Surah Ghafir in Amharic: translation and audio
Surah 40 · غافر · The Forgiver · 85 verses
Surah Ghafir verse by verse: the Arabic with a recitation you can repeat, the transliteration, and the Amharic translation by Sadiq and Sani. For the meaning of every word, see Surah Ghafir word by word in English.
Verse 1
حمٓ
Transliteration hha-meem
Amharic ሐ.መ (ሓ.ሚም)፤
Verse 2
تَنزِيلُ ٱلْكِتَـٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْعَلِيمِ
Transliteration tanzīlu l-kitābi mina l-lahi l-ʿazīzi l-ʿalīmi
Amharic የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ዐዋቂ ከሆነው አላህ ነው፡፡
Verse 3
غَافِرِ ٱلذَّنۢبِ وَقَابِلِ ٱلتَّوْبِ شَدِيدِ ٱلْعِقَابِ ذِى ٱلطَّوْلِ ۖ لَآ إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ إِلَيْهِ ٱلْمَصِيرُ
Transliteration ghāfiri l-dhanbi waqābili l-tawbi shadīdi l-ʿiqābi dhī l-ṭawli lā ilāha illā huwa ilayhi l-maṣīru
Amharic ኀጢአትን መሓሪ፣ ጸጸትንም ተቀባይ፣ ቅጣተ ብርቱ፣ የልግስና ባለቤት ከኾነው (አላህ የወረደ ነው)፡፡ ከእርሱ በቀር አምላክ የለም፡፡ መመለሻው ወደርሱ ብቻ ነው፡፡
Verse 4
مَا يُجَـٰدِلُ فِىٓ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ إِلَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فَلَا يَغْرُرْكَ تَقَلُّبُهُمْ فِى ٱلْبِلَـٰدِ
Transliteration mā yujādilu fī āyāti l-lahi illā alladhīna kafarū falā yaghrur'ka taqallubuhum fī l-bilādi
Amharic በአላህ አንቀጾች እነዚያ የካዱት ቢኾኑ እንጅ ማንም (በመዝለፍ) አይከራከርም፡፡ በያገሮችም ውስጥ መዘዋወራቸው አይሸንግልህ፡፡
Verse 5
كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَٱلْأَحْزَابُ مِنۢ بَعْدِهِمْ ۖ وَهَمَّتْ كُلُّ أُمَّةٍۭ بِرَسُولِهِمْ لِيَأْخُذُوهُ ۖ وَجَـٰدَلُوا۟ بِٱلْبَـٰطِلِ لِيُدْحِضُوا۟ بِهِ ٱلْحَقَّ فَأَخَذْتُهُمْ ۖ فَكَيْفَ كَانَ عِقَابِ
Transliteration kadhabat qablahum qawmu nūḥin wal-aḥzābu min baʿdihim wahammat kullu ummatin birasūlihim liyakhudhūhu wajādalū bil-bāṭili liyud'ḥiḍū bihi l-ḥaqa fa-akhadhtuhum fakayfa kāna ʿiqābi
Amharic ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች ከኋላቸውም አሕዛቦቹ አስተባባሉ፡፡ ሕዝቦችም ሁሉ መልክተኛቸውን ሊይዙ አሰቡ፡፡ በውሸትም በእርሱ እውነትን ሊያጠፉበት ተከራከሩ፡፡ ያዝኳቸውም፡፡ ታዲያ ቅጣቴ እንዴት ነበር?
Verse 6
وَكَذَٰلِكَ حَقَّتْ كَلِمَتُ رَبِّكَ عَلَى ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَنَّهُمْ أَصْحَـٰبُ ٱلنَّارِ
Transliteration wakadhālika ḥaqqat kalimatu rabbika ʿalā alladhīna kafarū annahum aṣḥābu l-nāri
Amharic እንደዚሁም የጌታህ ቃል በእነዚያ በካዱት ላይ እነርሱ የእሳት ጓዶች ናቸው ማለት ተረጋገጠች፡፡
Verse 7
ٱلَّذِينَ يَحْمِلُونَ ٱلْعَرْشَ وَمَنْ حَوْلَهُۥ يُسَبِّحُونَ بِحَمْدِ رَبِّهِمْ وَيُؤْمِنُونَ بِهِۦ وَيَسْتَغْفِرُونَ لِلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ رَبَّنَا وَسِعْتَ كُلَّ شَىْءٍ رَّحْمَةً وَعِلْمًا فَٱغْفِرْ لِلَّذِينَ تَابُوا۟ وَٱتَّبَعُوا۟ سَبِيلَكَ وَقِهِمْ عَذَابَ ٱلْجَحِيمِ
Transliteration alladhīna yaḥmilūna l-ʿarsha waman ḥawlahu yusabbiḥūna biḥamdi rabbihim wayu'minūna bihi wayastaghfirūna lilladhīna āmanū rabbanā wasiʿ'ta kulla shayin raḥmatan waʿil'man fa-igh'fir lilladhīna tābū wa-ittabaʿū sabīlaka waqihim ʿadhāba l-jaḥīmi
Amharic እነዚያ ዐርሹን የሚሸከሙት እነዚያም በዙሪያው ያሉት በጌታቸው ምስጋና ያወድሳሉ፡፡ በእርሱም ያምናሉ፡፡ «ጌታችን ሆይ! ነገሩን ሁሉ በእዝነትና በዕውቀት ከበሃል፡፡ ስለዚህ ለእነዚያ ለተጸጸቱት መንገድህንም ለተከተሉት ምሕረት አድርግላቸው፡፡ የእሳትንም ቅጣት ጠብቃቸው፡፡» እያሉ ለእነዚያ ላመኑት ምሕረትን ይለምናሉ፡፡
Verse 8
رَبَّنَا وَأَدْخِلْهُمْ جَنَّـٰتِ عَدْنٍ ٱلَّتِى وَعَدتَّهُمْ وَمَن صَلَحَ مِنْ ءَابَآئِهِمْ وَأَزْوَٰجِهِمْ وَذُرِّيَّـٰتِهِمْ ۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ
Transliteration rabbanā wa-adkhil'hum jannāti ʿadnin allatī waʿadttahum waman ṣalaḥa min ābāihim wa-azwājihim wadhurriyyātihim innaka anta l-ʿazīzu l-ḥakīmu
Amharic «ጌታችን ሆይ! እነርሱንም፣ ከአባቶቻቸውና ከሚስቶቻቸውም፣ ከዝርዮቻቸውም፣ የበጀውን ሁሉ እነዚያን ቃል የገባህላቸውን የመኖሪያ ገነቶች አግባቸው፡፡ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ነህና፡፡
Verse 9
وَقِهِمُ ٱلسَّيِّـَٔاتِ ۚ وَمَن تَقِ ٱلسَّيِّـَٔاتِ يَوْمَئِذٍ فَقَدْ رَحِمْتَهُۥ ۚ وَذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْعَظِيمُ
Transliteration waqihimu l-sayiāti waman taqi l-sayiāti yawma-idhin faqad raḥim'tahu wadhālika huwa l-fawzu l-ʿaẓīmu
Amharic «ከቅጣቶችም ጠብቃቸው፡፡ በዚያ ቀንም የምትጠብቃውን ሰው በእርግጥ አዘንክለት፡፡» ይህም እርሱ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
Verse 10
إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يُنَادَوْنَ لَمَقْتُ ٱللَّهِ أَكْبَرُ مِن مَّقْتِكُمْ أَنفُسَكُمْ إِذْ تُدْعَوْنَ إِلَى ٱلْإِيمَـٰنِ فَتَكْفُرُونَ
Transliteration inna alladhīna kafarū yunādawna lamaqtu l-lahi akbaru min maqtikum anfusakum idh tud'ʿawna ilā l-īmāni fatakfurūna
Amharic እነዚያ የካዱት ሰዎች «ወደ እምነት በምትጠሩና በምትክዱ ጊዜ አላህ (እናንተን) መጥላቱ ነፍሶቻችሁን (ዛሬ) ከመጥላታችሁ የበለጠ ነው» በማለት ይጥጠራሉ፡፡
Verse 11
قَالُوا۟ رَبَّنَآ أَمَتَّنَا ٱثْنَتَيْنِ وَأَحْيَيْتَنَا ٱثْنَتَيْنِ فَٱعْتَرَفْنَا بِذُنُوبِنَا فَهَلْ إِلَىٰ خُرُوجٍ مِّن سَبِيلٍ
Transliteration qālū rabbanā amattanā ith'natayni wa-aḥyaytanā ith'natayni fa-iʿ'tarafnā bidhunūbinā fahal ilā khurūjin min sabīlin
Amharic «ጌታችን ሆይ! ሁለትን ሞት አሞትከን፡፡ ሁለትንም ሕይወት ሕያው አደረግከን፡፡ በኃጢኣቶቻችንም መሰከርን፡፡ ታዲያ (ከእሳት) ወደ መውጣት መንገድ አለን?» ይላሉ፡፡
Verse 12
ذَٰلِكُم بِأَنَّهُۥٓ إِذَا دُعِىَ ٱللَّهُ وَحْدَهُۥ كَفَرْتُمْ ۖ وَإِن يُشْرَكْ بِهِۦ تُؤْمِنُوا۟ ۚ فَٱلْحُكْمُ لِلَّهِ ٱلْعَلِىِّ ٱلْكَبِيرِ
Transliteration dhālikum bi-annahu idhā duʿiya l-lahu waḥdahu kafartum wa-in yush'rak bihi tu'minū fal-ḥuk'mu lillahi l-ʿaliyi l-kabīri
Amharic «ይህ እነሆ አላህ ብቻውን በተጠራ ጊዜ ስለ ካዳችሁ በእርሱም ተጋሪ ቢደረግ የምታምኑ ስለ ኾናችሁ ነው፡፡ ስለዚህ ፍርዱ ከፍተኛ ታላቅ ለኾነው አላህ ብቻ ነው፡፡»
Verse 13
هُوَ ٱلَّذِى يُرِيكُمْ ءَايَـٰتِهِۦ وَيُنَزِّلُ لَكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ رِزْقًا ۚ وَمَا يَتَذَكَّرُ إِلَّا مَن يُنِيبُ
Transliteration huwa alladhī yurīkum āyātihi wayunazzilu lakum mina l-samāi riz'qan wamā yatadhakkaru illā man yunību
Amharic እርሱ ያ (ለአምላክነቱ) ምልክቶቹን የሚያሳያችሁ ለእናንተም ከሰማይ ሲሳይን የሚያወርድላችሁ ነው፡፡ ወደእርሱም የሚመለስ ሰው ቢኾን እንጂ ሌላው አይገሰጽም፡፡
Verse 14
فَٱدْعُوا۟ ٱللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَـٰفِرُونَ
Transliteration fa-id'ʿū l-laha mukh'liṣīna lahu l-dīna walaw kariha l-kāfirūna
Amharic አላህንም ከሓዲዎች ቢጠሉም ሃይማኖትን ለእርሱ አጥሪዎች ኾናችሁ ተገዙት፡፡
Verse 15
رَفِيعُ ٱلدَّرَجَـٰتِ ذُو ٱلْعَرْشِ يُلْقِى ٱلرُّوحَ مِنْ أَمْرِهِۦ عَلَىٰ مَن يَشَآءُ مِنْ عِبَادِهِۦ لِيُنذِرَ يَوْمَ ٱلتَّلَاقِ
Transliteration rafīʿu l-darajāti dhū l-ʿarshi yul'qī l-rūḥa min amrihi ʿalā man yashāu min ʿibādihi liyundhira yawma l-talāqi
Amharic (እርሱ) ደረጃዎችን ከፍ አድራጊ የዐርሹ ባለቤት ነው፡፡ የመገናኛውን ቀን ያስፈራራ ዘንድ ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ ከትዕዛዙ መንፈስን (ራእይን) ያወርዳል፡፡
Verse 16
يَوْمَ هُم بَـٰرِزُونَ ۖ لَا يَخْفَىٰ عَلَى ٱللَّهِ مِنْهُمْ شَىْءٌ ۚ لِّمَنِ ٱلْمُلْكُ ٱلْيَوْمَ ۖ لِلَّهِ ٱلْوَٰحِدِ ٱلْقَهَّارِ
Transliteration yawma hum bārizūna lā yakhfā ʿalā l-lahi min'hum shayon limani l-mul'ku l-yawma lillahi l-wāḥidi l-qahāri
Amharic እነርሱ (ከመቃብር) በሚወጡበት ቀን በአላህ ላይ ከእነርሱ ምንም ነገር አይደበቅም፡፡ «ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው?» (ይባላል፤)፡፡ «ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው» (ይባላል)፡፡
Verse 17
ٱلْيَوْمَ تُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ ۚ لَا ظُلْمَ ٱلْيَوْمَ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَرِيعُ ٱلْحِسَابِ
Transliteration al-yawma tuj'zā kullu nafsin bimā kasabat lā ẓul'ma l-yawma inna l-laha sarīʿu l-ḥisābi
Amharic «ዛሬ ነፍስ ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳለች፡፡ ዛሬ በደል የለም፡፡ አላህ በእርግጥ ምርመራው ፈጣን ነው» (ይባላል)፡፡
Verse 18
وَأَنذِرْهُمْ يَوْمَ ٱلْـَٔازِفَةِ إِذِ ٱلْقُلُوبُ لَدَى ٱلْحَنَاجِرِ كَـٰظِمِينَ ۚ مَا لِلظَّـٰلِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلَا شَفِيعٍ يُطَاعُ
Transliteration wa-andhir'hum yawma l-āzifati idhi l-qulūbu ladā l-ḥanājiri kāẓimīna mā lilẓẓālimīna min ḥamīmin walā shafīʿin yuṭāʿu
Amharic ቅርቢቱንም (የትንሣኤን) ቀን ልቦች ጭንቀትን የተመሉ ኾነው ላንቃዎች ዘንድ የሚደርሱበትን ጊዜ አስጠንቅቃቸው፡፡ ለበዳዮች ምንም ወዳጅና ተሰሚ አማላጅ የላቸውም፡፡
Verse 19
يَعْلَمُ خَآئِنَةَ ٱلْأَعْيُنِ وَمَا تُخْفِى ٱلصُّدُورُ
Transliteration yaʿlamu khāinata l-aʿyuni wamā tukh'fī l-ṣudūru
Amharic (አላህ) የዓይኖችን ክዳት ልቦችም የሚደብቁትን ሁሉ ያውቃል፡፡
Verse 20
وَٱللَّهُ يَقْضِى بِٱلْحَقِّ ۖ وَٱلَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَقْضُونَ بِشَىْءٍ ۗ إِنَّ ٱللَّهَ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
Transliteration wal-lahu yaqḍī bil-ḥaqi wa-alladhīna yadʿūna min dūnihi lā yaqḍūna bishayin inna l-laha huwa l-samīʿu l-baṣīru
Amharic አላህም በእውነት ይፈርዳል፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የሚግገዟቸው በምንም አይፈርዱም፡፡ አላህ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡
Verse 21
۞ أَوَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَـٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ كَانُوا۟ مِن قَبْلِهِمْ ۚ كَانُوا۟ هُمْ أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَءَاثَارًا فِى ٱلْأَرْضِ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ بِذُنُوبِهِمْ وَمَا كَانَ لَهُم مِّنَ ٱللَّهِ مِن وَاقٍ
Transliteration awalam yasīrū fī l-arḍi fayanẓurū kayfa kāna ʿāqibatu alladhīna kānū min qablihim kānū hum ashadda min'hum quwwatan waāthāran fī l-arḍi fa-akhadhahumu l-lahu bidhunūbihim wamā kāna lahum mina l-lahi min wāqin
Amharic የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶች፤ ከእነርሱ ይበልጥ የበረቱ ነበሩ፡፡ አላህም በኀጢአቶቻቸው ያዛቸው፡፡ ለእነርሱም ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ አልነበራቸውም፡፡
Verse 22
ذَٰلِكَ بِأَنَّهُمْ كَانَت تَّأْتِيهِمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَـٰتِ فَكَفَرُوا۟ فَأَخَذَهُمُ ٱللَّهُ ۚ إِنَّهُۥ قَوِىٌّ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
Transliteration dhālika bi-annahum kānat tatīhim rusuluhum bil-bayināti fakafarū fa-akhadhahumu l-lahu innahu qawiyyun shadīdu l-ʿiqābi
Amharic ይህ (መያዝ) እነርሱ መልክተኞቻቸው በተዓምራቶች ይመጡባቸው ስለነበሩና ስለ ካዱ ነው፡፡ አላህም ያዛቸው፡፡ እርሱ ኀያል ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
Verse 23
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا مُوسَىٰ بِـَٔايَـٰتِنَا وَسُلْطَـٰنٍ مُّبِينٍ
Transliteration walaqad arsalnā mūsā biāyātinā wasul'ṭānin mubīnin
Amharic ሙሳንም በተዓምራቶቻችንና በግልጽ ማስረጃ በእርግጥ ላክነው፡፡
Verse 24
إِلَىٰ فِرْعَوْنَ وَهَـٰمَـٰنَ وَقَـٰرُونَ فَقَالُوا۟ سَـٰحِرٌ كَذَّابٌ
Transliteration ilā fir'ʿawna wahāmāna waqārūna faqālū sāḥirun kadhābun
Amharic ወደ ፈርዖንና ወደ ሃማን፤ ወደ ቃሩንም (ላክነው)፡፡ «ድግምተኛ ውሸታም ነው» አሉም፡፡
Verse 25
فَلَمَّا جَآءَهُم بِٱلْحَقِّ مِنْ عِندِنَا قَالُوا۟ ٱقْتُلُوٓا۟ أَبْنَآءَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مَعَهُۥ وَٱسْتَحْيُوا۟ نِسَآءَهُمْ ۚ وَمَا كَيْدُ ٱلْكَـٰفِرِينَ إِلَّا فِى ضَلَـٰلٍ
Transliteration falammā jāahum bil-ḥaqi min ʿindinā qālū uq'tulū abnāa alladhīna āmanū maʿahu wa-is'taḥyū nisāahum wamā kaydu l-kāfirīna illā fī ḍalālin
Amharic ከእኛ ዘንድ እውነትን ይዞ በመጣላቸውም ጊዜ «የእነዚያን ከእርሱ ጋር ያመኑትን ሰዎች ወንዶች ልጆች ግደሉ፤ ሴቶቻቸውንም አስቀሩ» አሉ፡፡ የከሓዲዎችም ተንኮል በጥፋት ውስጥ እንጅ አይደለም፡፡
Verse 26
وَقَالَ فِرْعَوْنُ ذَرُونِىٓ أَقْتُلْ مُوسَىٰ وَلْيَدْعُ رَبَّهُۥٓ ۖ إِنِّىٓ أَخَافُ أَن يُبَدِّلَ دِينَكُمْ أَوْ أَن يُظْهِرَ فِى ٱلْأَرْضِ ٱلْفَسَادَ
Transliteration waqāla fir'ʿawnu dharūnī aqtul mūsā walyadʿu rabbahu innī akhāfu an yubaddila dīnakum aw an yuẓ'hira fī l-arḍi l-fasāda
Amharic ፈርዖንም «ተዉኝ፤ ሙሳን ልግደል፡፡ ጌታውንም ይጥራ፡፡ ያድነው እንደኾነ፡፡ እኔ ሃይማኖታችሁን ሊለውጥ፤ ወይም በምድር ውስጥ ጥፋትን ሊያሰራጭ እፈራለሁና» አለ፡፡
Verse 27
وَقَالَ مُوسَىٰٓ إِنِّى عُذْتُ بِرَبِّى وَرَبِّكُم مِّن كُلِّ مُتَكَبِّرٍ لَّا يُؤْمِنُ بِيَوْمِ ٱلْحِسَابِ
Transliteration waqāla mūsā innī ʿudh'tu birabbī warabbikum min kulli mutakabbirin lā yu'minu biyawmi l-ḥisābi
Amharic ሙሳም «እኔ በምርመራው ቀን ከማያምን ትዕቢተኛ ሁሉ በጌታዬና በጌታችሁ ተጠበቅሁ» አለ፡፡
Verse 28
وَقَالَ رَجُلٌ مُّؤْمِنٌ مِّنْ ءَالِ فِرْعَوْنَ يَكْتُمُ إِيمَـٰنَهُۥٓ أَتَقْتُلُونَ رَجُلًا أَن يَقُولَ رَبِّىَ ٱللَّهُ وَقَدْ جَآءَكُم بِٱلْبَيِّنَـٰتِ مِن رَّبِّكُمْ ۖ وَإِن يَكُ كَـٰذِبًا فَعَلَيْهِ كَذِبُهُۥ ۖ وَإِن يَكُ صَادِقًا يُصِبْكُم بَعْضُ ٱلَّذِى يَعِدُكُمْ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَهْدِى مَنْ هُوَ مُسْرِفٌ كَذَّابٌ
Transliteration waqāla rajulun mu'minun min āli fir'ʿawna yaktumu īmānahu ataqtulūna rajulan an yaqūla rabbiya l-lahu waqad jāakum bil-bayināti min rabbikum wa-in yaku kādhiban faʿalayhi kadhibuhu wa-in yaku ṣādiqan yuṣib'kum baʿḍu alladhī yaʿidukum inna l-laha lā yahdī man huwa mus'rifun kadhābun
Amharic ከፈርዖንም ቤተሰቦች አንድ እምነቱን የሚደብቅ ምእመን ሰው አለ፡- «ሰውየውን ከጌታችሁ በተዓምራቶች በእርግጥ የመጣለችሁ ሲኾን ‹ጌታዬ አላህ ነው› ስለሚል ትገድላላችሁን? ውሸታምም ቢኾን ውሸቱ በርሱው ላይ ነው፡፡ እውነተኛ ቢኾን ግን የዚያ የሚያሰፈራራችሁ ከፊሉ ያገኛችኋል፡፡ አላህ ያንን እርሱ ድንበር አላፊ ውሸታም የኾነውን አይመራምና፡፡
Verse 29
يَـٰقَوْمِ لَكُمُ ٱلْمُلْكُ ٱلْيَوْمَ ظَـٰهِرِينَ فِى ٱلْأَرْضِ فَمَن يَنصُرُنَا مِنۢ بَأْسِ ٱللَّهِ إِن جَآءَنَا ۚ قَالَ فِرْعَوْنُ مَآ أُرِيكُمْ إِلَّا مَآ أَرَىٰ وَمَآ أَهْدِيكُمْ إِلَّا سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ
Transliteration yāqawmi lakumu l-mul'ku l-yawma ẓāhirīna fī l-arḍi faman yanṣurunā min basi l-lahi in jāanā qāla fir'ʿawnu mā urīkum illā mā arā wamā ahdīkum illā sabīla l-rashādi
Amharic «ወገኖቼ ሆይ! በምድር ላይ አሸናፊዎች ስትኾኑ ዛሬ መንግስቱ የእናንተ ነው፡፡ ታዲያ ከአላህ ቅጣት ቢመጣብን የሚያድነን ማን ነው?» (አለ)፡፡ ፈርዖን «የማየውን ነገር እንጅ፤ አላመለክታችሁም፡፡ ቅኑንም መንገድ እንጅ አልመራችሁም» አላቸው፡፡
Verse 30
وَقَالَ ٱلَّذِىٓ ءَامَنَ يَـٰقَوْمِ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُم مِّثْلَ يَوْمِ ٱلْأَحْزَابِ
Transliteration waqāla alladhī āmana yāqawmi innī akhāfu ʿalaykum mith'la yawmi l-aḥzābi
Amharic ያም ያመነው ሰው አለ «እኔ በናንተ ላይ የአሕዛቦቹን ቀን ብጤ እፈራላችኋለሁ፡፡
Verse 31
مِثْلَ دَأْبِ قَوْمِ نُوحٍ وَعَادٍ وَثَمُودَ وَٱلَّذِينَ مِنۢ بَعْدِهِمْ ۚ وَمَا ٱللَّهُ يُرِيدُ ظُلْمًا لِّلْعِبَادِ
Transliteration mith'la dabi qawmi nūḥin waʿādin wathamūda wa-alladhīna min baʿdihim wamā l-lahu yurīdu ẓul'man lil'ʿibādi
Amharic «የኑሕን ሕዝቦች፣ የዓድንና የሰሙድንም፣ የእነዚያንም ከኋላቸው የነበሩትን ልማድ ብጤ (እፈራላችኋለሁ)፡፡ አላህም ለባሮቹ መበደልን የሚሻ አይደለም፡፡
Verse 32
وَيَـٰقَوْمِ إِنِّىٓ أَخَافُ عَلَيْكُمْ يَوْمَ ٱلتَّنَادِ
Transliteration wayāqawmi innī akhāfu ʿalaykum yawma l-tanādi
Amharic «ወገኖቼ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ የመጠራሪያን ቀን እፈራለሁ፡፡»
Verse 33
يَوْمَ تُوَلُّونَ مُدْبِرِينَ مَا لَكُم مِّنَ ٱللَّهِ مِنْ عَاصِمٍ ۗ وَمَن يُضْلِلِ ٱللَّهُ فَمَا لَهُۥ مِنْ هَادٍ
Transliteration yawma tuwallūna mud'birīna mā lakum mina l-lahi min ʿāṣimin waman yuḍ'lili l-lahu famā lahu min hādin
Amharic ወደ ኋላ ዞራችሁ በምትሸሹበት ቀን፤ ለናንተ ከአላህ (ቅጣት) ምንም ጠባቂ የላችሁም፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
Verse 34
وَلَقَدْ جَآءَكُمْ يُوسُفُ مِن قَبْلُ بِٱلْبَيِّنَـٰتِ فَمَا زِلْتُمْ فِى شَكٍّ مِّمَّا جَآءَكُم بِهِۦ ۖ حَتَّىٰٓ إِذَا هَلَكَ قُلْتُمْ لَن يَبْعَثَ ٱللَّهُ مِنۢ بَعْدِهِۦ رَسُولًا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ مَنْ هُوَ مُسْرِفٌ مُّرْتَابٌ
Transliteration walaqad jāakum yūsufu min qablu bil-bayināti famā zil'tum fī shakkin mimmā jāakum bihi ḥattā idhā halaka qul'tum lan yabʿatha l-lahu min baʿdihi rasūlan kadhālika yuḍillu l-lahu man huwa mus'rifun mur'tābun
Amharic ዩሱፍም ከዚህ በፊት ግልጽ ማስረጃዎችን በእርግጥ አመጣላቸሁ፡፡ ከዚያም እርሱ ካመጣላችሁ ነገር ከመጠራጠር አልተወገዳችሁም፡፡ በጠፋም ጊዜ «አላህ ከእርሱ ኋላ መልክተኛን በጭራሽ አይልክም» አላችሁ፡፡ አላህ እንደዚሁ ድንበር አላፊ ተጠራጣሪ የኾነን ሰው ያሳስታል፡፡
Verse 35
ٱلَّذِينَ يُجَـٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَـٰنٍ أَتَىٰهُمْ ۖ كَبُرَ مَقْتًا عِندَ ٱللَّهِ وَعِندَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ۚ كَذَٰلِكَ يَطْبَعُ ٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ قَلْبِ مُتَكَبِّرٍ جَبَّارٍ
Transliteration alladhīna yujādilūna fī āyāti l-lahi bighayri sul'ṭānin atāhum kabura maqtan ʿinda l-lahi waʿinda alladhīna āmanū kadhālika yaṭbaʿu l-lahu ʿalā kulli qalbi mutakabbirin jabbārin
Amharic እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ ተዓምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ በጣም ተለቀ፡፡ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል፡፡
Verse 36
وَقَالَ فِرْعَوْنُ يَـٰهَـٰمَـٰنُ ٱبْنِ لِى صَرْحًا لَّعَلِّىٓ أَبْلُغُ ٱلْأَسْبَـٰبَ
Transliteration waqāla fir'ʿawnu yāhāmānu ib'ni lī ṣarḥan laʿallī ablughu l-asbāba
Amharic ፈርዖንም አለ «ሃማን ሆይ! መንገዶችን እደርስ ዘንድ ረዢም ሕንጻን ለእኔ ካብልኝ፡፡
Verse 37
أَسْبَـٰبَ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ فَأَطَّلِعَ إِلَىٰٓ إِلَـٰهِ مُوسَىٰ وَإِنِّى لَأَظُنُّهُۥ كَـٰذِبًا ۚ وَكَذَٰلِكَ زُيِّنَ لِفِرْعَوْنَ سُوٓءُ عَمَلِهِۦ وَصُدَّ عَنِ ٱلسَّبِيلِ ۚ وَمَا كَيْدُ فِرْعَوْنَ إِلَّا فِى تَبَابٍ
Transliteration asbāba l-samāwāti fa-aṭṭaliʿa ilā ilāhi mūsā wa-innī la-aẓunnuhu kādhiban wakadhālika zuyyina lifir'ʿawna sūu ʿamalihi waṣudda ʿani l-sabīli wamā kaydu fir'ʿawna illā fī tabābin
Amharic «የሰማያትን መንገዶች (እደርስ ዘንድ)፣ ወደ ሙሳም አምላክ እመለከት ዘንድ፡፡ እኔም ውሸታም ነው ብዬ በእርግጥ እጠረጥረዋለሁ» (አለ)፡፡ እንደዚሁም ለፈርዖን መጥፎ ሥራው ተሸለመለት፡፡ ከቅን መንገድም ታገደ፡፡ የፈርዖንም ተንኮል በከሳራ ውስጥ እንጅ አይደለም፡፡
Verse 38
وَقَالَ ٱلَّذِىٓ ءَامَنَ يَـٰقَوْمِ ٱتَّبِعُونِ أَهْدِكُمْ سَبِيلَ ٱلرَّشَادِ
Transliteration waqāla alladhī āmana yāqawmi ittabiʿūni ahdikum sabīla l-rashādi
Amharic ያም ያመነው አለ «ወገኖቼ ሆይ! ተከተሉኝ፡፡ ቀጥታውን መንገድ እመራችኋለሁና፡፡
Verse 39
يَـٰقَوْمِ إِنَّمَا هَـٰذِهِ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا مَتَـٰعٌ وَإِنَّ ٱلْـَٔاخِرَةَ هِىَ دَارُ ٱلْقَرَارِ
Transliteration yāqawmi innamā hādhihi l-ḥayatu l-dun'yā matāʿun wa-inna l-ākhirata hiya dāru l-qarāri
Amharic «ወገኖቼ ሆይ! ይህቺ ቅርቢቱ ሕይወት (ጥቂት) መጣቀሚያ ብቻ ናት፡፡ መጨረሻይቱም ዓለም እርሷ መርጊያ አገር ናት፡፡»
Verse 40
مَنْ عَمِلَ سَيِّئَةً فَلَا يُجْزَىٰٓ إِلَّا مِثْلَهَا ۖ وَمَنْ عَمِلَ صَـٰلِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُو۟لَـٰٓئِكَ يَدْخُلُونَ ٱلْجَنَّةَ يُرْزَقُونَ فِيهَا بِغَيْرِ حِسَابٍ
Transliteration man ʿamila sayyi-atan falā yuj'zā illā mith'lahā waman ʿamila ṣāliḥan min dhakarin aw unthā wahuwa mu'minun fa-ulāika yadkhulūna l-janata yur'zaqūna fīhā bighayri ḥisābin
Amharic «መጥፎን የሠራ ሰው ብጤዋን እንጅ አይምመነዳም፡፡ እርሱ ምእመን ኾኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፡፡ በእርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ፡፡
Verse 41
۞ وَيَـٰقَوْمِ مَا لِىٓ أَدْعُوكُمْ إِلَى ٱلنَّجَوٰةِ وَتَدْعُونَنِىٓ إِلَى ٱلنَّارِ
Transliteration wayāqawmi mā lī adʿūkum ilā l-najati watadʿūnanī ilā l-nāri
Amharic «ወገኖቼም ሆይ! ወደ መዳን የምጠራችሁ ስኾን ወደ እሳትም የምትጠሩኝ ስትኾኑ ለኔ ምን አለኝ!
Verse 42
تَدْعُونَنِى لِأَكْفُرَ بِٱللَّهِ وَأُشْرِكَ بِهِۦ مَا لَيْسَ لِى بِهِۦ عِلْمٌ وَأَنَا۠ أَدْعُوكُمْ إِلَى ٱلْعَزِيزِ ٱلْغَفَّـٰرِ
Transliteration tadʿūnanī li-akfura bil-lahi wa-ush'rika bihi mā laysa lī bihi ʿil'mun wa-anā adʿūkum ilā l-ʿazīzi l-ghafāri
Amharic «በአላህ ልክድና በእርሱም ለእኔ ዕውቀት የሌለኝን ነገር በእርሱ እንዳጋራ ትጠሩኛላችሁ፡፡ እኔም ወደ አሸናፊው፤ መሓሪው (አላህ) እጠራችኋለሁ፡፡
Verse 43
لَا جَرَمَ أَنَّمَا تَدْعُونَنِىٓ إِلَيْهِ لَيْسَ لَهُۥ دَعْوَةٌ فِى ٱلدُّنْيَا وَلَا فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ وَأَنَّ مَرَدَّنَآ إِلَى ٱللَّهِ وَأَنَّ ٱلْمُسْرِفِينَ هُمْ أَصْحَـٰبُ ٱلنَّارِ
Transliteration lā jarama annamā tadʿūnanī ilayhi laysa lahu daʿwatun fī l-dun'yā walā fī l-ākhirati wa-anna maraddanā ilā l-lahi wa-anna l-mus'rifīna hum aṣḥābu l-nāri
Amharic «በእርግጥ ወደእርሱ የምትጠሩብኝ (ጣዖት) ለእርሱ በቅርቢቱም ኾነ በመጨረሻይቱ ዓለም (ተሰሚ) ጥሪ የለውም፡፡ መመለሻችንም በእርግጥ ወደ አላህ ነው፡፡ ወሰን አላፊዎቹም እነሱ የእሳት ጓዶች ናቸው፡፡
Verse 44
فَسَتَذْكُرُونَ مَآ أَقُولُ لَكُمْ ۚ وَأُفَوِّضُ أَمْرِىٓ إِلَى ٱللَّهِ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ بَصِيرٌۢ بِٱلْعِبَادِ
Transliteration fasatadhkurūna mā aqūlu lakum wa-ufawwiḍu amrī ilā l-lahi inna l-laha baṣīrun bil-ʿibādi
Amharic «ወደ ፊትም ለእናንተ የምላችሁን ምክር (ቅጣትን በምታዩ ጊዜ) ታስታውሳላችሁ፡፡ ነገሬንም ሁሉ ወደ አላህ አስጠጋለሁ፡፡ አላህ ባሮቹን ተመልካች ነውና፡፡»
Verse 45
فَوَقَىٰهُ ٱللَّهُ سَيِّـَٔاتِ مَا مَكَرُوا۟ ۖ وَحَاقَ بِـَٔالِ فِرْعَوْنَ سُوٓءُ ٱلْعَذَابِ
Transliteration fawaqāhu l-lahu sayyiāti mā makarū waḥāqa biāli fir'ʿawna sūu l-ʿadhābi
Amharic ከመከሩዋቸውም መጥፎዎች አላህ ጠበቀው፡፡ በፈርዖን ቤተሰቦችም ላይ ክፉ ቅጣት ሰፈረባቸው፡፡
Verse 46
ٱلنَّارُ يُعْرَضُونَ عَلَيْهَا غُدُوًّا وَعَشِيًّا ۖ وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ أَدْخِلُوٓا۟ ءَالَ فِرْعَوْنَ أَشَدَّ ٱلْعَذَابِ
Transliteration al-nāru yuʿ'raḍūna ʿalayhā ghuduwwan waʿashiyyan wayawma taqūmu l-sāʿatu adkhilū āla fir'ʿawna ashadda l-ʿadhābi
Amharic እሳት በጧትና በማታ በእርሷ ላይ ይቀርባሉ፡፡ ሰዓቲቱም በምትኾንበት ቀን «የፈርዖንን ቤተሰቦች ብርቱን ቅጣት (ገሀነምን) አግቡዋቸው» (ይባላል)፡፡
Verse 47
وَإِذْ يَتَحَآجُّونَ فِى ٱلنَّارِ فَيَقُولُ ٱلضُّعَفَـٰٓؤُا۟ لِلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا كُنَّا لَكُمْ تَبَعًا فَهَلْ أَنتُم مُّغْنُونَ عَنَّا نَصِيبًا مِّنَ ٱلنَّارِ
Transliteration wa-idh yataḥājjūna fī l-nāri fayaqūlu l-ḍuʿafāu lilladhīna is'takbarū innā kunnā lakum tabaʿan fahal antum mugh'nūna ʿannā naṣīban mina l-nāri
Amharic በእሳትም ውስጥ የሚከራከሩበትን ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ደካማዎቹም ለእነዚያ ለኮሩት «እኛ ለእናንተ ተከታዮች ነበርንና እናንተ (አሁን) ከእሳት ከፊሉን ከእኛ ላይ ገፍታሪዎች ናችሁን?» ይላሉ፡፡
Verse 48
قَالَ ٱلَّذِينَ ٱسْتَكْبَرُوٓا۟ إِنَّا كُلٌّ فِيهَآ إِنَّ ٱللَّهَ قَدْ حَكَمَ بَيْنَ ٱلْعِبَادِ
Transliteration qāla alladhīna is'takbarū innā kullun fīhā inna l-laha qad ḥakama bayna l-ʿibādi
Amharic እነዚያም የኮሩት «እኛ ሁላችንም በውስጧ ነን፡፡ አላህ በባሮቹ መካከል በእርግጥ ፈረደ» ይላሉ፡፡
Verse 49
وَقَالَ ٱلَّذِينَ فِى ٱلنَّارِ لِخَزَنَةِ جَهَنَّمَ ٱدْعُوا۟ رَبَّكُمْ يُخَفِّفْ عَنَّا يَوْمًا مِّنَ ٱلْعَذَابِ
Transliteration waqāla alladhīna fī l-nāri likhazanati jahannama id'ʿū rabbakum yukhaffif ʿannā yawman mina l-ʿadhābi
Amharic እነዚያም በእሳት ውሰጥ ያሉት ለገሀነም ዘበኞች «ጌታችሁን ለምኑልን፤ ከእኛ ላይ ከቅጣቱ አንድን ቀን ያቃልልን» ይላሉ፡፡
Verse 50
قَالُوٓا۟ أَوَلَمْ تَكُ تَأْتِيكُمْ رُسُلُكُم بِٱلْبَيِّنَـٰتِ ۖ قَالُوا۟ بَلَىٰ ۚ قَالُوا۟ فَٱدْعُوا۟ ۗ وَمَا دُعَـٰٓؤُا۟ ٱلْكَـٰفِرِينَ إِلَّا فِى ضَلَـٰلٍ
Transliteration qālū awalam taku tatīkum rusulukum bil-bayināti qālū balā qālū fa-id'ʿū wamā duʿāu l-kāfirīna illā fī ḍalālin
Amharic (ዘበኞቹም) «መልእክተኞቻችሁ በተዓምራቶች ይመጡላችሁ አልነበሩምን?» ይላሉ፡፡ (ከሓዲዎቹም) «እንዴታ መጥተውናል እንጅ፤ (ግን አስተባበልናቸው)» ይላሉ፡፡
Verse 51
إِنَّا لَنَنصُرُ رُسُلَنَا وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ فِى ٱلْحَيَوٰةِ ٱلدُّنْيَا وَيَوْمَ يَقُومُ ٱلْأَشْهَـٰدُ
Transliteration innā lananṣuru rusulanā wa-alladhīna āmanū fī l-ḥayati l-dun'yā wayawma yaqūmu l-ashhādu
Amharic እኛ መልክተኞቻችንን፣ እነዚያንም ያመኑትን በቅርቢቱ ሕይወት ምስክሮችም በሚቆሙበት ቀን በእርግጥ እንረዳለን፡፡
Verse 52
يَوْمَ لَا يَنفَعُ ٱلظَّـٰلِمِينَ مَعْذِرَتُهُمْ ۖ وَلَهُمُ ٱللَّعْنَةُ وَلَهُمْ سُوٓءُ ٱلدَّارِ
Transliteration yawma lā yanfaʿu l-ẓālimīna maʿdhiratuhum walahumu l-laʿnatu walahum sūu l-dāri
Amharic በደለኞችን ምክንያታቸው በማይጠቅማቸው ቀን (እንረዳለን)፡፡ ለእነርሱም ርግማን አልላቸው፡፡ ለእነርሱም መጥፎ አገር አልላቸው፡፡
Verse 53
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَى ٱلْهُدَىٰ وَأَوْرَثْنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْكِتَـٰبَ
Transliteration walaqad ātaynā mūsā l-hudā wa-awrathnā banī is'rāīla l-kitāba
Amharic ሙሳንም መምሪያን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ የእስራኤልንም ልጆች መጽሐፉን አወረስናቸው፡፡
Verse 54
هُدًى وَذِكْرَىٰ لِأُو۟لِى ٱلْأَلْبَـٰبِ
Transliteration hudan wadhik'rā li-ulī l-albābi
Amharic ለባለ አእምሮዎች መሪና ገሳጭ ሲኾን፡፡
Verse 55
فَٱصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَٱسْتَغْفِرْ لِذَنۢبِكَ وَسَبِّحْ بِحَمْدِ رَبِّكَ بِٱلْعَشِىِّ وَٱلْإِبْكَـٰرِ
Transliteration fa-iṣ'bir inna waʿda l-lahi ḥaqqun wa-is'taghfir lidhanbika wasabbiḥ biḥamdi rabbika bil-ʿashiyi wal-ib'kāri
Amharic (ሙሐመድ ሆይ!) ታገስም የአላህ ተስፋ እውነት ነውና፡፡ ለስህተትህም ምሕረትን ለምን፡፡ ከቀትር በኋላም በማለዳም ጌታሀን ከማመስገን ጋር አጥራው፡፡
Verse 56
إِنَّ ٱلَّذِينَ يُجَـٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَـٰنٍ أَتَىٰهُمْ ۙ إِن فِى صُدُورِهِمْ إِلَّا كِبْرٌ مَّا هُم بِبَـٰلِغِيهِ ۚ فَٱسْتَعِذْ بِٱللَّهِ ۖ إِنَّهُۥ هُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْبَصِيرُ
Transliteration inna alladhīna yujādilūna fī āyāti l-lahi bighayri sul'ṭānin atāhum in fī ṣudūrihim illā kib'run mā hum bibālighīhi fa-is'taʿidh bil-lahi innahu huwa l-samīʿu l-baṣīru
Amharic እነዚያ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር በአላህ አንቀጾች የሚከራከሩ በልቦቻቸው ውስጥ እነርሱ ደራሾቹ ያልኾኑት ኩራት ብቻ እንጅ ምንም የለም፡፡ በአላህም ተጠበቅ፡፡ እነሆ እርሱ ሰሚው ተመልካቹ ነውና፡፡
Verse 57
لَخَلْقُ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ أَكْبَرُ مِنْ خَلْقِ ٱلنَّاسِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ
Transliteration lakhalqu l-samāwāti wal-arḍi akbaru min khalqi l-nāsi walākinna akthara l-nāsi lā yaʿlamūna
Amharic ሰማያትንና ምድርን መፍጠር ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
Verse 58
وَمَا يَسْتَوِى ٱلْأَعْمَىٰ وَٱلْبَصِيرُ وَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَلَا ٱلْمُسِىٓءُ ۚ قَلِيلًا مَّا تَتَذَكَّرُونَ
Transliteration wamā yastawī l-aʿmā wal-baṣīru wa-alladhīna āmanū waʿamilū l-ṣāliḥāti walā l-musīu qalīlan mā tatadhakkarūna
Amharic ዕውርና የሚያይ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሠሩና መጥፎ ሠሪው አይስተካከሉም፡፡ በጣም ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡
Verse 59
إِنَّ ٱلسَّاعَةَ لَـَٔاتِيَةٌ لَّا رَيْبَ فِيهَا وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ
Transliteration inna l-sāʿata laātiyatun lā rayba fīhā walākinna akthara l-nāsi lā yu'minūna
Amharic ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡
Verse 60
وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ
Transliteration waqāla rabbukumu id'ʿūnī astajib lakum inna alladhīna yastakbirūna ʿan ʿibādatī sayadkhulūna jahannama dākhirīna
Amharic ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡
Verse 61
ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلَّيْلَ لِتَسْكُنُوا۟ فِيهِ وَٱلنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ ٱللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى ٱلنَّاسِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ
Transliteration al-lahu alladhī jaʿala lakumu al-layla litaskunū fīhi wal-nahāra mub'ṣiran inna l-laha ladhū faḍlin ʿalā l-nāsi walākinna akthara l-nāsi lā yashkurūna
Amharic አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ) ቀንንም (ልትሠሩበት) የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው፡፡ አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡
Verse 62
ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ خَـٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍ لَّآ إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ
Transliteration dhālikumu l-lahu rabbukum khāliqu kulli shayin lā ilāha illā huwa fa-annā tu'fakūna
Amharic ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡
Verse 63
كَذَٰلِكَ يُؤْفَكُ ٱلَّذِينَ كَانُوا۟ بِـَٔايَـٰتِ ٱللَّهِ يَجْحَدُونَ
Transliteration kadhālika yu'faku alladhīna kānū biāyāti l-lahi yajḥadūna
Amharic እንደዚሁ እነዚያ በአላህ አንቀጾች ይክዱ የነበሩት (ከእምነት) ይመለሳሉ፡፡
Verse 64
ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَرْضَ قَرَارًا وَٱلسَّمَآءَ بِنَآءً وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ وَرَزَقَكُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَـٰتِ ۚ ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ فَتَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَـٰلَمِينَ
Transliteration al-lahu alladhī jaʿala lakumu l-arḍa qarāran wal-samāa bināan waṣawwarakum fa-aḥsana ṣuwarakum warazaqakum mina l-ṭayibāti dhālikumu l-lahu rabbukum fatabāraka l-lahu rabbu l-ʿālamīna
Amharic አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፡፡ የቀረጻችኁም ቅርጻችሁንም ያሳመረ ከጣፋጮችም ሲሳዮች የሰጣችሁ ነው፡፡ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ፡፡
Verse 65
هُوَ ٱلْحَىُّ لَآ إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَٱدْعُوهُ مُخْلِصِينَ لَهُ ٱلدِّينَ ۗ ٱلْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَـٰلَمِينَ
Transliteration huwa l-ḥayu lā ilāha illā huwa fa-id'ʿūhu mukh'liṣīna lahu l-dīna l-ḥamdu lillahi rabbi l-ʿālamīna
Amharic እርሱ ብቻ (ሁል ጊዜ) ሕያው ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ሃይማኖትንም ለእርሱ ያጠራችሁ ስትኾኑ «ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይኹን» የምትሉ ኾናችሁ ተገዙት፡፡
Verse 66
۞ قُلْ إِنِّى نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَمَّا جَآءَنِىَ ٱلْبَيِّنَـٰتُ مِن رَّبِّى وَأُمِرْتُ أَنْ أُسْلِمَ لِرَبِّ ٱلْعَـٰلَمِينَ
Transliteration qul innī nuhītu an aʿbuda alladhīna tadʿūna min dūni l-lahi lammā jāaniya l-bayinātu min rabbī wa-umir'tu an us'lima lirabbi l-ʿālamīna
Amharic «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ እነዚያን ከአላህ ሌላ የምትገዙዋቸውን እንዳልገዛ ተከልክያለሁ፡፡ ለዓለማት ጌታም እንድገዛ ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡
Verse 67
هُوَ ٱلَّذِى خَلَقَكُم مِّن تُرَابٍ ثُمَّ مِن نُّطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ يُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوٓا۟ أَشُدَّكُمْ ثُمَّ لِتَكُونُوا۟ شُيُوخًا ۚ وَمِنكُم مَّن يُتَوَفَّىٰ مِن قَبْلُ ۖ وَلِتَبْلُغُوٓا۟ أَجَلًا مُّسَمًّى وَلَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ
Transliteration huwa alladhī khalaqakum min turābin thumma min nuṭ'fatin thumma min ʿalaqatin thumma yukh'rijukum ṭif'lan thumma litablughū ashuddakum thumma litakūnū shuyūkhan waminkum man yutawaffā min qablu walitablughū ajalan musamman walaʿallakum taʿqilūna
Amharic እርሱ ያ ከዐፈር ከዚያም ከፍትወት ጠብታ ከዚያም ከረጋ ደም የፈጠራችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሕጻናት አድርጎ ያወጣችኋል፡፡ ከዚያም ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፤ ከዚያም ሽማግሌዎች ትኾኑ ዘንድ (ያቆያችኋል)፡፡ ከእናንተም ውስጥ ከዚህ በፊት የሚሞት አልለ፡፡ (ይህንንም ያደረገው ልትኖሩና) የተወሰነ ጊዜንም ልትደርሱ ታውቁም ዘንድ ነው፡፡
Verse 68
هُوَ ٱلَّذِى يُحْىِۦ وَيُمِيتُ ۖ فَإِذَا قَضَىٰٓ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُۥ كُن فَيَكُونُ
Transliteration huwa alladhī yuḥ'yī wayumītu fa-idhā qaḍā amran fa-innamā yaqūlu lahu kun fayakūnu
Amharic እርሱ ያ ሕያው የሚያደርግ የሚገድልም ነው፡፡ አንዳችን ነገር በሻም ጊዜ ለእርሱ የሚለውን «ኹን» ነው፤ ወዲያውም ይኾናል፡፡
Verse 69
أَلَمْ تَرَ إِلَى ٱلَّذِينَ يُجَـٰدِلُونَ فِىٓ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ أَنَّىٰ يُصْرَفُونَ
Transliteration alam tara ilā alladhīna yujādilūna fī āyāti l-lahi annā yuṣ'rafūna
Amharic ወደእነዚያ በአላህ አንቀጾች ወደሚከራከሩት (ከእምነት) እንዴት እንደሚመለሱ አታይምን?
Verse 70
ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِٱلْكِتَـٰبِ وَبِمَآ أَرْسَلْنَا بِهِۦ رُسُلَنَا ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ
Transliteration alladhīna kadhabū bil-kitābi wabimā arsalnā bihi rusulanā fasawfa yaʿlamūna
Amharic ወደእነዚያ በመጽሐፉ በዚያም መልክተኞቻችንን በእርሱ በላክንበት ወዳስተባበሉት (አታይምን?) ወደፊትም ያውቃሉ፡፡
Verse 71
إِذِ ٱلْأَغْلَـٰلُ فِىٓ أَعْنَـٰقِهِمْ وَٱلسَّلَـٰسِلُ يُسْحَبُونَ
Transliteration idhi l-aghlālu fī aʿnāqihim wal-salāsilu yus'ḥabūna
Amharic እንዛዝላዎቹና ሰንሰለቶቹ በአንገቶቻቸው ላይ በተደረጉ ጊዜ (በእርሷ) ይጎተታሉ፡፡
Verse 72
فِى ٱلْحَمِيمِ ثُمَّ فِى ٱلنَّارِ يُسْجَرُونَ
Transliteration fī l-ḥamīmi thumma fī l-nāri yus'jarūna
Amharic በገሀነም ውስጥ (ይጎተታሉ)፤ ከዚያም በእሳት ውስጥ ይማገዳሉ፡፡
Verse 73
ثُمَّ قِيلَ لَهُمْ أَيْنَ مَا كُنتُمْ تُشْرِكُونَ
Transliteration thumma qīla lahum ayna mā kuntum tush'rikūna
Amharic ከዚያም ለእነርሱ ይባላሉ (በአላህ) «ታጋሯቸው የነበራችሁት የታሉ?»
Verse 74
مِن دُونِ ٱللَّهِ ۖ قَالُوا۟ ضَلُّوا۟ عَنَّا بَل لَّمْ نَكُن نَّدْعُوا۟ مِن قَبْلُ شَيْـًٔا ۚ كَذَٰلِكَ يُضِلُّ ٱللَّهُ ٱلْكَـٰفِرِينَ
Transliteration min dūni l-lahi qālū ḍallū ʿannā bal lam nakun nadʿū min qablu shayan kadhālika yuḍillu l-lahu l-kāfirīna
Amharic «ከአላህ ሌላ (የምታጋሩዋቸው)፤ ከኛ ተሰወሩን?» «ከቶ ከዚህ በፊት ምንንም የምንገዛ አልነበርንም» ይላሉ፤ እንደዚሁ አላህ ከሓዲዎችን ያሳስታል፡፡
Verse 75
ذَٰلِكُم بِمَا كُنتُمْ تَفْرَحُونَ فِى ٱلْأَرْضِ بِغَيْرِ ٱلْحَقِّ وَبِمَا كُنتُمْ تَمْرَحُونَ
Transliteration dhālikum bimā kuntum tafraḥūna fī l-arḍi bighayri l-ḥaqi wabimā kuntum tamraḥūna
Amharic ይህ (ቅጣት) ያላግባብ በምድር ውሰጥ ትደሰቱ በነበራችሁትና ትንበጣረሩ በነበራችሁት ነው (ይባላሉ)፡፡
Verse 76
ٱدْخُلُوٓا۟ أَبْوَٰبَ جَهَنَّمَ خَـٰلِدِينَ فِيهَا ۖ فَبِئْسَ مَثْوَى ٱلْمُتَكَبِّرِينَ
Transliteration ud'khulū abwāba jahannama khālidīna fīhā fabi'sa mathwā l-mutakabirīna
Amharic የገሀነምን በሮች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ (ይባላሉ)፡፡ የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ገሀነም) ምን ትከፋ!
Verse 77
فَٱصْبِرْ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ ۚ فَإِمَّا نُرِيَنَّكَ بَعْضَ ٱلَّذِى نَعِدُهُمْ أَوْ نَتَوَفَّيَنَّكَ فَإِلَيْنَا يُرْجَعُونَ
Transliteration fa-iṣ'bir inna waʿda l-lahi ḥaqqun fa-immā nuriyannaka baʿḍa alladhī naʿiduhum aw natawaffayannaka fa-ilaynā yur'jaʿūna
Amharic ታገስም የአላህ ቀጠሮ እውነት ነውና፡፡ የዚያንም የምናስፈራራቸውን ከፊሉን (በሕይወትህ) ብናሳይህ (መልካም ነው)፡፡ ወይም ብንገድልህ ወደኛ ይመለሳሉ፡፡
Verse 78
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ مِنْهُم مَّن قَصَصْنَا عَلَيْكَ وَمِنْهُم مَّن لَّمْ نَقْصُصْ عَلَيْكَ ۗ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِىَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ ۚ فَإِذَا جَآءَ أَمْرُ ٱللَّهِ قُضِىَ بِٱلْحَقِّ وَخَسِرَ هُنَالِكَ ٱلْمُبْطِلُونَ
Transliteration walaqad arsalnā rusulan min qablika min'hum man qaṣaṣnā ʿalayka wamin'hum man lam naqṣuṣ ʿalayka wamā kāna lirasūlin an yatiya biāyatin illā bi-idh'ni l-lahi fa-idhā jāa amru l-lahi quḍiya bil-ḥaqi wakhasira hunālika l-mub'ṭilūna
Amharic ካንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ከእነርሱ ባንተ ላይ የተረክንልህ አልለ፡፡ ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነው አልለ፡፡ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልኾነ ተዓምርን ሊያመጣ አይገባውም፡፡ የአላህም ትእዛዝ በመጣ ጊዜ በእውነት ይፈረዳል፡፡ እዚያ ዘንድም አጥፊዎቹ ይከስራሉ፡፡
Verse 79
ٱللَّهُ ٱلَّذِى جَعَلَ لَكُمُ ٱلْأَنْعَـٰمَ لِتَرْكَبُوا۟ مِنْهَا وَمِنْهَا تَأْكُلُونَ
Transliteration al-lahu alladhī jaʿala lakumu l-anʿāma litarkabū min'hā wamin'hā takulūna
Amharic አላህ ያ ለእናንተ ግመልን ከብትንና ፍየልን ከእርሷ (ከፊሏን) ልትጋልቡ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ከእርሷም ትበላላችሁ፡፡
Verse 80
وَلَكُمْ فِيهَا مَنَـٰفِعُ وَلِتَبْلُغُوا۟ عَلَيْهَا حَاجَةً فِى صُدُورِكُمْ وَعَلَيْهَا وَعَلَى ٱلْفُلْكِ تُحْمَلُونَ
Transliteration walakum fīhā manāfiʿu walitablughū ʿalayhā ḥājatan fī ṣudūrikum waʿalayhā waʿalā l-ful'ki tuḥ'malūna
Amharic ለእናንተም በእርሷ ውስጥ ጥቅሞች አልሏችሁ፡፡ በእርሷም ላይ (እቃን በመጫን) በልቦቻችሁ ያሰባችሁትን ጉዳይ ትደርሱ ዘንድ (ፈጠረላችሁ)፡፡ በእርሷም ላይ በመርከቦችም ላይ ትሳፈራላችሁ፡፡
Verse 81
وَيُرِيكُمْ ءَايَـٰتِهِۦ فَأَىَّ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ تُنكِرُونَ
Transliteration wayurīkum āyātihi fa-ayya āyāti l-lahi tunkirūna
Amharic ተዓምራቱንም ያሳያችኋል፡፡ ታዲያ ከአላህ ተዓምራት የትኛውን ትክዳላችሁ?
Verse 82
أَفَلَمْ يَسِيرُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ فَيَنظُرُوا۟ كَيْفَ كَانَ عَـٰقِبَةُ ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِهِمْ ۚ كَانُوٓا۟ أَكْثَرَ مِنْهُمْ وَأَشَدَّ قُوَّةً وَءَاثَارًا فِى ٱلْأَرْضِ فَمَآ أَغْنَىٰ عَنْهُم مَّا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ
Transliteration afalam yasīrū fī l-arḍi fayanẓurū kayfa kāna ʿāqibatu alladhīna min qablihim kānū akthara min'hum wa-ashadda quwwatan waāthāran fī l-arḍi famā aghnā ʿanhum mā kānū yaksibūna
Amharic የእነዚያን ከእነርሱ በፊት የነበሩትን ሕዝቦች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ ይመለከቱ ዘንድ በምድር ላይ አይኼዱምን? ከእነርሱ ይበልጥ ብዙዎች በኀይልና በምድር ላይ በተዋቸው ምልክቶችም በጣም ብርቱዎች ነበሩ፡፡ ያም ይሠሩት የነበሩት ከእነርሱ ምንም አልጠቀማቸውም፡፡
Verse 83
فَلَمَّا جَآءَتْهُمْ رُسُلُهُم بِٱلْبَيِّنَـٰتِ فَرِحُوا۟ بِمَا عِندَهُم مِّنَ ٱلْعِلْمِ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ
Transliteration falammā jāathum rusuluhum bil-bayināti fariḥū bimā ʿindahum mina l-ʿil'mi waḥāqa bihim mā kānū bihi yastahziūna
Amharic መልክተኞቻቸውም ተዓምራቶችን ባመጡላቸው ጊዜ እነርሱ ዘንድ ባለው ዕውቀት ተደሰቱ፡፡ በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣትም በእነርሱ ላይ ሰፈረባቸው፡፡
Verse 84
فَلَمَّا رَأَوْا۟ بَأْسَنَا قَالُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱللَّهِ وَحْدَهُۥ وَكَفَرْنَا بِمَا كُنَّا بِهِۦ مُشْرِكِينَ
Transliteration falammā ra-aw basanā qālū āmannā bil-lahi waḥdahu wakafarnā bimā kunnā bihi mush'rikīna
Amharic ብርቱ ቅጣታችንንም ባዩ ጊዜ «በአላህ አንድ ሲኾን አምነናል፤ በእርሱም እናጋራ በነበርነው (ጣዖታት) ክደናል» አሉ፡፡
Verse 85
فَلَمْ يَكُ يَنفَعُهُمْ إِيمَـٰنُهُمْ لَمَّا رَأَوْا۟ بَأْسَنَا ۖ سُنَّتَ ٱللَّهِ ٱلَّتِى قَدْ خَلَتْ فِى عِبَادِهِۦ ۖ وَخَسِرَ هُنَالِكَ ٱلْكَـٰفِرُونَ
Transliteration falam yaku yanfaʿuhum īmānuhum lammā ra-aw basanā sunnata l-lahi allatī qad khalat fī ʿibādihi wakhasira hunālika l-kāfirūna
Amharic ብርቱ ቅጣታችንን ባዩ ጊዜ ማመናቸውም የሚጠቅማቸው አልነበረም፡፡ የአላህን ደንብ ያችን በባሮቹ ውስጥ ያለፈችውን (ተጠንቀቁ) በዚያ ጊዜም ከሓዲዎች ከሰሩ፡፡
Read Surah Ghafir in another language
- English (word by word)
- Albanian
- Amazigh
- Assamese
- Azerbaijani
- Bambara
- Bangla
- Bosnian
- Bulgarian
- Chechen
- Chinese
- Czech
- Dari
- Dhivehi
- Dutch
- Finnish
- French
- German
- Gujarati
- Hausa
- Hebrew
- Hindi
- Indonesian
- Italian
- Japanese
- Kannada
- Kazakh
- Khmer
- Kinyarwanda
- Korean
- Kurdish
- Luganda
- Malay
- Malayalam
- Maranao
- Marathi
- Nepali
- Norwegian
- Oromo
- Pashto
- Persian
- Polish
- Portuguese
- Romanian
- Russian
- Sindhi
- Sinhala
- Somali
- Spanish
- Swahili
- Swedish
- Tagalog
- Tajik
- Tamil
- Tatar
- Telugu
- Thai
- Turkish
- Ukrainian
- Urdu
- Uyghur
- Uzbek
- Vietnamese
- Yao
- Yoruba
All 114 surahs in Amharic: the Qur’an in Amharic.
Amharic translation: Sadiq and Sani, from Quran.com. Transliteration: Quran.com. Recitation: Mishary Alafasy, from EveryAyah.com. MyDugsi is a learning aid, not a replacement for a qualified teacher.