MyDugsiStart learning

Surah Al-Anfal in Amharic: translation and audio

Surah 8 · الأنفال · The Spoils of War · 75 verses

Surah Al-Anfal verse by verse: the Arabic with a recitation you can repeat, the transliteration, and the Amharic translation by Sadiq and Sani. For the meaning of every word, see Surah Al-Anfal word by word in English.

Verse 1

يَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْأَنفَالِ ۖ قُلِ ٱلْأَنفَالُ لِلَّهِ وَٱلرَّسُولِ ۖ فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ وَأَصْلِحُوا۟ ذَاتَ بَيْنِكُمْ ۖ وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥٓ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

Transliteration yasalūnaka ʿani l-anfāli quli l-anfālu lillahi wal-rasūli fa-ittaqū l-laha wa-aṣliḥū dhāta baynikum wa-aṭīʿū l-laha warasūlahu in kuntum mu'minīna

Amharic ከጦር ዘረፋ ገንዘቦች ይጠይቁሃል፡፡ «የዘረፋ ገንዘቦች የአላህና የመልክተኛው ናቸው፡፡» ስለዚህ አላህን ፍሩ፡፡ በመካከላችሁ ያለችውንም ኹኔታ አሳምሩ፡፡ አማኞችም እንደኾናችሁ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ በላቸው፡፡

Verse 2

إِنَّمَا ٱلْمُؤْمِنُونَ ٱلَّذِينَ إِذَا ذُكِرَ ٱللَّهُ وَجِلَتْ قُلُوبُهُمْ وَإِذَا تُلِيَتْ عَلَيْهِمْ ءَايَـٰتُهُۥ زَادَتْهُمْ إِيمَـٰنًا وَعَلَىٰ رَبِّهِمْ يَتَوَكَّلُونَ

Transliteration innamā l-mu'minūna alladhīna idhā dhukira l-lahu wajilat qulūbuhum wa-idhā tuliyat ʿalayhim āyātuhu zādathum īmānan waʿalā rabbihim yatawakkalūna

Amharic ፍጹም ምእምናን እነዚያ አላህ በተወሳ ጊዜ ልቦቻቸው የሚፈሩት፣ በነሱም ላይ አንቀጾቻችን በተነበቡ ጊዜ እምነትን የሚጨምሩላቸው፣ በጌታቸውም ላይ ብቻ የሚመኩት ናቸው፡፡

Verse 3

ٱلَّذِينَ يُقِيمُونَ ٱلصَّلَوٰةَ وَمِمَّا رَزَقْنَـٰهُمْ يُنفِقُونَ

Transliteration alladhīna yuqīmūna l-ṣalata wamimmā razaqnāhum yunfiqūna

Amharic እነዚያ ሶላትን ደንቡን አሟልተው የሚሰግዱ ከሰጠናቸውም ሲሳይ የሚለግሱ ናቸው፡፡

Verse 4

أُو۟لَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُمْ دَرَجَـٰتٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَمَغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

Transliteration ulāika humu l-mu'minūna ḥaqqan lahum darajātun ʿinda rabbihim wamaghfiratun wariz'qun karīmun

Amharic እነዚያ በእውነት አማኞች እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለእነሱ በጌታቸው ዘንድ ደረጃዎች ምህረትና የከበረ ሲሳይም አላቸው፡፡

Verse 5

كَمَآ أَخْرَجَكَ رَبُّكَ مِنۢ بَيْتِكَ بِٱلْحَقِّ وَإِنَّ فَرِيقًا مِّنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ لَكَـٰرِهُونَ

Transliteration kamā akhrajaka rabbuka min baytika bil-ḥaqi wa-inna farīqan mina l-mu'minīna lakārihūna

Amharic (ይህ በዘረፋ ክፍያ የከፊሉ ሰው መጥላት) ከምእምናን ከፊሉ የጠሉ ሲኾኑ ጌታህ ከቤትህ በእውነት ላይ ኾነህ እንዳወጣህ ነው፡፡

Verse 6

يُجَـٰدِلُونَكَ فِى ٱلْحَقِّ بَعْدَ مَا تَبَيَّنَ كَأَنَّمَا يُسَاقُونَ إِلَى ٱلْمَوْتِ وَهُمْ يَنظُرُونَ

Transliteration yujādilūnaka fī l-ḥaqi baʿdamā tabayyana ka-annamā yusāqūna ilā l-mawti wahum yanẓurūna

Amharic እነርሱ እያዩ ወደሞት እንደሚነዱ ኾነው በእውነቱ ነገር (በመጋደል ግዴታነት) ከተገለጸላቸው በኋላ ይከራከሩሃል፡፡

Verse 7

وَإِذْ يَعِدُكُمُ ٱللَّهُ إِحْدَى ٱلطَّآئِفَتَيْنِ أَنَّهَا لَكُمْ وَتَوَدُّونَ أَنَّ غَيْرَ ذَاتِ ٱلشَّوْكَةِ تَكُونُ لَكُمْ وَيُرِيدُ ٱللَّهُ أَن يُحِقَّ ٱلْحَقَّ بِكَلِمَـٰتِهِۦ وَيَقْطَعَ دَابِرَ ٱلْكَـٰفِرِينَ

Transliteration wa-idh yaʿidukumu l-lahu iḥ'dā l-ṭāifatayni annahā lakum watawaddūna anna ghayra dhāti l-shawkati takūnu lakum wayurīdu l-lahu an yuḥiqqa l-ḥaqa bikalimātihi wayaqṭaʿa dābira l-kāfirīna

Amharic አላህም ከሁለቱ ጭፍሮች አንደኛዋን እርሷ ለናንተ ናት ሲል ተስፋ በሰጣችሁ ጊዜ፣ የሀይል ባለቤት ያልኾነችውም (ነጋዴይቱ) ለናንተ ልትኾን በወደዳችሁ ጊዜ፣ አላህም በተስፋ ቃላቱ እውነትን ማረጋገጡን ሊገልጽና የከሓዲዎችንም መጨረሻ ሊቆርጥ በሻ ጊዜ (የኾነውን አስታውስ)፡፡

Verse 8

لِيُحِقَّ ٱلْحَقَّ وَيُبْطِلَ ٱلْبَـٰطِلَ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُجْرِمُونَ

Transliteration liyuḥiqqa l-ḥaqa wayub'ṭila l-bāṭila walaw kariha l-muj'rimūna

Amharic (ይህንንም ያደረገው) አጋሪዎቹ ቢጠሉም እውነቱን ሊያረጋግጥ ክህደትንም ሊያጠፋ ነው፡፡

Verse 9

إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَٱسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّى مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ ٱلْمَلَـٰٓئِكَةِ مُرْدِفِينَ

Transliteration idh tastaghīthūna rabbakum fa-is'tajāba lakum annī mumiddukum bi-alfin mina l-malāikati mur'difīna

Amharic ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን (አስታውሱ)፡፡

Verse 10

وَمَا جَعَلَهُ ٱللَّهُ إِلَّا بُشْرَىٰ وَلِتَطْمَئِنَّ بِهِۦ قُلُوبُكُمْ ۚ وَمَا ٱلنَّصْرُ إِلَّا مِنْ عِندِ ٱللَّهِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Transliteration wamā jaʿalahu l-lahu illā bush'rā walitaṭma-inna bihi qulūbukum wamā l-naṣru illā min ʿindi l-lahi inna l-laha ʿazīzun ḥakīmun

Amharic አላህም (ይኽንን ርዳታ) ለብስራትና ልቦቻችሁ በርሱ ሊረኩበት እንጂ ለሌላ አላደረገውም፡፡ ድልም መንሳት ከአላህ ዘንድ እንጂ ከሌላ አይደለም፡፡ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡

Verse 11

إِذْ يُغَشِّيكُمُ ٱلنُّعَاسَ أَمَنَةً مِّنْهُ وَيُنَزِّلُ عَلَيْكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ مَآءً لِّيُطَهِّرَكُم بِهِۦ وَيُذْهِبَ عَنكُمْ رِجْزَ ٱلشَّيْطَـٰنِ وَلِيَرْبِطَ عَلَىٰ قُلُوبِكُمْ وَيُثَبِّتَ بِهِ ٱلْأَقْدَامَ

Transliteration idh yughashīkumu l-nuʿāsa amanatan min'hu wayunazzilu ʿalaykum mina l-samāi māan liyuṭahhirakum bihi wayudh'hiba ʿankum rij'za l-shayṭāni waliyarbiṭa ʿalā qulūbikum wayuthabbita bihi l-aqdāma

Amharic ከእርሱ በኾነው ጸጥታ (በጦር ግንባር) በእንቅልፍ በሸፈናችሁና ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፣ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከእናንተ ሊያስወግድላችሁ፣ ልቦቻችሁንም (በትዕግስት) ሊያጠነክርላችሁ፣ በእርሱም ጫማዎችን (በአሸዋው ላይ) ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡

Verse 12

إِذْ يُوحِى رَبُّكَ إِلَى ٱلْمَلَـٰٓئِكَةِ أَنِّى مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا۟ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ۚ سَأُلْقِى فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلرُّعْبَ فَٱضْرِبُوا۟ فَوْقَ ٱلْأَعْنَاقِ وَٱضْرِبُوا۟ مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍ

Transliteration idh yūḥī rabbuka ilā l-malāikati annī maʿakum fathabbitū alladhīna āmanū sa-ul'qī fī qulūbi alladhīna kafarū l-ruʿ'ba fa-iḍ'ribū fawqa l-aʿnāqi wa-iḍ'ribū min'hum kulla banānin

Amharic ጌታህ ወደ መላእክቱ «»እኔ (በእርዳታዬ) ከእናንተ ጋር ነኝና እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ፡፡ በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፡፡ ከአንገቶችም በላይ (ራሶችን) ምቱ፡፡ ከእነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ፡፡ ሲል ያወረደውን (አስታውስ)፡፡

Verse 13

ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ شَآقُّوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ ۚ وَمَن يُشَاقِقِ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ فَإِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Transliteration dhālika bi-annahum shāqqū l-laha warasūlahu waman yushāqiqi l-laha warasūlahu fa-inna l-laha shadīdu l-ʿiqābi

Amharic ይህ እነርሱ አላህንና መልክተኛውን ስለተቃወሙ ነው፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚቃወም ሁሉ አላህ ቅጣቱ ብርቱ ነው፡፡

Verse 14

ذَٰلِكُمْ فَذُوقُوهُ وَأَنَّ لِلْكَـٰفِرِينَ عَذَابَ ٱلنَّارِ

Transliteration dhālikum fadhūqūhu wa-anna lil'kāfirīna ʿadhāba l-nāri

Amharic ይህ (ቅጣታችሁ ነው) ቅመሱትም፡፡ ለከሓዲዎችም የእሳት ቅጣት በእርግጥ አለባቸው፡፡

Verse 15

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا لَقِيتُمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ زَحْفًا فَلَا تُوَلُّوهُمُ ٱلْأَدْبَارَ

Transliteration yāayyuhā alladhīna āmanū idhā laqītumu alladhīna kafarū zaḥfan falā tuwallūhumu l-adbāra

Amharic እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን የካዱትን ሰዎች (ለጦር) ሲጓዙ ባገኛችኋቸው ጊዜ ጀርባዎችን አታዙሩላቸው፡፡

Verse 16

وَمَن يُوَلِّهِمْ يَوْمَئِذٍ دُبُرَهُۥٓ إِلَّا مُتَحَرِّفًا لِّقِتَالٍ أَوْ مُتَحَيِّزًا إِلَىٰ فِئَةٍ فَقَدْ بَآءَ بِغَضَبٍ مِّنَ ٱللَّهِ وَمَأْوَىٰهُ جَهَنَّمُ ۖ وَبِئْسَ ٱلْمَصِيرُ

Transliteration waman yuwallihim yawma-idhin duburahu illā mutaḥarrifan liqitālin aw mutaḥayyizan ilā fi-atin faqad bāa bighaḍabin mina l-lahi wamawāhu jahannamu wabi'sa l-maṣīru

Amharic ያን ጊዜም ለግድያ ለመዘዋወር ወይም ወደ ሠራዊት ለመቀላቀል ሳይኾን ጀርባውን የሚያዞርላቸው ሰው ከአላህ በኾነ ቁጣ በእርግጥ ተመለሰ፡፡ መኖሪያውም ገሀነም ናት፡፡ መመለሻይቱም ከፋች፡፡

Verse 17

فَلَمْ تَقْتُلُوهُمْ وَلَـٰكِنَّ ٱللَّهَ قَتَلَهُمْ ۚ وَمَا رَمَيْتَ إِذْ رَمَيْتَ وَلَـٰكِنَّ ٱللَّهَ رَمَىٰ ۚ وَلِيُبْلِىَ ٱلْمُؤْمِنِينَ مِنْهُ بَلَآءً حَسَنًا ۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Transliteration falam taqtulūhum walākinna l-laha qatalahum wamā ramayta idh ramayta walākinna l-laha ramā waliyub'liya l-mu'minīna min'hu balāan ḥasanan inna l-laha samīʿun ʿalīmun

Amharic አልገደላችኋቸውም ግን አላህ ገደላቸው፡፡ (ጭብጥን ዐፈር) በወረወርክም ጊዜ አንተ አልወረወርክም፡፡ ግን አላህ ወረወረ (ወደ ዓይኖቻቸው አደረሰው)፡፡ ለአማኞችም ከርሱ የኾነን መልካም ጸጋ ለመስጠት (ይህን አደረገ)፡፡ አላህ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡

Verse 18

ذَٰلِكُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ مُوهِنُ كَيْدِ ٱلْكَـٰفِرِينَ

Transliteration dhālikum wa-anna l-laha mūhinu kaydi l-kāfirīna

Amharic ይህ (ዕውነት ነው)፡፡ አላህም የከሓዲዎችን ተንኮል አድካሚ ነው፡፡

Verse 19

إِن تَسْتَفْتِحُوا۟ فَقَدْ جَآءَكُمُ ٱلْفَتْحُ ۖ وَإِن تَنتَهُوا۟ فَهُوَ خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ وَإِن تَعُودُوا۟ نَعُدْ وَلَن تُغْنِىَ عَنكُمْ فِئَتُكُمْ شَيْـًٔا وَلَوْ كَثُرَتْ وَأَنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Transliteration in tastaftiḥū faqad jāakumu l-fatḥu wa-in tantahū fahuwa khayrun lakum wa-in taʿūdū naʿud walan tugh'niya ʿankum fi-atukum shayan walaw kathurat wa-anna l-laha maʿa l-mu'minīna

Amharic ፍትሕን (ፍርድን) ብትጠይቁ ፍትሑ በእርግጥ መጥቶላችኋል፡፡ (ክህደትንና መዋጋትን) ብትከለከሉም እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ (ወደ መጋደል) ብትመለሱም እንመለሳለን፡፡ ሰራዊታችሁም ብትበዛም እንኳ ከናንተ ምንም አትጠቅማችሁም፡፡ አላህም ከምእምናን ጋር ነው፡፡

Verse 20

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَوَلَّوْا۟ عَنْهُ وَأَنتُمْ تَسْمَعُونَ

Transliteration yāayyuhā alladhīna āmanū aṭīʿū l-laha warasūlahu walā tawallaw ʿanhu wa-antum tasmaʿūna

Amharic እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ፡፡ እናንተም የምትሰሙ ስትኾኑ ከርሱ አትሽሹ፡፡

Verse 21

وَلَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ قَالُوا۟ سَمِعْنَا وَهُمْ لَا يَسْمَعُونَ

Transliteration walā takūnū ka-alladhīna qālū samiʿ'nā wahum lā yasmaʿūna

Amharic እንደነዚያም እነሱ የማይሰሙ ሲኾኑ ሰማን እንዳሉት አትሁኑ፡፡

Verse 22

۞ إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلصُّمُّ ٱلْبُكْمُ ٱلَّذِينَ لَا يَعْقِلُونَ

Transliteration inna sharra l-dawābi ʿinda l-lahi l-ṣumu l-buk'mu alladhīna lā yaʿqilūna

Amharic ከተንቀሳቃሾች ሁሉ አላህ ዘንድ መጥፎ ተንኮለኞች እነዚያ የማያውቁት፣ ደንቆሮዎቹ፣ ዲዳዎቹ ናቸው፡፡

Verse 23

وَلَوْ عَلِمَ ٱللَّهُ فِيهِمْ خَيْرًا لَّأَسْمَعَهُمْ ۖ وَلَوْ أَسْمَعَهُمْ لَتَوَلَّوا۟ وَّهُم مُّعْرِضُونَ

Transliteration walaw ʿalima l-lahu fīhim khayran la-asmaʿahum walaw asmaʿahum latawallaw wahum muʿ'riḍūna

Amharic በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አላህ ባወቀ ኖሮ (የመረዳትን መስማት) ባሰማቸው ነበር፡፡ (ደግ የሌለባቸው መኾኑን ሲያውቅ) ባሰማቸውም ኖሮ እነሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር፡፡

Verse 24

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ٱسْتَجِيبُوا۟ لِلَّهِ وَلِلرَّسُولِ إِذَا دَعَاكُمْ لِمَا يُحْيِيكُمْ ۖ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ يَحُولُ بَيْنَ ٱلْمَرْءِ وَقَلْبِهِۦ وَأَنَّهُۥٓ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ

Transliteration yāayyuhā alladhīna āmanū is'tajībū lillahi walilrrasūli idhā daʿākum limā yuḥ'yīkum wa-iʿ'lamū anna l-laha yaḥūlu bayna l-mari waqalbihi wa-annahu ilayhi tuḥ'sharūna

Amharic እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ፡፡ አላህም በሰውየውና በልቡ መካከል የሚጋርድ መኾኑን ወደርሱም የምትሰበሰቡ መኾናችሁን እወቁ፡፡

Verse 25

وَٱتَّقُوا۟ فِتْنَةً لَّا تُصِيبَنَّ ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنكُمْ خَآصَّةً ۖ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Transliteration wa-ittaqū fit'natan lā tuṣībanna alladhīna ẓalamū minkum khāṣṣatan wa-iʿ'lamū anna l-laha shadīdu l-ʿiqābi

Amharic ከናንተም ውስጥ እነዚያን የበደሉትን ብቻ ለይታ የማትነካን ፈተና ተጠንቀቁ፡፡ አላህም ቅጣቱ ብርቱ መኾኑን እወቁ፡፡

Verse 26

وَٱذْكُرُوٓا۟ إِذْ أَنتُمْ قَلِيلٌ مُّسْتَضْعَفُونَ فِى ٱلْأَرْضِ تَخَافُونَ أَن يَتَخَطَّفَكُمُ ٱلنَّاسُ فَـَٔاوَىٰكُمْ وَأَيَّدَكُم بِنَصْرِهِۦ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَـٰتِ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Transliteration wa-udh'kurū idh antum qalīlun mus'taḍʿafūna fī l-arḍi takhāfūna an yatakhaṭṭafakumu l-nāsu faāwākum wa-ayyadakum binaṣrihi warazaqakum mina l-ṭayibāti laʿallakum tashkurūna

Amharic እናንተም በምድር ላይ የተናቃችሁ ጥቂቶች ኾናችሁ ሳላችሁ ሰዎች ሊነጥቁዋችሁ የምትፈሩ ስትኾኑ ያስጠጋችሁን በእርዳታውም ያበረታችሁን ከመልካሞች ሲሳዮችም ታመሰግኑ ዘንድ የሰጣችሁን አስታውሱ፡፡

Verse 27

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا تَخُونُوا۟ ٱللَّهَ وَٱلرَّسُولَ وَتَخُونُوٓا۟ أَمَـٰنَـٰتِكُمْ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ

Transliteration yāayyuhā alladhīna āmanū lā takhūnū l-laha wal-rasūla watakhūnū amānātikum wa-antum taʿlamūna

Amharic እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህንና መልክተኛውን አትክዱ፡፡ አደራዎቻችሁንም እናንተ እያወቃችሁ አትክዱ፡፡

Verse 28

وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَآ أَمْوَٰلُكُمْ وَأَوْلَـٰدُكُمْ فِتْنَةٌ وَأَنَّ ٱللَّهَ عِندَهُۥٓ أَجْرٌ عَظِيمٌ

Transliteration wa-iʿ'lamū annamā amwālukum wa-awlādukum fit'natun wa-anna l-laha ʿindahu ajrun ʿaẓīmun

Amharic ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁም ፈተና ብቻ መኾናቸውንና አላህም እሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ ያለው መኾኑን እወቁ፡፡

Verse 29

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَتَّقُوا۟ ٱللَّهَ يَجْعَل لَّكُمْ فُرْقَانًا وَيُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّـَٔاتِكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ ذُو ٱلْفَضْلِ ٱلْعَظِيمِ

Transliteration yāayyuhā alladhīna āmanū in tattaqū l-laha yajʿal lakum fur'qānan wayukaffir ʿankum sayyiātikum wayaghfir lakum wal-lahu dhū l-faḍli l-ʿaẓīmi

Amharic እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያን ብርሃን ያደርግላችኋል፡፡ ክፉ ሥራዎቻችሁንም ከእናንተ ላይ ያብስላችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው፡፡

Verse 30

وَإِذْ يَمْكُرُ بِكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لِيُثْبِتُوكَ أَوْ يَقْتُلُوكَ أَوْ يُخْرِجُوكَ ۚ وَيَمْكُرُونَ وَيَمْكُرُ ٱللَّهُ ۖ وَٱللَّهُ خَيْرُ ٱلْمَـٰكِرِينَ

Transliteration wa-idh yamkuru bika alladhīna kafarū liyuth'bitūka aw yaqtulūka aw yukh'rijūka wayamkurūna wayamkuru l-lahu wal-lahu khayru l-mākirīna

Amharic እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው፡፡

Verse 31

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَـٰتُنَا قَالُوا۟ قَدْ سَمِعْنَا لَوْ نَشَآءُ لَقُلْنَا مِثْلَ هَـٰذَآ ۙ إِنْ هَـٰذَآ إِلَّآ أَسَـٰطِيرُ ٱلْأَوَّلِينَ

Transliteration wa-idhā tut'lā ʿalayhim āyātunā qālū qad samiʿ'nā law nashāu laqul'nā mith'la hādhā in hādhā illā asāṭīru l-awalīna

Amharic አንቀጾቻችንም በነሱ ላይ በተነበቡ ጊዜ «በእርግጥ ሰምተናል፤ በሻን ኖሮ የዚህን ብጤ ባልን ነበር፤ ይህ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ጽሑፍ ተረቶች እንጂ ሌላ አይደለም» ይላሉ፡፡

Verse 32

وَإِذْ قَالُوا۟ ٱللَّهُمَّ إِن كَانَ هَـٰذَا هُوَ ٱلْحَقَّ مِنْ عِندِكَ فَأَمْطِرْ عَلَيْنَا حِجَارَةً مِّنَ ٱلسَّمَآءِ أَوِ ٱئْتِنَا بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

Transliteration wa-idh qālū l-lahuma in kāna hādhā huwa l-ḥaqa min ʿindika fa-amṭir ʿalaynā ḥijāratan mina l-samāi awi i'tinā biʿadhābin alīmin

Amharic «ጌታችን ሆይ! ይህ እርሱ ካንተ ዘንድ (የተወረደ) እውነት እንደ ኾነ በኛ ላይ ከሰማይ ድንጋዮችን አዝንብብን ወይም አሳማሚ ቅጣትን አምጣብን» ባሉም ጊዜ (አስታውስ)

Verse 33

وَمَا كَانَ ٱللَّهُ لِيُعَذِّبَهُمْ وَأَنتَ فِيهِمْ ۚ وَمَا كَانَ ٱللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ

Transliteration wamā kāna l-lahu liyuʿadhibahum wa-anta fīhim wamā kāna l-lahu muʿadhibahum wahum yastaghfirūna

Amharic አላህም አንተ በውስጣቸው እያለህ (ድንጋይ በማዝነብና ባሳማሚ ቅጣት) የሚቀጣቸው አይደለም፡፡ አላህም እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡

Verse 34

وَمَا لَهُمْ أَلَّا يُعَذِّبَهُمُ ٱللَّهُ وَهُمْ يَصُدُّونَ عَنِ ٱلْمَسْجِدِ ٱلْحَرَامِ وَمَا كَانُوٓا۟ أَوْلِيَآءَهُۥٓ ۚ إِنْ أَوْلِيَآؤُهُۥٓ إِلَّا ٱلْمُتَّقُونَ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَهُمْ لَا يَعْلَمُونَ

Transliteration wamā lahum allā yuʿadhibahumu l-lahu wahum yaṣuddūna ʿani l-masjidi l-ḥarāmi wamā kānū awliyāahu in awliyāuhu illā l-mutaqūna walākinna aktharahum lā yaʿlamūna

Amharic እነሱ ከተከበረው መስጊድ የሚከለክሉ ሲኾኑም አላህ (በሰይፍ) የማይቀጣቸው ለነሱ ምን አልላቸው (የቤቱ) ጠባቂዎችም አልነበሩም፡፡ ጠባቂዎቹ (ክሕደትን) ተጠንቃቂዎቹ እንጂ ሌሎቹ አይደሉም፡፡ ግን አብዛኛዎቻቸው አያውቁም፡፡

Verse 35

وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمْ عِندَ ٱلْبَيْتِ إِلَّا مُكَآءً وَتَصْدِيَةً ۚ فَذُوقُوا۟ ٱلْعَذَابَ بِمَا كُنتُمْ تَكْفُرُونَ

Transliteration wamā kāna ṣalātuhum ʿinda l-bayti illā mukāan wataṣdiyatan fadhūqū l-ʿadhāba bimā kuntum takfurūna

Amharic በቤቱ ዘንድም (በካዕባ) ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም፡፡ ትክዱት በነበራችሁትም ነገር ቅጣትን ቅመሱ (ይባላሉ)፡፡

Verse 36

إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يُنفِقُونَ أَمْوَٰلَهُمْ لِيَصُدُّوا۟ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ ۚ فَسَيُنفِقُونَهَا ثُمَّ تَكُونُ عَلَيْهِمْ حَسْرَةً ثُمَّ يُغْلَبُونَ ۗ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِلَىٰ جَهَنَّمَ يُحْشَرُونَ

Transliteration inna alladhīna kafarū yunfiqūna amwālahum liyaṣuddū ʿan sabīli l-lahi fasayunfiqūnahā thumma takūnu ʿalayhim ḥasratan thumma yugh'labūna wa-alladhīna kafarū ilā jahannama yuḥ'sharūna

Amharic እነዚያ የካዱት ከአላህ መንገድ ሊከለክሉ ገንዘቦቻቸውን ያወጣሉ፡፡ በእርግጥም ያወጡዋታል፡፡ ከዚያም በእነሱ ላይ ጸጸት ትኾንባቸዋለች፡፡ ከዚያም ይሸነፋሉ፡፡ እነዚያም የካዱት ወደ ገሀነም ይሰበሰባሉ፡፡

Verse 37

لِيَمِيزَ ٱللَّهُ ٱلْخَبِيثَ مِنَ ٱلطَّيِّبِ وَيَجْعَلَ ٱلْخَبِيثَ بَعْضَهُۥ عَلَىٰ بَعْضٍ فَيَرْكُمَهُۥ جَمِيعًا فَيَجْعَلَهُۥ فِى جَهَنَّمَ ۚ أُو۟لَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلْخَـٰسِرُونَ

Transliteration liyamīza l-lahu l-khabītha mina l-ṭayibi wayajʿala l-khabītha baʿḍahu ʿalā baʿḍin fayarkumahu jamīʿan fayajʿalahu fī jahannama ulāika humu l-khāsirūna

Amharic አላህ መጥፎውን ከመልካሙ ሊለይ መጥፎውንም ከፊሉን በከፊሉ ላይ ሊያደርግና ባንድ ላይ ሊያነባብረው በገሀነም ውስጥም ሊያደርገው (ይሰበሰባሉ)፡፡ እነዚያ እነሱ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡

Verse 38

قُل لِّلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِن يَنتَهُوا۟ يُغْفَرْ لَهُم مَّا قَدْ سَلَفَ وَإِن يَعُودُوا۟ فَقَدْ مَضَتْ سُنَّتُ ٱلْأَوَّلِينَ

Transliteration qul lilladhīna kafarū in yantahū yugh'far lahum mā qad salafa wa-in yaʿūdū faqad maḍat sunnatu l-awalīna

Amharic ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል፡፡ (ወደ መጋደል) ቢመለሱም (እናጠፋቸዋለን)፡፡ የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፋለችና፡፡

Verse 39

وَقَـٰتِلُوهُمْ حَتَّىٰ لَا تَكُونَ فِتْنَةٌ وَيَكُونَ ٱلدِّينُ كُلُّهُۥ لِلَّهِ ۚ فَإِنِ ٱنتَهَوْا۟ فَإِنَّ ٱللَّهَ بِمَا يَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

Transliteration waqātilūhum ḥattā lā takūna fit'natun wayakūna l-dīnu kulluhu lillahi fa-ini intahaw fa-inna l-laha bimā yaʿmalūna baṣīrun

Amharic ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው፡፡ ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

Verse 40

وَإِن تَوَلَّوْا۟ فَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّ ٱللَّهَ مَوْلَىٰكُمْ ۚ نِعْمَ ٱلْمَوْلَىٰ وَنِعْمَ ٱلنَّصِيرُ

Transliteration wa-in tawallaw fa-iʿ'lamū anna l-laha mawlākum niʿ'ma l-mawlā waniʿ'ma l-naṣīru

Amharic (ከእምነት) ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መኾኑን ዕወቁ፡፡ (እርሱ) ምን ያምር ጠባቂ! ምን ያምርም ረዳት!

Verse 41

۞ وَٱعْلَمُوٓا۟ أَنَّمَا غَنِمْتُم مِّن شَىْءٍ فَأَنَّ لِلَّهِ خُمُسَهُۥ وَلِلرَّسُولِ وَلِذِى ٱلْقُرْبَىٰ وَٱلْيَتَـٰمَىٰ وَٱلْمَسَـٰكِينِ وَٱبْنِ ٱلسَّبِيلِ إِن كُنتُمْ ءَامَنتُم بِٱللَّهِ وَمَآ أَنزَلْنَا عَلَىٰ عَبْدِنَا يَوْمَ ٱلْفُرْقَانِ يَوْمَ ٱلْتَقَى ٱلْجَمْعَانِ ۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ

Transliteration wa-iʿ'lamū annamā ghanim'tum min shayin fa-anna lillahi khumusahu walilrrasūli walidhī l-qur'bā wal-yatāmā wal-masākīni wa-ib'ni l-sabīli in kuntum āmantum bil-lahi wamā anzalnā ʿalā ʿabdinā yawma l-fur'qāni yawma l-taqā l-jamʿāni wal-lahu ʿalā kulli shayin qadīrun

Amharic ከማንኛውም ነገር በጦር (ከከሓዲዎች) የዘረፋችሁትም አንድ አምስተኛው ለአላህና ለመልክተኛው፣ (ለነቢዩ) የዝምድና ባለቤቶችም፣ ለየቲሞችም፣ ለምስኪኖችም፣ ለመንገደኛም የተገባ መኾኑን ዕውቁ፣ በአላህና በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት (በበድር) ቀን በባሪያችን ላይ ባወረድነው የምታምኑ እንደኾናችሁ (ይህንን ዕወቁ)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

Verse 42

إِذْ أَنتُم بِٱلْعُدْوَةِ ٱلدُّنْيَا وَهُم بِٱلْعُدْوَةِ ٱلْقُصْوَىٰ وَٱلرَّكْبُ أَسْفَلَ مِنكُمْ ۚ وَلَوْ تَوَاعَدتُّمْ لَٱخْتَلَفْتُمْ فِى ٱلْمِيعَـٰدِ ۙ وَلَـٰكِن لِّيَقْضِىَ ٱللَّهُ أَمْرًا كَانَ مَفْعُولًا لِّيَهْلِكَ مَنْ هَلَكَ عَنۢ بَيِّنَةٍ وَيَحْيَىٰ مَنْ حَىَّ عَنۢ بَيِّنَةٍ ۗ وَإِنَّ ٱللَّهَ لَسَمِيعٌ عَلِيمٌ

Transliteration idh antum bil-ʿud'wati l-dun'yā wahum bil-ʿud'wati l-quṣ'wā wal-rakbu asfala minkum walaw tawāʿadttum la-ikh'talaftum fī l-mīʿādi walākin liyaqḍiya l-lahu amran kāna mafʿūlan liyahlika man halaka ʿan bayyinatin wayaḥyā man ḥayya ʿan bayyinatin wa-inna l-laha lasamīʿun ʿalīmun

Amharic እናንተ በቅርቢቱ ዳርቻ ኾናችሁ እነርሱም በሩቂቱ ዳርቻ ኾነው የነጋዴዎቹም ጭፍራ ከናንተ በታች ሲኾኑ በሰፈራችሁ ጊዜ (ያደረግንላችሁን አስታውሱ)፡፡ በተቃጠራችሁም ኖሮ በቀጠሮው በተለያያችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ ሊሠራው የሚገባውን ነገር ሊፈጽም የሚጠፋ ሰው ከአስረጅ በኋላ እንዲጠፋ ሕያው የሚኾንም ሰው ከአስረጅ በኋላ ሕያው እንዲኾን (ያለቀጠሮ አጋጠማችሁ)፡፡ አላህም በእርግጥ ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

Verse 43

إِذْ يُرِيكَهُمُ ٱللَّهُ فِى مَنَامِكَ قَلِيلًا ۖ وَلَوْ أَرَىٰكَهُمْ كَثِيرًا لَّفَشِلْتُمْ وَلَتَنَـٰزَعْتُمْ فِى ٱلْأَمْرِ وَلَـٰكِنَّ ٱللَّهَ سَلَّمَ ۗ إِنَّهُۥ عَلِيمٌۢ بِذَاتِ ٱلصُّدُورِ

Transliteration idh yurīkahumu l-lahu fī manāmika qalīlan walaw arākahum kathīran lafashil'tum walatanāzaʿtum fī l-amri walākinna l-laha sallama innahu ʿalīmun bidhāti l-ṣudūri

Amharic አላህ በሕልምህ እነሱን ጥቂት አድርጎ ባሳየህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ እነሱን ብዙ አድርጎ ባሳየህም ኖሮ በፈራችሁና በነገሩ በተጨቃጨቃችሁ ነበር፡፡ ግን አላህ አዳናችሁ፡፡ እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለን ሁሉ ዐዋቂ ነውና፡፡

Verse 44

وَإِذْ يُرِيكُمُوهُمْ إِذِ ٱلْتَقَيْتُمْ فِىٓ أَعْيُنِكُمْ قَلِيلًا وَيُقَلِّلُكُمْ فِىٓ أَعْيُنِهِمْ لِيَقْضِىَ ٱللَّهُ أَمْرًا كَانَ مَفْعُولًا ۗ وَإِلَى ٱللَّهِ تُرْجَعُ ٱلْأُمُورُ

Transliteration wa-idh yurīkumūhum idhi l-taqaytum fī aʿyunikum qalīlan wayuqallilukum fī aʿyunihim liyaqḍiya l-lahu amran kāna mafʿūlan wa-ilā l-lahi tur'jaʿu l-umūru

Amharic አላህም ሊሠራው የሚገባን ነገር ይፈጽም ዘንድ በተጋጠማችሁ ጊዜ እነርሱን በዓይኖቻችሁ ጥቂት አድርጎ ያሳያችሁንና በዓይኖቻቸውም ላይ ያሳነሳችሁን (አስታውሱ)፡፡ ነገሮቹም ሁሉ ወደ አላህ ብቻ ይመለሳሉ፡፡

Verse 45

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِذَا لَقِيتُمْ فِئَةً فَٱثْبُتُوا۟ وَٱذْكُرُوا۟ ٱللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

Transliteration yāayyuhā alladhīna āmanū idhā laqītum fi-atan fa-uth'butū wa-udh'kurū l-laha kathīran laʿallakum tuf'liḥūna

Amharic እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሰራዊትን በገጠማችሁ ጊዜ እርጉ፤ (መክቱ)፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፤ በእርግጥ ትድናላችሁና፡፡

Verse 46

وَأَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَلَا تَنَـٰزَعُوا۟ فَتَفْشَلُوا۟ وَتَذْهَبَ رِيحُكُمْ ۖ وَٱصْبِرُوٓا۟ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِينَ

Transliteration wa-aṭīʿū l-laha warasūlahu walā tanāzaʿū fatafshalū watadhhaba rīḥukum wa-iṣ'birū inna l-laha maʿa l-ṣābirīna

Amharic አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አትጨቃጨቁም፡፡ ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና፡፡ ታገሱም፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡

Verse 47

وَلَا تَكُونُوا۟ كَٱلَّذِينَ خَرَجُوا۟ مِن دِيَـٰرِهِم بَطَرًا وَرِئَآءَ ٱلنَّاسِ وَيَصُدُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ ۚ وَٱللَّهُ بِمَا يَعْمَلُونَ مُحِيطٌ

Transliteration walā takūnū ka-alladhīna kharajū min diyārihim baṭaran wariāa l-nāsi wayaṣuddūna ʿan sabīli l-lahi wal-lahu bimā yaʿmalūna muḥīṭun

Amharic እንደነዚያ ለትዕቢትና ለሰዎች ይዩልኝ ሲሉ ከአላህም መንገድ ለማገድ ከአገራቸው እንደወጡት አትኹኑ፡፡ አላህም በሚሠሩት ሁሉ (በዕውቀቱ) ከባቢ ነው፡፡

Verse 48

وَإِذْ زَيَّنَ لَهُمُ ٱلشَّيْطَـٰنُ أَعْمَـٰلَهُمْ وَقَالَ لَا غَالِبَ لَكُمُ ٱلْيَوْمَ مِنَ ٱلنَّاسِ وَإِنِّى جَارٌ لَّكُمْ ۖ فَلَمَّا تَرَآءَتِ ٱلْفِئَتَانِ نَكَصَ عَلَىٰ عَقِبَيْهِ وَقَالَ إِنِّى بَرِىٓءٌ مِّنكُمْ إِنِّىٓ أَرَىٰ مَا لَا تَرَوْنَ إِنِّىٓ أَخَافُ ٱللَّهَ ۚ وَٱللَّهُ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Transliteration wa-idh zayyana lahumu l-shayṭānu aʿmālahum waqāla lā ghāliba lakumu l-yawma mina l-nāsi wa-innī jārun lakum falammā tarāati l-fi-atāni nakaṣa ʿalā ʿaqibayhi waqāla innī barīon minkum innī arā mā lā tarawna innī akhāfu l-laha wal-lahu shadīdu l-ʿiqābi

Amharic ሰይጣንም ሥራዎቻቸውን ለእነርሱ ባሳመረላቸውና «ዛሬ ለእናንተ ከሰዎች አሸናፊ የላችሁም እኔም ለእናንተ ረዳት ነኝ» ባለ ጊዜም (አስታውስ)፡፡ ሁለቱ ጭፍሮችም በተያዩ ጊዜ፤ ወደኋላው አፈገፈገ፡፡ «እኔ ከናንተ ንጹህ ነኝ፡፡ እኔ እናንተ የማታዩትን አያለሁ፡፡ እኔ አላህን እፈራለሁ፡፡ አላህም ቅጣተ ብርቱ ነው» አላቸውም፡፡

Verse 49

إِذْ يَقُولُ ٱلْمُنَـٰفِقُونَ وَٱلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌ غَرَّ هَـٰٓؤُلَآءِ دِينُهُمْ ۗ وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ فَإِنَّ ٱللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Transliteration idh yaqūlu l-munāfiqūna wa-alladhīna fī qulūbihim maraḍun gharra hāulāi dīnuhum waman yatawakkal ʿalā l-lahi fa-inna l-laha ʿazīzun ḥakīmun

Amharic መናፍቃንና እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ያለባቸው «እነዚህን (ሙስሊሞች) ሃይማኖታቸው አታለላቸው» ባሉ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በአላህም ላይ የሚጠጋ (ያሸንፋል)፤ አላህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡

Verse 50

وَلَوْ تَرَىٰٓ إِذْ يَتَوَفَّى ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ۙ ٱلْمَلَـٰٓئِكَةُ يَضْرِبُونَ وُجُوهَهُمْ وَأَدْبَـٰرَهُمْ وَذُوقُوا۟ عَذَابَ ٱلْحَرِيقِ

Transliteration walaw tarā idh yatawaffā alladhīna kafarū l-malāikatu yaḍribūna wujūhahum wa-adbārahum wadhūqū ʿadhāba l-ḥarīqi

Amharic እነዚያንም የካዱትን መላእክት ፊቶቻቸውንና ጀርባዎቻቸውን እየመቱ «የቃጠሎንም ስቃይ ቅመሱ» (እያሉ) በሚገድሏቸው ጊዜ ብታይ ኖሮ (አስደንጋጭን ነገር ታይ ነበር)፡፡

Verse 51

ذَٰلِكَ بِمَا قَدَّمَتْ أَيْدِيكُمْ وَأَنَّ ٱللَّهَ لَيْسَ بِظَلَّـٰمٍ لِّلْعَبِيدِ

Transliteration dhālika bimā qaddamat aydīkum wa-anna l-laha laysa biẓallāmin lil'ʿabīdi

Amharic ይህ እጆቻችሁ ባስቀደሙት ምክንያት አላህም ለባሮቹ በዳይ ባለመኾኑ ነው (ይባላሉ)፡፡

Verse 52

كَدَأْبِ ءَالِ فِرْعَوْنَ ۙ وَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَـٰتِ ٱللَّهِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ قَوِىٌّ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

Transliteration kadabi āli fir'ʿawna wa-alladhīna min qablihim kafarū biāyāti l-lahi fa-akhadhahumu l-lahu bidhunūbihim inna l-laha qawiyyun shadīdu l-ʿiqābi

Amharic (የነዚያ ልማድ) እንደ ፈርዖን ቤተሰብና እንደነዚያም ከእነሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ ነው፡፡ በአላህ አንቀጾች ካዱ፤ አላህም በኃጢኣቶቻቸው ያዛቸው፤ አላህ ኀይለኛ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡

Verse 53

ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ لَمْ يَكُ مُغَيِّرًا نِّعْمَةً أَنْعَمَهَا عَلَىٰ قَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمْ ۙ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

Transliteration dhālika bi-anna l-laha lam yaku mughayyiran niʿ'matan anʿamahā ʿalā qawmin ḥattā yughayyirū mā bi-anfusihim wa-anna l-laha samīʿun ʿalīmun

Amharic ይህ (ቅጣት) አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመኾኑ ምክንያት ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡

Verse 54

كَدَأْبِ ءَالِ فِرْعَوْنَ ۙ وَٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَـٰتِ رَبِّهِمْ فَأَهْلَكْنَـٰهُم بِذُنُوبِهِمْ وَأَغْرَقْنَآ ءَالَ فِرْعَوْنَ ۚ وَكُلٌّ كَانُوا۟ ظَـٰلِمِينَ

Transliteration kadabi āli fir'ʿawna wa-alladhīna min qablihim kadhabū biāyāti rabbihim fa-ahlaknāhum bidhunūbihim wa-aghraqnā āla fir'ʿawna wakullun kānū ẓālimīna

Amharic እንደ ፈርዖን ቤተሰቦችና እንደእነዚያም ከእነሱ በፊት እንደ ነበሩት ልማድ (እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥባቸውም)፡፡ በጌታቸው ተአምራት አስተባበሉና በኃጢኣቶቻቸው አጠፋናቸው፡፡ የፈርዖንንም ቤተሰቦች አሰጠምናቸው፡፡ ሁሉም በዳዮች ነበሩም፡፡

Verse 55

إِنَّ شَرَّ ٱلدَّوَآبِّ عِندَ ٱللَّهِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَهُمْ لَا يُؤْمِنُونَ

Transliteration inna sharra l-dawābi ʿinda l-lahi alladhīna kafarū fahum lā yu'minūna

Amharic ከሚንቀሳቀሱ እንስሳዎች ሁሉ አላህ ዘንድ ይበልጥ ክፉዎቹ እነዚያ ዘወትር የካዱት ናቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ አያምኑም፡፡

Verse 56

ٱلَّذِينَ عَـٰهَدتَّ مِنْهُمْ ثُمَّ يَنقُضُونَ عَهْدَهُمْ فِى كُلِّ مَرَّةٍ وَهُمْ لَا يَتَّقُونَ

Transliteration alladhīna ʿāhadtta min'hum thumma yanquḍūna ʿahdahum fī kulli marratin wahum lā yattaqūna

Amharic እነዚያ ከነሱ ቃል ኪዳን የያዝክባቸው ከዚያም በየጊዜው ቃል ኪዳናቸውን የሚያፈርሱ ናቸው፡፡ እነሱም አይጠነቀቁም፡፡

Verse 57

فَإِمَّا تَثْقَفَنَّهُمْ فِى ٱلْحَرْبِ فَشَرِّدْ بِهِم مَّنْ خَلْفَهُمْ لَعَلَّهُمْ يَذَّكَّرُونَ

Transliteration fa-immā tathqafannahum fī l-ḥarbi fasharrid bihim man khalfahum laʿallahum yadhakkarūna

Amharic በጦርም ላይ ብታገኛቸው በእነርሱ ቅጣት ምክንያት (ሌሎቹ ከሓዲዎች) ይገሰጹ ዘንድ ከኋላቸው ያሉትን በትንባቸው፡፡

Verse 58

وَإِمَّا تَخَافَنَّ مِن قَوْمٍ خِيَانَةً فَٱنۢبِذْ إِلَيْهِمْ عَلَىٰ سَوَآءٍ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُحِبُّ ٱلْخَآئِنِينَ

Transliteration wa-immā takhāfanna min qawmin khiyānatan fa-inbidh ilayhim ʿalā sawāin inna l-laha lā yuḥibbu l-khāinīna

Amharic ከሕዝቦችም ክዳትን ብትፈራ (የኪዳኑን መፍረስ በማወቅ) በመተካከል ላይ ኾናችሁ ኪዳናቸውን ወደነሱ ጣልላቸው፡፡ አላህ ከዳተኞችን አይወድምና፡፡

Verse 59

وَلَا يَحْسَبَنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ سَبَقُوٓا۟ ۚ إِنَّهُمْ لَا يُعْجِزُونَ

Transliteration walā yaḥsabanna alladhīna kafarū sabaqū innahum lā yuʿ'jizūna

Amharic እነዚያም የካዱት ከአላህ ቅጣት ያመለጡ መኾናቸውን አያስቡ፡፡ እነሱ አያቅቱምና፡፡

Verse 60

وَأَعِدُّوا۟ لَهُم مَّا ٱسْتَطَعْتُم مِّن قُوَّةٍ وَمِن رِّبَاطِ ٱلْخَيْلِ تُرْهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمْ وَءَاخَرِينَ مِن دُونِهِمْ لَا تَعْلَمُونَهُمُ ٱللَّهُ يَعْلَمُهُمْ ۚ وَمَا تُنفِقُوا۟ مِن شَىْءٍ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ

Transliteration wa-aʿiddū lahum mā is'taṭaʿtum min quwwatin wamin ribāṭi l-khayli tur'hibūna bihi ʿaduwwa l-lahi waʿaduwwakum waākharīna min dūnihim lā taʿlamūnahumu l-lahu yaʿlamuhum wamā tunfiqū min shayin fī sabīli l-lahi yuwaffa ilaykum wa-antum lā tuẓ'lamūna

Amharic ለእነሱም ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን ሌሎችንም ከእነርሱ በቀር ያሉትን የማታውቋቸውን አላህ የሚያውቃቸውን (መናፍቃን) የምታሸብሩበት ስትኾኑ አዘጋጁላቸው፡፡ ከማንኛውም ነገር በአላህ መንገድ የምትለግሱትም ምንዳው ወደናንተ በሙሉ ይሰጣል፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡

Verse 61

۞ وَإِن جَنَحُوا۟ لِلسَّلْمِ فَٱجْنَحْ لَهَا وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ

Transliteration wa-in janaḥū lilssalmi fa-ij'naḥ lahā watawakkal ʿalā l-lahi innahu huwa l-samīʿu l-ʿalīmu

Amharic ወደ ዕርቅም ቢያዘነብሉ ወደ እርሷ አዘንብል፡፡ በአላህም ላይ ተጠጋ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚ ዐዋቂ ነውና፡፡

Verse 62

وَإِن يُرِيدُوٓا۟ أَن يَخْدَعُوكَ فَإِنَّ حَسْبَكَ ٱللَّهُ ۚ هُوَ ٱلَّذِىٓ أَيَّدَكَ بِنَصْرِهِۦ وَبِٱلْمُؤْمِنِينَ

Transliteration wa-in yurīdū an yakhdaʿūka fa-inna ḥasbaka l-lahu huwa alladhī ayyadaka binaṣrihi wabil-mu'minīna

Amharic ሊያታልሉህም ቢፈልጉ አላህ በቂህ ነው፡፡ እርሱ ያ በእርዳታውና በምእምናን ያበረታህ ነው፡፡

Verse 63

وَأَلَّفَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ ۚ لَوْ أَنفَقْتَ مَا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا مَّآ أَلَّفْتَ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ وَلَـٰكِنَّ ٱللَّهَ أَلَّفَ بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّهُۥ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Transliteration wa-allafa bayna qulūbihim law anfaqta mā fī l-arḍi jamīʿan mā allafta bayna qulūbihim walākinna l-laha allafa baynahum innahu ʿazīzun ḥakīmun

Amharic በልቦቻቸውም መካከል ያስማማ ነው፡፡ በምድር ያለውን ሁሉ (ሀብት) በለገስክ ኖሮ በልቦቻቸው መካከል ባላስማማህ ነበር፡፡ ግን አላህ በመካከላቸው አስማማ፡፡ እርሱ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና፡፡

Verse 64

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ حَسْبُكَ ٱللَّهُ وَمَنِ ٱتَّبَعَكَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ

Transliteration yāayyuhā l-nabiyu ḥasbuka l-lahu wamani ittabaʿaka mina l-mu'minīna

Amharic አንተ ነቢዩ ሆይ! አላህ በቂህ ነው፡፡ ለተከተሉህም ምእምናን (አላህ በቂያቸው ነው)፡፡

Verse 65

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ حَرِّضِ ٱلْمُؤْمِنِينَ عَلَى ٱلْقِتَالِ ۚ إِن يَكُن مِّنكُمْ عِشْرُونَ صَـٰبِرُونَ يَغْلِبُوا۟ مِا۟ئَتَيْنِ ۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّا۟ئَةٌ يَغْلِبُوٓا۟ أَلْفًا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِأَنَّهُمْ قَوْمٌ لَّا يَفْقَهُونَ

Transliteration yāayyuhā l-nabiyu ḥarriḍi l-mu'minīna ʿalā l-qitāli in yakun minkum ʿish'rūna ṣābirūna yaghlibū mi-atayni wa-in yakun minkum mi-atun yaghlibū alfan mina alladhīna kafarū bi-annahum qawmun lā yafqahūna

Amharic አንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናንን በመዋጋት ላይ አደፋፍራቸው፡፡ ከእናንተ ውስጥ ሃያ ታጋሾች ኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ፡፡ ከእናንተም መቶ ቢኖሩ ከእነዚያ ከካዱት እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች ስለኾኑ ሺህን ያሸንፋሉ፤

Verse 66

ٱلْـَٔـٰنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمْ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمْ ضَعْفًا ۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّا۟ئَةٌ صَابِرَةٌ يَغْلِبُوا۟ مِا۟ئَتَيْنِ ۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمْ أَلْفٌ يَغْلِبُوٓا۟ أَلْفَيْنِ بِإِذْنِ ٱللَّهِ ۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِينَ

Transliteration al-āna khaffafa l-lahu ʿankum waʿalima anna fīkum ḍaʿfan fa-in yakun minkum mi-atun ṣābiratun yaghlibū mi-atayni wa-in yakun minkum alfun yaghlibū alfayni bi-idh'ni l-lahi wal-lahu maʿa l-ṣābirīna

Amharic አሁን አላህ ከእናንተ ላይ አቀለለላችሁ፡፡ በእናንተ ውስጥም ድክመት መኖሩን ዐወቀ፡፡ ስለዚህ ከእናንተ መቶ ታጋሾች ቢኖሩ ሁለት መቶን ያሸንፋሉ፡፡ ከእናንተም ሺህ ቢኖሩ በአላህ ፈቃድ ሁለት ሺህን ያሸንፋሉ፡፡ አላህም ከታጋሾቹ ጋር ነው፡፡

Verse 67

مَا كَانَ لِنَبِىٍّ أَن يَكُونَ لَهُۥٓ أَسْرَىٰ حَتَّىٰ يُثْخِنَ فِى ٱلْأَرْضِ ۚ تُرِيدُونَ عَرَضَ ٱلدُّنْيَا وَٱللَّهُ يُرِيدُ ٱلْـَٔاخِرَةَ ۗ وَٱللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

Transliteration mā kāna linabiyyin an yakūna lahu asrā ḥattā yuth'khina fī l-arḍi turīdūna ʿaraḍa l-dun'yā wal-lahu yurīdu l-ākhirata wal-lahu ʿazīzun ḥakīmun

Amharic ለነቢይ በምድር ላይ እስቲያደክም ድረስ ለእርሱ ምርኮኞች ሊኖሩት አይገባም፡፡ የቅርቢቱን ዓለም ጠፊ ጥቅም ትፈልጋላችሁ፡፡ አላህም መጨረሻይቱን ይሻል፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡

Verse 68

لَّوْلَا كِتَـٰبٌ مِّنَ ٱللَّهِ سَبَقَ لَمَسَّكُمْ فِيمَآ أَخَذْتُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Transliteration lawlā kitābun mina l-lahi sabaqa lamassakum fīmā akhadhtum ʿadhābun ʿaẓīmun

Amharic ከአላህ ያለፈ ፍርድ ባልነበረ ኖሮ በወሰዳችሁት (ቤዛ) ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር፡፡

Verse 69

فَكُلُوا۟ مِمَّا غَنِمْتُمْ حَلَـٰلًا طَيِّبًا ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Transliteration fakulū mimmā ghanim'tum ḥalālan ṭayyiban wa-ittaqū l-laha inna l-laha ghafūrun raḥīmun

Amharic (ከጠላት) ከዘረፋችሁትም (ሀብት) የተፈቀደ መልካም ሲኾን ብሉ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

Verse 70

يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِىُّ قُل لِّمَن فِىٓ أَيْدِيكُم مِّنَ ٱلْأَسْرَىٰٓ إِن يَعْلَمِ ٱللَّهُ فِى قُلُوبِكُمْ خَيْرًا يُؤْتِكُمْ خَيْرًا مِّمَّآ أُخِذَ مِنكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ۗ وَٱللَّهُ غَفُورٌ رَّحِيمٌ

Transliteration yāayyuhā l-nabiyu qul liman fī aydīkum mina l-asrā in yaʿlami l-lahu fī qulūbikum khayran yu'tikum khayran mimmā ukhidha minkum wayaghfir lakum wal-lahu ghafūrun raḥīmun

Amharic አንተ ነቢዩ ሆይ! ከምርኮኞች በእጆቻችሁ ላሉት በላቸው፡- «አላህ በልቦቻችሁ ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከእናንተ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል፡፡ ለእናንተም ይምራችኋል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡»

Verse 71

وَإِن يُرِيدُوا۟ خِيَانَتَكَ فَقَدْ خَانُوا۟ ٱللَّهَ مِن قَبْلُ فَأَمْكَنَ مِنْهُمْ ۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ

Transliteration wa-in yurīdū khiyānataka faqad khānū l-laha min qablu fa-amkana min'hum wal-lahu ʿalīmun ḥakīmun

Amharic ሊከዱህም ቢፈልጉ ከዚህ በፊት አላህን በእርግጥ ከድተዋል፡፡ ከነሱም አስመችቶሃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

Verse 72

إِنَّ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَهَاجَرُوا۟ وَجَـٰهَدُوا۟ بِأَمْوَٰلِهِمْ وَأَنفُسِهِمْ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَوا۟ وَّنَصَرُوٓا۟ أُو۟لَـٰٓئِكَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ ۚ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَلَمْ يُهَاجِرُوا۟ مَا لَكُم مِّن وَلَـٰيَتِهِم مِّن شَىْءٍ حَتَّىٰ يُهَاجِرُوا۟ ۚ وَإِنِ ٱسْتَنصَرُوكُمْ فِى ٱلدِّينِ فَعَلَيْكُمُ ٱلنَّصْرُ إِلَّا عَلَىٰ قَوْمٍۭ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُم مِّيثَـٰقٌ ۗ وَٱللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ بَصِيرٌ

Transliteration inna alladhīna āmanū wahājarū wajāhadū bi-amwālihim wa-anfusihim fī sabīli l-lahi wa-alladhīna āwaw wanaṣarū ulāika baʿḍuhum awliyāu baʿḍin wa-alladhīna āmanū walam yuhājirū mā lakum min walāyatihim min shayin ḥattā yuhājirū wa-ini is'tanṣarūkum fī l-dīni faʿalaykumu l-naṣru illā ʿalā qawmin baynakum wabaynahum mīthāqun wal-lahu bimā taʿmalūna baṣīrun

Amharic እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም (ስደተኞቹን) ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ እነዚያም ያመኑና ያልተሰደዱ እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ምንም ዝምድና የላችሁም፡፡ በሃይማኖትም እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በነሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ሕዝቦች ላይ ካልኾነ በስተቀር በናንተ ላይ መርዳት አለባችሁ፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

Verse 73

وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ ۚ إِلَّا تَفْعَلُوهُ تَكُن فِتْنَةٌ فِى ٱلْأَرْضِ وَفَسَادٌ كَبِيرٌ

Transliteration wa-alladhīna kafarū baʿḍuhum awliyāu baʿḍin illā tafʿalūhu takun fit'natun fī l-arḍi wafasādun kabīrun

Amharic እነዚያም የካዱት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ (ከምእምናን መረዳዳትን ከከሓዲያን መቆራረጥን) ባትሠሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይኾናል፡፡

Verse 74

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَهَاجَرُوا۟ وَجَـٰهَدُوا۟ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ وَٱلَّذِينَ ءَاوَوا۟ وَّنَصَرُوٓا۟ أُو۟لَـٰٓئِكَ هُمُ ٱلْمُؤْمِنُونَ حَقًّا ۚ لَّهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ

Transliteration wa-alladhīna āmanū wahājarū wajāhadū fī sabīli l-lahi wa-alladhīna āwaw wanaṣarū ulāika humu l-mu'minūna ḥaqqan lahum maghfiratun wariz'qun karīmun

Amharic እነዚያም ያመኑና የተሰደዱ በአላህም መንገድ ላይ የታገሉ፣ እነዚያም ያስጠጉና የረዱ እነዚያ እነሱ በእውነት አማኞች ናቸው፡፡ ለእነሱም ምሕረትና የከበረ ሲሳይ አላቸው፡፡

Verse 75

وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنۢ بَعْدُ وَهَاجَرُوا۟ وَجَـٰهَدُوا۟ مَعَكُمْ فَأُو۟لَـٰٓئِكَ مِنكُمْ ۚ وَأُو۟لُوا۟ ٱلْأَرْحَامِ بَعْضُهُمْ أَوْلَىٰ بِبَعْضٍ فِى كِتَـٰبِ ٱللَّهِ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ بِكُلِّ شَىْءٍ عَلِيمٌۢ

Transliteration wa-alladhīna āmanū min baʿdu wahājarū wajāhadū maʿakum fa-ulāika minkum wa-ulū l-arḥāmi baʿḍuhum awlā bibaʿḍin fī kitābi l-lahi inna l-laha bikulli shayin ʿalīmun

Amharic እነዚያም በኋላ ያመኑና የተሰደዱ፣ ከእናንተም ጋር ኾነው የታገሉ እነዚያ ከናንተው ናቸው፡፡ የዝምድናዎች ባለቤቶችም በአላህ መጽሐፍ ከፊሎቻቸው በከፊሉ (መውረስ) የተገቡ ናቸው፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

Read Surah Al-Anfal in another language

All languages

All 114 surahs in Amharic: the Qur’an in Amharic.

Learn it in MyDugsi

Amharic translation: Sadiq and Sani, from Quran.com. Transliteration: Quran.com. Recitation: Mishary Alafasy, from EveryAyah.com. MyDugsi is a learning aid, not a replacement for a qualified teacher.