ ቁርኣን እንጅ (ቅኔ) አይደለም፡፡

Verse 70

لِّيُنذِرَ مَن كَانَ حَيًّا وَيَحِقَّ ٱلْقَوْلُ عَلَى ٱلْكَـٰفِرِينَ

Transliteration liyundhira man kāna ḥayyan wayaḥiqqa l-qawlu ʿalā l-kāfirīna

Amharic (ግሣጼነቱም ልቡ) ሕያው የኾነን ሰው ሊያስፈራራበትና ቃሉም በከሓዲዎች ላይ ይፈጸም ዘንድ ነው፡፡

Verse 71

أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَـٰمًا فَهُمْ لَهَا مَـٰلِكُونَ

Transliteration awalam yaraw annā khalaqnā lahum mimmā ʿamilat aydīnā anʿāman fahum lahā mālikūna

Amharic እኛ እጆቻችን (ኃይሎቻችን) ከሠሩት ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡

Verse 72

وَذَلَّلْنَـٰهَا لَهُمْ فَمِنْهَا رَكُوبُهُمْ وَمِنْهَا يَأْكُلُونَ

Transliteration wadhallalnāhā lahum famin'hā rakūbuhum wamin'hā yakulūna

Amharic ለእነርሱም ገራናት፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ውስጥ የሚጋልቡት አልለ፡፡ ከእርሷም ይበላሉ፡፡

Verse 73

وَلَهُمْ فِيهَا مَنَـٰفِعُ وَمَشَارِبُ ۖ أَفَلَا يَشْكُرُونَ

Transliteration walahum fīhā manāfiʿu wamashāribu afalā yashkurūna

Amharic ለእነርሱም በእርሷ ውስጥ (ሌሎች) ጥቅሞች መጠጦችም አሉዋቸው፡፡ ታዲያ አያመሰግኑምን;

Verse 74

وَٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ ءَالِهَةً لَّعَلَّهُمْ يُنصَرُونَ

Transliteration wa-ittakhadhū min dūni l-lahi ālihatan laʿallahum yunṣarūna

Amharic መረዳትንም በመከጀል ከአላህ ሌላ አማልክትን ያዙ፡፡

Verse 75

لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَهُمْ وَهُمْ لَهُمْ جُندٌ مُّحْضَرُونَ

Transliteration lā yastaṭīʿūna naṣrahum wahum lahum jundun muḥ'ḍarūna

Amharic መርዳታቸውን አይችሉም፡፡ እነርሱም ለእርሳቸው (ወደ እሳት) የተቀረቡ ሰራዊት ናቸው፡፡

Verse 76

فَلَا يَحْزُنكَ قَوْلُهُمْ ۘ إِنَّا نَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ

Transliteration falā yaḥzunka qawluhum innā naʿlamu mā yusirrūna wamā yuʿ'linūna

Amharic ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ እኛ የሚደብቁትንም የሚገልጹትንም እናውቃለንና፡፡

Verse 77

أَوَلَمْ يَرَ ٱلْإِنسَـٰنُ أَنَّا خَلَقْنَـٰهُ مِن نُّطْفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُّبِينٌ

Transliteration awalam yara l-insānu annā khalaqnāhu min nuṭ'fatin fa-idhā huwa khaṣīmun mubīnun

Amharic ሰውየው እኛ ከፍቶት ጠብታ የፈጠርነው መኾናችን አላወቀምን? ወዲያውም እርሱ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይኾናልን?

Verse 78

وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِىَ خَلْقَهُۥ ۖ قَالَ مَن يُحْىِ ٱلْعِظَـٰمَ وَهِىَ رَمِيمٌ

Transliteration waḍaraba lanā mathalan wanasiya khalqahu qāla man yuḥ'yī l-ʿiẓāma wahiya ramīmun

Amharic ለእኛም ምሳሌን አደረገልን፡፡ መፈጠሩንም ረሳ፡፡ «አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲኾኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው?» አለ፡፡

Verse 79

قُلْ يُحْيِيهَا ٱلَّذِىٓ أَنشَأَهَآ أَوَّلَ مَرَّةٍ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ خَلْقٍ عَلِيمٌ

Transliteration qul yuḥ'yīhā alladhī ansha-ahā awwala marratin wahuwa bikulli khalqin ʿalīmun

Amharic «ያ በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ሕያው ያደርጋታል፡፡ እርሱም በፍጡሩ ሁሉ (ኹኔታ) ዐዋቂ ነው» በለው፡፡

Verse 80

ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُم مِّنَ ٱلشَّجَرِ ٱلْأَخْضَرِ نَارًا فَإِذَآ أَنتُم مِّنْهُ تُوقِدُونَ

Transliteration alladhī jaʿala lakum mina l-shajari l-akhḍari nāran fa-idhā antum min'hu tūqidūna

Amharic ያ ለእናንተ በእርጥብ ዛፍ እሳትን ያደረገላችሁ ነው፡፡ ወዲያውኑም እናንተ ከእርሱ ታቀጣጥላላችሁ፡፡

Verse 81

أَوَلَيْسَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِقَـٰدِرٍ عَلَىٰٓ أَن يَخْلُقَ مِثْلَهُم ۚ بَلَىٰ وَهُوَ ٱلْخَلَّـٰقُ ٱلْعَلِيمُ

Transliteration awalaysa alladhī khalaqa l-samāwāti wal-arḍa biqādirin ʿalā an yakhluqa mith'lahum balā wahuwa l-khalāqu l-ʿalīmu

Amharic ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ አይደለምን? ነው እንጅ፡፡ እርሱም በብዙ ፈጣሪው ዐዋቂው ነው፡፡

Verse 82

إِنَّمَآ أَمْرُهُۥٓ إِذَآ أَرَادَ شَيْـًٔا أَن يَقُولَ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ

Transliteration innamā amruhu idhā arāda shayan an yaqūla lahu kun fayakūnu

Amharic ነገሩም አንዳችን በሻ ጊዜ ኹን ማለት ነው፡፡ ወዲያው ይኾናልም፡፡

Verse 83

فَسُبْحَـٰنَ ٱلَّذِى بِيَدِهِۦ مَلَكُوتُ كُلِّ شَىْءٍ وَإِلَيْهِ تُرْجَعُونَ

Transliteration fasub'ḥāna alladhī biyadihi malakūtu kulli shayin wa-ilayhi tur'jaʿūna

Amharic ያ የነገሩ ሁሉ ስልጣን በእጁ የኾነው ጌታ ጥራት ይገባው፡፡ ወደእርሱም ትመለሳላችሁ፡፡

Read Surah Ya-Sin in another language

All languages

All 114 surahs in Amharic: the Qur’an in Amharic.

Learn it in MyDugsi

Amharic translation: Sadiq and Sani, from Quran.com. Transliteration: Quran.com. Recitation: Mishary Alafasy, from EveryAyah.com. MyDugsi is a learning aid, not a replacement for a qualified teacher.