Surah Al-Anbya in Amharic: translation and audio
Surah 21 · الأنبياء · The Prophets · 112 verses
Surah Al-Anbya verse by verse: the Arabic with a recitation you can repeat, the transliteration, and the Amharic translation by Sadiq and Sani. For the meaning of every word, see Surah Al-Anbya word by word in English.
Verse 1
ٱقْتَرَبَ لِلنَّاسِ حِسَابُهُمْ وَهُمْ فِى غَفْلَةٍ مُّعْرِضُونَ
Transliteration iq'taraba lilnnāsi ḥisābuhum wahum fī ghaflatin muʿ'riḍūna
Amharic ለሰዎች እነርሱ በዝንጋቴ ውስጥ (መሰናዳትን) የተው ኾነው ሳሉ ምርመራቸው ቀረበ፡፡
Verse 2
مَا يَأْتِيهِم مِّن ذِكْرٍ مِّن رَّبِّهِم مُّحْدَثٍ إِلَّا ٱسْتَمَعُوهُ وَهُمْ يَلْعَبُونَ
Transliteration mā yatīhim min dhik'rin min rabbihim muḥ'dathin illā is'tamaʿūhu wahum yalʿabūna
Amharic ከጌታቸው አዲስ የተወረደ ቁርኣን አይመጣላቸውም፡፡ እነሱ የሚያላግጡ ሆነው የሚያደምጡት ቢሆኑ እንጂ፡፡
Verse 3
لَاهِيَةً قُلُوبُهُمْ ۗ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّجْوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ هَلْ هَـٰذَآ إِلَّا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ ۖ أَفَتَأْتُونَ ٱلسِّحْرَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ
Transliteration lāhiyatan qulūbuhum wa-asarrū l-najwā alladhīna ẓalamū hal hādhā illā basharun mith'lukum afatatūna l-siḥ'ra wa-antum tub'ṣirūna
Amharic ልቦቻቸው ዝንጉዎች ኾነው (የሚያዳምጡት ቢኾኑ እንጅ)፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ፡፡ «ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን እናንተም የምታዩ ስትኾኑ ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን» (አሉ)፡፡
Verse 4
قَالَ رَبِّى يَعْلَمُ ٱلْقَوْلَ فِى ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ ۖ وَهُوَ ٱلسَّمِيعُ ٱلْعَلِيمُ
Transliteration qāla rabbī yaʿlamu l-qawla fī l-samāi wal-arḍi wahuwa l-samīʿu l-ʿalīmu
Amharic (ሙሐመድም) «ጌታዬ ቃልን ሁሉ በሰማይና በምድር ውስጥ ያለ ሲኾን ያውቃል እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው» አለ፡፡
Verse 5
بَلْ قَالُوٓا۟ أَضْغَـٰثُ أَحْلَـٰمٍۭ بَلِ ٱفْتَرَىٰهُ بَلْ هُوَ شَاعِرٌ فَلْيَأْتِنَا بِـَٔايَةٍ كَمَآ أُرْسِلَ ٱلْأَوَّلُونَ
Transliteration bal qālū aḍghāthu aḥlāmin bali if'tarāhu bal huwa shāʿirun falyatinā biāyatin kamā ur'sila l-awalūna
Amharic «በእውነቱ (ቁርኣኑ) የሕልሞች ቅዠቶች ነው፡፡ ይልቁንም ቀጠፈው እንዲያውም እርሱ ቅኔን ገጣሚ ነው፡፡ የቀድሞዎቹም እንደተላኩ (መልክተኛ ከኾነ) በተዓምር ይምጣብን» አሉ፡፡
Verse 6
مَآ ءَامَنَتْ قَبْلَهُم مِّن قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَـٰهَآ ۖ أَفَهُمْ يُؤْمِنُونَ
Transliteration mā āmanat qablahum min qaryatin ahlaknāhā afahum yu'minūna
Amharic ከእነሱ በፊት ያጠፋናት ከተማ አላመነችም፡፡ ታዲያ እነሱ ያምናሉን
Verse 7
وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
Transliteration wamā arsalnā qablaka illā rijālan nūḥī ilayhim fasalū ahla l-dhik'ri in kuntum lā taʿlamūna
Amharic ከአንተም በፊት ወደእነሱ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡
Verse 8
وَمَا جَعَلْنَـٰهُمْ جَسَدًا لَّا يَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُوا۟ خَـٰلِدِينَ
Transliteration wamā jaʿalnāhum jasadan lā yakulūna l-ṭaʿāma wamā kānū khālidīna
Amharic ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም፡፡ ዘውታሪዎችም አልነበሩም፡፡
Verse 9
ثُمَّ صَدَقْنَـٰهُمُ ٱلْوَعْدَ فَأَنجَيْنَـٰهُمْ وَمَن نَّشَآءُ وَأَهْلَكْنَا ٱلْمُسْرِفِينَ
Transliteration thumma ṣadaqnāhumu l-waʿda fa-anjaynāhum waman nashāu wa-ahlaknā l-mus'rifīna
Amharic ከዚያም ቀጠሮን ሞላንላቸው፡፡ አዳንናቸውም፡፡ የምንሻውንም ሰው (አዳን)፡፡ ወሰን አላፊዎቹንም አጠፋን፡፡
Verse 10
لَقَدْ أَنزَلْنَآ إِلَيْكُمْ كِتَـٰبًا فِيهِ ذِكْرُكُمْ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Transliteration laqad anzalnā ilaykum kitāban fīhi dhik'rukum afalā taʿqilūna
Amharic ክብራችሁ በውስጡ ያለበትን መጽሐፍ ወደእናንተ በእርግጥ አወረድን፡፡ አታውቁምን
Verse 11
وَكَمْ قَصَمْنَا مِن قَرْيَةٍ كَانَتْ ظَالِمَةً وَأَنشَأْنَا بَعْدَهَا قَوْمًا ءَاخَرِينَ
Transliteration wakam qaṣamnā min qaryatin kānat ẓālimatan wa-anshanā baʿdahā qawman ākharīna
Amharic በዳይም ከነበረች ከተማ ያጠፋናትና ከኋላዋም ሌሎችን ሕዝቦች ያስገኘነው ብዙ ናት፡፡
Verse 12
فَلَمَّآ أَحَسُّوا۟ بَأْسَنَآ إِذَا هُم مِّنْهَا يَرْكُضُونَ
Transliteration falammā aḥassū basanā idhā hum min'hā yarkuḍūna
Amharic ቅጣታችንም በተሰማቸው ጊዜ እነርሱ ወዲያውኑ ከእርሷ (ለመሸሽ) ይገሠግሣሉ፡፡
Verse 13
لَا تَرْكُضُوا۟ وَٱرْجِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَآ أُتْرِفْتُمْ فِيهِ وَمَسَـٰكِنِكُمْ لَعَلَّكُمْ تُسْـَٔلُونَ
Transliteration lā tarkuḍū wa-ir'jiʿū ilā mā ut'rif'tum fīhi wamasākinikum laʿallakum tus'alūna
Amharic አትገሥግሡ፤ ትለመኑም ይኾናልና፡፡ በእርሱ ወደ ተቀማጠላችሁበት ጸጋ ወደ መኖሪያዎቻችሁም ተመለሱ (ይባላሉ)፡፡
Verse 14
قَالُوا۟ يَـٰوَيْلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَـٰلِمِينَ
Transliteration qālū yāwaylanā innā kunnā ẓālimīna
Amharic «ዋ ጥፋታችን! እኛ በእርግጥ በዳዮች ነበርን» ይላሉ፡፡
Verse 15
فَمَا زَالَت تِّلْكَ دَعْوَىٰهُمْ حَتَّىٰ جَعَلْنَـٰهُمْ حَصِيدًا خَـٰمِدِينَ
Transliteration famā zālat til'ka daʿwāhum ḥattā jaʿalnāhum ḥaṣīdan khāmidīna
Amharic የታጨዱ ሬሳዎችም እስካደረግናቸው ድረስ ይህቺ ጠሪያቸው ከመኾን አልተወገደችም፡፡
Verse 16
وَمَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا لَـٰعِبِينَ
Transliteration wamā khalaqnā l-samāa wal-arḍa wamā baynahumā lāʿibīna
Amharic ሰማይንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ ቀላጆች ኾነን አልፈጠርንም፡፡
Verse 17
لَوْ أَرَدْنَآ أَن نَّتَّخِذَ لَهْوًا لَّٱتَّخَذْنَـٰهُ مِن لَّدُنَّآ إِن كُنَّا فَـٰعِلِينَ
Transliteration law aradnā an nattakhidha lahwan la-ittakhadhnāhu min ladunnā in kunnā fāʿilīna
Amharic መጫወቻን (ሚስትና ልጅን) ልንይዝ በሻን ኖሮ ከእኛ ዘንድ በያዝነው ነበር፡፡ (ግን) ሠሪዎች አይደለንም፡፡
Verse 18
بَلْ نَقْذِفُ بِٱلْحَقِّ عَلَى ٱلْبَـٰطِلِ فَيَدْمَغُهُۥ فَإِذَا هُوَ زَاهِقٌ ۚ وَلَكُمُ ٱلْوَيْلُ مِمَّا تَصِفُونَ
Transliteration bal naqdhifu bil-ḥaqi ʿalā l-bāṭili fayadmaghuhu fa-idhā huwa zāhiqun walakumu l-waylu mimmā taṣifūna
Amharic በእርግጥ እውነትን በውሸት ላይ እንጥላለን፡፡ አንጎሉን ያፈርሰዋልም፡፡ ወዲያውም እርሱ ጠፊ ነው፡፡ ለእናንተም ከዚያ (ሚስትና ልጅ አለው በማለት) ከምትመጥኑት ነገር ብርቱ ቅጣት አላችሁ፤ (ወዮላችሁ)፡፡
Verse 19
وَلَهُۥ مَن فِى ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ وَمَنْ عِندَهُۥ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِۦ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ
Transliteration walahu man fī l-samāwāti wal-arḍi waman ʿindahu lā yastakbirūna ʿan ʿibādatihi walā yastaḥsirūna
Amharic በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የእርሱ ነው፡፡ እርሱ ዘንድ ያሉትም (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፡፡ አይሰለቹምም፡፡
Verse 20
يُسَبِّحُونَ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ لَا يَفْتُرُونَ
Transliteration yusabbiḥūna al-layla wal-nahāra lā yafturūna
Amharic በሌሊትና በቀንም ያጠሩታል፤ አያርፉም፡፡
Verse 21
أَمِ ٱتَّخَذُوٓا۟ ءَالِهَةً مِّنَ ٱلْأَرْضِ هُمْ يُنشِرُونَ
Transliteration ami ittakhadhū ālihatan mina l-arḍi hum yunshirūna
Amharic ይልቁንም ከምድር የኾኑን እነርሱ ሙታንን የሚያስነሱን አማልክት ያዙን (የለም)፡፡
Verse 22
لَوْ كَانَ فِيهِمَآ ءَالِهَةٌ إِلَّا ٱللَّهُ لَفَسَدَتَا ۚ فَسُبْحَـٰنَ ٱللَّهِ رَبِّ ٱلْعَرْشِ عَمَّا يَصِفُونَ
Transliteration law kāna fīhimā ālihatun illā l-lahu lafasadatā fasub'ḥāna l-lahi rabbi l-ʿarshi ʿammā yaṣifūna
Amharic በሁለቱ (በሰማያትና በምድር) ውስጥ ከአላህ ሌላ አማልክት በነበሩ ኖሮ በተበላሹ ነበር፡፡ የዐርሹ ጌታ አላህም ከሚሉት ሁሉ ጠራ፡፡
Verse 23
لَا يُسْـَٔلُ عَمَّا يَفْعَلُ وَهُمْ يُسْـَٔلُونَ
Transliteration lā yus'alu ʿammā yafʿalu wahum yus'alūna
Amharic ከሚሠራው ሁሉ አይጠየቅም፡፡ እነርሱ (ፍጥረቶቹ) ግን ይጠየቃሉ፡፡
Verse 24
أَمِ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِهِۦٓ ءَالِهَةً ۖ قُلْ هَاتُوا۟ بُرْهَـٰنَكُمْ ۖ هَـٰذَا ذِكْرُ مَن مَّعِىَ وَذِكْرُ مَن قَبْلِى ۗ بَلْ أَكْثَرُهُمْ لَا يَعْلَمُونَ ٱلْحَقَّ ۖ فَهُم مُّعْرِضُونَ
Transliteration ami ittakhadhū min dūnihi ālihatan qul hātū bur'hānakum hādhā dhik'ru man maʿiya wadhik'ru man qablī bal aktharuhum lā yaʿlamūna l-ḥaqa fahum muʿ'riḍūna
Amharic ይልቁንም ከእርሱ ሌላ አማልክትን ያዙን «አስረጃችሁን አምጡ፡፡ ይህ (ቁርኣን) እኔ ዘንድ ያለው ሕዝብ መገሰጫ ከእኔ በፊትም የነበሩት ሕዝቦች መገሰጫ ነው» በላቸው፡፡ በውነቱ አብዛኞቻቸው እውነቱን አያውቁም፡፡ ስለዚህ እነሱ እምቢተኞች ናቸው፡፡
Verse 25
وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَـٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
Transliteration wamā arsalnā min qablika min rasūlin illā nūḥī ilayhi annahu lā ilāha illā anā fa-uʿ'budūni
Amharic ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡
Verse 26
وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحْمَـٰنُ وَلَدًا ۗ سُبْحَـٰنَهُۥ ۚ بَلْ عِبَادٌ مُّكْرَمُونَ
Transliteration waqālū ittakhadha l-raḥmānu waladan sub'ḥānahu bal ʿibādun muk'ramūna
Amharic «አልረሕማንም (ከመላእክት) ልጅን ያዘ» አሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ አይደለም (መላእክት) የተከበሩ ባሮች ናቸው፡፡
Verse 27
لَا يَسْبِقُونَهُۥ بِٱلْقَوْلِ وَهُم بِأَمْرِهِۦ يَعْمَلُونَ
Transliteration lā yasbiqūnahu bil-qawli wahum bi-amrihi yaʿmalūna
Amharic በንግግር አይቀድሙትም፤ (ያላለውን አይሉም)፡፡ እነርሱም በትእዛዙ ይሠራሉ፡፡
Verse 28
يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلَا يَشْفَعُونَ إِلَّا لِمَنِ ٱرْتَضَىٰ وَهُم مِّنْ خَشْيَتِهِۦ مُشْفِقُونَ
Transliteration yaʿlamu mā bayna aydīhim wamā khalfahum walā yashfaʿūna illā limani ir'taḍā wahum min khashyatihi mush'fiqūna
Amharic በፊታቸው ያለውንና በኋላቸው ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ለወደደውም ሰው እንጅ ለሌላው አያማልዱም፡፡ እነርሱም እርሱን ከመፍራታቸው የተነሳ ተጨናቂዎች ናቸው፡፡
Verse 29
۞ وَمَن يَقُلْ مِنْهُمْ إِنِّىٓ إِلَـٰهٌ مِّن دُونِهِۦ فَذَٰلِكَ نَجْزِيهِ جَهَنَّمَ ۚ كَذَٰلِكَ نَجْزِى ٱلظَّـٰلِمِينَ
Transliteration waman yaqul min'hum innī ilāhun min dūnihi fadhālika najzīhi jahannama kadhālika najzī l-ẓālimīna
Amharic ከእነሱም «እኔ ከእርሱ ሌላ አምላክ ነኝ» የሚል ያንን ገሀነምን እንመነዳዋለን፡፡ እንደዚሁ በዳዮችን እንመነዳለን፡፡
Verse 30
أَوَلَمْ يَرَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَنَّ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ كَانَتَا رَتْقًا فَفَتَقْنَـٰهُمَا ۖ وَجَعَلْنَا مِنَ ٱلْمَآءِ كُلَّ شَىْءٍ حَىٍّ ۖ أَفَلَا يُؤْمِنُونَ
Transliteration awalam yara alladhīna kafarū anna l-samāwāti wal-arḍa kānatā ratqan fafataqnāhumā wajaʿalnā mina l-māi kulla shayin ḥayyin afalā yu'minūna
Amharic እነዚያም የካዱት ሰማያትና ምድር የተጣበቁ የነበሩና የለያየናቸው መኾናችንን አያውቁምን ሕያው የኾነንም ነገር ሁሉ ከውሃ ፈጠርን፡፡ አያምኑምን
Verse 31
وَجَعَلْنَا فِى ٱلْأَرْضِ رَوَٰسِىَ أَن تَمِيدَ بِهِمْ وَجَعَلْنَا فِيهَا فِجَاجًا سُبُلًا لَّعَلَّهُمْ يَهْتَدُونَ
Transliteration wajaʿalnā fī l-arḍi rawāsiya an tamīda bihim wajaʿalnā fīhā fijājan subulan laʿallahum yahtadūna
Amharic በምድርም ውስጥ በእነሱ እንዳታረገርግ ጋራዎችን አደረግን፡፡ ይመሩም ዘንድ በእርሷ ውስጥ ሰፋፊ መንገዶችን አደረግን፡፡
Verse 32
وَجَعَلْنَا ٱلسَّمَآءَ سَقْفًا مَّحْفُوظًا ۖ وَهُمْ عَنْ ءَايَـٰتِهَا مُعْرِضُونَ
Transliteration wajaʿalnā l-samāa saqfan maḥfūẓan wahum ʿan āyātihā muʿ'riḍūna
Amharic ሰማይንም (ከመውደቅ) የተጠበቀ ጣራ አደረግን፡፡ እነርሱም ከተዓምራቶቿ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
Verse 33
وَهُوَ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ ۖ كُلٌّ فِى فَلَكٍ يَسْبَحُونَ
Transliteration wahuwa alladhī khalaqa al-layla wal-nahāra wal-shamsa wal-qamara kullun fī falakin yasbaḥūna
Amharic እርሱም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ ነው፡፡ ሁሉም በፈለካቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡
Verse 34
وَمَا جَعَلْنَا لِبَشَرٍ مِّن قَبْلِكَ ٱلْخُلْدَ ۖ أَفَإِي۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلْخَـٰلِدُونَ
Transliteration wamā jaʿalnā libasharin min qablika l-khul'da afa-in mitta fahumu l-khālidūna
Amharic (ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም፡፡ ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን
Verse 35
كُلُّ نَفْسٍ ذَآئِقَةُ ٱلْمَوْتِ ۗ وَنَبْلُوكُم بِٱلشَّرِّ وَٱلْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ
Transliteration kullu nafsin dhāiqatu l-mawti wanablūkum bil-shari wal-khayri fit'natan wa-ilaynā tur'jaʿūna
Amharic ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ለመፈተንም በክፉም በበጎም እንሞክራችኋለን፡፡ ወደኛም ትመለሳላችሁ፡፡
Verse 36
وَإِذَا رَءَاكَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ إِن يَتَّخِذُونَكَ إِلَّا هُزُوًا أَهَـٰذَا ٱلَّذِى يَذْكُرُ ءَالِهَتَكُمْ وَهُم بِذِكْرِ ٱلرَّحْمَـٰنِ هُمْ كَـٰفِرُونَ
Transliteration wa-idhā raāka alladhīna kafarū in yattakhidhūnaka illā huzuwan ahādhā alladhī yadhkuru ālihatakum wahum bidhik'ri l-raḥmāni hum kāfirūna
Amharic እነዚያም የካዱት ሰዎች ባዩህ ጊዜ መሳለቂያ አድርገው እንጂ አይይዙህም፡፡ እነሱ በአልረሕማን መወሳት እነርሱ ከሓዲዎች ሲሆኑ «ያ አማልክቶቻችሁን (በክፉ) የሚያነሳው ይህ ነውን» (ይላሉ)፡፡
Verse 37
خُلِقَ ٱلْإِنسَـٰنُ مِنْ عَجَلٍ ۚ سَأُو۟رِيكُمْ ءَايَـٰتِى فَلَا تَسْتَعْجِلُونِ
Transliteration khuliqa l-insānu min ʿajalin sa-urīkum āyātī falā tastaʿjilūni
Amharic ሰው ቸኳይ ሆኖ ተፈጠረ፡፡ ተዓምራቶቼን በእርግጥ አሳያችኋለሁና አታቻኩሉኝ፡፡
Verse 38
وَيَقُولُونَ مَتَىٰ هَـٰذَا ٱلْوَعْدُ إِن كُنتُمْ صَـٰدِقِينَ
Transliteration wayaqūlūna matā hādhā l-waʿdu in kuntum ṣādiqīna
Amharic «ይህ ቀጠሮም መቼ ነው እውነተኞች ከኾናችሁ (አምጡት)» ይላሉ፡፡
Verse 39
لَوْ يَعْلَمُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ حِينَ لَا يَكُفُّونَ عَن وُجُوهِهِمُ ٱلنَّارَ وَلَا عَن ظُهُورِهِمْ وَلَا هُمْ يُنصَرُونَ
Transliteration law yaʿlamu alladhīna kafarū ḥīna lā yakuffūna ʿan wujūhihimu l-nāra walā ʿan ẓuhūrihim walā hum yunṣarūna
Amharic እነዚያ የካዱት ከፊቶቻቸውና ከጀርባዎቻቸው ላይ እሳትን የማይከለክሉበትን እነሱም የማይረዳዱበትን ጊዜ ቢያውቁ ኖሮ (ይህንን አይሉም ነበር)፡፡
Verse 40
بَلْ تَأْتِيهِم بَغْتَةً فَتَبْهَتُهُمْ فَلَا يَسْتَطِيعُونَ رَدَّهَا وَلَا هُمْ يُنظَرُونَ
Transliteration bal tatīhim baghtatan fatabhatuhum falā yastaṭīʿūna raddahā walā hum yunẓarūna
Amharic ይልቁንም (ሰዓቲቱ) በድንገት ትመጣቸዋለች፤ ታዋልላቸዋለችም፡፡ መመለሷንም አይችሉም፡፡ እነሱም አይቆዩም፡፡
Verse 41
وَلَقَدِ ٱسْتُهْزِئَ بِرُسُلٍ مِّن قَبْلِكَ فَحَاقَ بِٱلَّذِينَ سَخِرُوا۟ مِنْهُم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ
Transliteration walaqadi us'tuh'zi-a birusulin min qablika faḥāqa bi-alladhīna sakhirū min'hum mā kānū bihi yastahziūna
Amharic ከአንተ በፊትም የነበሩት መልክተኞች በእርግጥ ተቀለደባቸው፡፡ በእነዚያም ከእነሱ ይቀልዱ በነበሩት በርሱ ይሳለቁበት የነበሩት (ቅጣት) ሰፈረባቸው፡፡
Verse 42
قُلْ مَن يَكْلَؤُكُم بِٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ مِنَ ٱلرَّحْمَـٰنِ ۗ بَلْ هُمْ عَن ذِكْرِ رَبِّهِم مُّعْرِضُونَ
Transliteration qul man yakla-ukum bi-al-layli wal-nahāri mina l-raḥmāni bal hum ʿan dhik'ri rabbihim muʿ'riḍūna
Amharic «ከአልረሕማን (ቅጣት) በሌሊትና በቀን የሚጠብቃችሁ ማነው» በላቸው፡፡ በእውነቱ እነሱ ከጌታቸው ግሳጼ (ከቁርአን) ዘንጊዎች ናቸው፡፡
Verse 43
أَمْ لَهُمْ ءَالِهَةٌ تَمْنَعُهُم مِّن دُونِنَا ۚ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَ أَنفُسِهِمْ وَلَا هُم مِّنَّا يُصْحَبُونَ
Transliteration am lahum ālihatun tamnaʿuhum min dūninā lā yastaṭīʿūna naṣra anfusihim walā hum minnā yuṣ'ḥabūna
Amharic ለእነሱ ከእኛ ሌላ የምትከላከልላቸው አማልክት አለቻቸውን ነፍሶቻቸውን መርዳትን አይችሉም፡፡ እነርሱም (ከሓዲዎቹ) ከእኛ አይጠበቁም፡፡
Verse 44
بَلْ مَتَّعْنَا هَـٰٓؤُلَآءِ وَءَابَآءَهُمْ حَتَّىٰ طَالَ عَلَيْهِمُ ٱلْعُمُرُ ۗ أَفَلَا يَرَوْنَ أَنَّا نَأْتِى ٱلْأَرْضَ نَنقُصُهَا مِنْ أَطْرَافِهَآ ۚ أَفَهُمُ ٱلْغَـٰلِبُونَ
Transliteration bal mattaʿnā hāulāi waābāahum ḥattā ṭāla ʿalayhimu l-ʿumuru afalā yarawna annā natī l-arḍa nanquṣuhā min aṭrāfihā afahumu l-ghālibūna
Amharic በእውነት እነዚህንና አባቶቻቸውን በእነሱ ላይ ዕድሜ እስከ ረዘመባቸው ድረስ አጣቀምናቸው፡፡ (ተታለሉም)፡፡ እኛ ምድርን ከጫፎችዋ የምናጎላት ኾነን ስንመጣባት አያዩምን እነሱ አሸናፊዎች ናቸውን
Verse 45
قُلْ إِنَّمَآ أُنذِرُكُم بِٱلْوَحْىِ ۚ وَلَا يَسْمَعُ ٱلصُّمُّ ٱلدُّعَآءَ إِذَا مَا يُنذَرُونَ
Transliteration qul innamā undhirukum bil-waḥyi walā yasmaʿu l-ṣumu l-duʿāa idhā mā yundharūna
Amharic «የማስፈራራችሁ በተወረደልኝ ብቻ ነው፡፡ ግን ደንቆሮዎች በሚስፈራሩ ጊዜ ጥሪን አይሰሙም» በላቸው፡፡
Verse 46
وَلَئِن مَّسَّتْهُمْ نَفْحَةٌ مِّنْ عَذَابِ رَبِّكَ لَيَقُولُنَّ يَـٰوَيْلَنَآ إِنَّا كُنَّا ظَـٰلِمِينَ
Transliteration wala-in massathum nafḥatun min ʿadhābi rabbika layaqūlunna yāwaylanā innā kunnā ẓālimīna
Amharic ከጌታህ ቅጣትም ወላፈን ብትነካቸው «ዋ ጥፋታችን! እኛ በዳዮች ነበርን» ይላሉ፡፡
Verse 47
وَنَضَعُ ٱلْمَوَٰزِينَ ٱلْقِسْطَ لِيَوْمِ ٱلْقِيَـٰمَةِ فَلَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْـًٔا ۖ وَإِن كَانَ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ أَتَيْنَا بِهَا ۗ وَكَفَىٰ بِنَا حَـٰسِبِينَ
Transliteration wanaḍaʿu l-mawāzīna l-qis'ṭa liyawmi l-qiyāmati falā tuẓ'lamu nafsun shayan wa-in kāna mith'qāla ḥabbatin min khardalin ataynā bihā wakafā binā ḥāsibīna
Amharic በትንሣኤም ቀን ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፡፡ (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢኾንም እርሷን እናመጣታለን፡፡ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ፡፡
Verse 48
وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَـٰرُونَ ٱلْفُرْقَانَ وَضِيَآءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ
Transliteration walaqad ātaynā mūsā wahārūna l-fur'qāna waḍiyāan wadhik'ran lil'muttaqīna
Amharic ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡
Verse 49
ٱلَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِٱلْغَيْبِ وَهُم مِّنَ ٱلسَّاعَةِ مُشْفِقُونَ
Transliteration alladhīna yakhshawna rabbahum bil-ghaybi wahum mina l-sāʿati mush'fiqūna
Amharic ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለኾኑ (መገሰጫን ሰጠን)፡፡
Verse 50
وَهَـٰذَا ذِكْرٌ مُّبَارَكٌ أَنزَلْنَـٰهُ ۚ أَفَأَنتُمْ لَهُۥ مُنكِرُونَ
Transliteration wahādhā dhik'run mubārakun anzalnāhu afa-antum lahu munkirūna
Amharic ይህም (ቁርኣን) ያወረድነው የኾነ ብሩክ መገሰጫ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ ለእርሱ ከሓዲዎች ናችሁን
Verse 51
۞ وَلَقَدْ ءَاتَيْنَآ إِبْرَٰهِيمَ رُشْدَهُۥ مِن قَبْلُ وَكُنَّا بِهِۦ عَـٰلِمِينَ
Transliteration walaqad ātaynā ib'rāhīma rush'dahu min qablu wakunnā bihi ʿālimīna
Amharic ለኢብራሂምም ከዚያ በፊት ቅን መንገዱን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ እኛም በእርሱ (ተገቢነት) ዐዋቂዎች ነበርን፡፡
Verse 52
إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِۦ مَا هَـٰذِهِ ٱلتَّمَاثِيلُ ٱلَّتِىٓ أَنتُمْ لَهَا عَـٰكِفُونَ
Transliteration idh qāla li-abīhi waqawmihi mā hādhihi l-tamāthīlu allatī antum lahā ʿākifūna
Amharic ለአባቱና ለሕዝቦቹ «ይህቺ ቅርጻ ቅርጽ ያቺ እናንተ ለእርሷ ተገዢዎች የኾናችሁት ምንድን ናት» ባለ ጊዜ (መራነው)፡፡
Verse 53
قَالُوا۟ وَجَدْنَآ ءَابَآءَنَا لَهَا عَـٰبِدِينَ
Transliteration qālū wajadnā ābāanā lahā ʿābidīna
Amharic «አባቶቻችንን ለእርሷ ተገዢዎች ኾነው አገኘን» አሉት፡፡
Verse 54
قَالَ لَقَدْ كُنتُمْ أَنتُمْ وَءَابَآؤُكُمْ فِى ضَلَـٰلٍ مُّبِينٍ
Transliteration qāla laqad kuntum antum waābāukum fī ḍalālin mubīnin
Amharic «እናንተም አባቶቻችሁም በእርግጥ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነበራችሁ» አላቸው፡፡
Verse 55
قَالُوٓا۟ أَجِئْتَنَا بِٱلْحَقِّ أَمْ أَنتَ مِنَ ٱللَّـٰعِبِينَ
Transliteration qālū aji'tanā bil-ḥaqi am anta mina l-lāʿibīna
Amharic «በምሩ መጣህልን ወይንስ አንተ ከሚቀልዱት ነህ» አሉት፡፡
Verse 56
قَالَ بَل رَّبُّكُمْ رَبُّ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ٱلَّذِى فَطَرَهُنَّ وَأَنَا۠ عَلَىٰ ذَٰلِكُم مِّنَ ٱلشَّـٰهِدِينَ
Transliteration qāla bal rabbukum rabbu l-samāwāti wal-arḍi alladhī faṭarahunna wa-anā ʿalā dhālikum mina l-shāhidīna
Amharic «አይደለም ጌታችሁ የሰማያትና የምድር ጌታ ያ የፈጠራቸው ነው፡፡ እኔም በዚህ ላይ ከመስካሪዎቹ ነኝ» አለ፡፡
Verse 57
وَتَٱللَّهِ لَأَكِيدَنَّ أَصْنَـٰمَكُم بَعْدَ أَن تُوَلُّوا۟ مُدْبِرِينَ
Transliteration watal-lahi la-akīdanna aṣnāmakum baʿda an tuwallū mud'birīna
Amharic «በአላህም እምላለሁ ዟሪዎች ኾናችሁ ከሄዳችሁ በኋላ ጣዖቶቻችሁን ተንኮል እሠራባቸዋለሁ» (አለ)፡፡
Verse 58
فَجَعَلَهُمْ جُذَٰذًا إِلَّا كَبِيرًا لَّهُمْ لَعَلَّهُمْ إِلَيْهِ يَرْجِعُونَ
Transliteration fajaʿalahum judhādhan illā kabīran lahum laʿallahum ilayhi yarjiʿūna
Amharic (ዘወር ሲሉ) ስብርብሮችም አደረጋቸው፡፡ ለእነሱ የኾነ አንድ ታላቅ (ጣዖት) ብቻ ሲቀር ወደርሱ ይመለሱ ዘንድ (እርሱን ተወው)፡፡
Verse 59
قَالُوا۟ مَن فَعَلَ هَـٰذَا بِـَٔالِهَتِنَآ إِنَّهُۥ لَمِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ
Transliteration qālū man faʿala hādhā biālihatinā innahu lamina l-ẓālimīna
Amharic «በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራ ማነው እርሱ በእርግጥ ከበደለኞች ነው» አሉ፡፡
Verse 60
قَالُوا۟ سَمِعْنَا فَتًى يَذْكُرُهُمْ يُقَالُ لَهُۥٓ إِبْرَٰهِيمُ
Transliteration qālū samiʿ'nā fatan yadhkuruhum yuqālu lahu ib'rāhīmu
Amharic «ኢብራሂም የሚባል ጎበዝ (በመጥፎ) ሲያነሳቸው ሰምተናል» ተባባሉ፡፡
Verse 61
قَالُوا۟ فَأْتُوا۟ بِهِۦ عَلَىٰٓ أَعْيُنِ ٱلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَشْهَدُونَ
Transliteration qālū fatū bihi ʿalā aʿyuni l-nāsi laʿallahum yashhadūna
Amharic «ይመሰክሩበት ዘንድ በሰዎቹ ዓይን (ፊት) ላይ አምጡት» አሉ፡፡
Verse 62
قَالُوٓا۟ ءَأَنتَ فَعَلْتَ هَـٰذَا بِـَٔالِهَتِنَا يَـٰٓإِبْرَٰهِيمُ
Transliteration qālū a-anta faʿalta hādhā biālihatinā yāib'rāhīmu
Amharic «ኢብራሂም ሆይ! በአማልክቶቻችን ይህንን የሠራህ አንተ ነህን» አሉት፡፡
Verse 63
قَالَ بَلْ فَعَلَهُۥ كَبِيرُهُمْ هَـٰذَا فَسْـَٔلُوهُمْ إِن كَانُوا۟ يَنطِقُونَ
Transliteration qāla bal faʿalahu kabīruhum hādhā fasalūhum in kānū yanṭiqūna
Amharic «አይደለም ይህ ታላቃቸው ሠራው፡፡ ይናገሩም እንደ ኾነ ጠይቋቸው» አለ፡፡
Verse 64
فَرَجَعُوٓا۟ إِلَىٰٓ أَنفُسِهِمْ فَقَالُوٓا۟ إِنَّكُمْ أَنتُمُ ٱلظَّـٰلِمُونَ
Transliteration farajaʿū ilā anfusihim faqālū innakum antumu l-ẓālimūna
Amharic ወደ ነፍሶቻቸውም ተመለሱ፡፡ «እናንተ (በመጠየቃችሁ) በዳዮቹ እናንተው ናችሁም» ተባባሉ፡፡
Verse 65
ثُمَّ نُكِسُوا۟ عَلَىٰ رُءُوسِهِمْ لَقَدْ عَلِمْتَ مَا هَـٰٓؤُلَآءِ يَنطِقُونَ
Transliteration thumma nukisū ʿalā ruūsihim laqad ʿalim'ta mā hāulāi yanṭiqūna
Amharic ከዚያም በራሶቻቸው ላይ ተገለበጡ፡፡ «እነዚህ የሚናገሩ አለመኾናቸውን በእርግጥ ዐውቀሃል፤» (አሉ)፡፡
Verse 66
قَالَ أَفَتَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكُمْ شَيْـًٔا وَلَا يَضُرُّكُمْ
Transliteration qāla afataʿbudūna min dūni l-lahi mā lā yanfaʿukum shayan walā yaḍurrukum
Amharic «ታዲያ ለእናንተ ምንም የማይጠቅማችሁንና የማይጎዳችሁን ነገር ከአላህ ሌላ ትገዛላችሁን» አላቸው፡፡
Verse 67
أُفٍّ لَّكُمْ وَلِمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ ۖ أَفَلَا تَعْقِلُونَ
Transliteration uffin lakum walimā taʿbudūna min dūni l-lahi afalā taʿqilūna
Amharic «ፎህ! ለእናንተ ከአላህ ሌላ ለምትገዙትም ነገር፤ አታውቁምን» (አለ)፡፡
Verse 68
قَالُوا۟ حَرِّقُوهُ وَٱنصُرُوٓا۟ ءَالِهَتَكُمْ إِن كُنتُمْ فَـٰعِلِينَ
Transliteration qālū ḥarriqūhu wa-unṣurū ālihatakum in kuntum fāʿilīna
Amharic «ሠሪዎች እንደ ኾናችሁ አቃጥሉት፡፡ አማልክቶቻችሁንም እርዱ» አሉ፡፡ (በእሳት ላይ ጣሉትም)፡፡
Verse 69
قُلْنَا يَـٰنَارُ كُونِى بَرْدًا وَسَلَـٰمًا عَلَىٰٓ إِبْرَٰهِيمَ
Transliteration qul'nā yānāru kūnī bardan wasalāman ʿalā ib'rāhīma
Amharic «እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛ፤ ሰላምም ሁኚ» አልን፡፡
Verse 70
وَأَرَادُوا۟ بِهِۦ كَيْدًا فَجَعَلْنَـٰهُمُ ٱلْأَخْسَرِينَ
Transliteration wa-arādū bihi kaydan fajaʿalnāhumu l-akhsarīna
Amharic በእርሱም ተንኮልን አሰቡ፡፡ በጣም ከሳሪዎችም አደረግናቸው፡፡
Verse 71
وَنَجَّيْنَـٰهُ وَلُوطًا إِلَى ٱلْأَرْضِ ٱلَّتِى بَـٰرَكْنَا فِيهَا لِلْعَـٰلَمِينَ
Transliteration wanajjaynāhu walūṭan ilā l-arḍi allatī bāraknā fīhā lil'ʿālamīna
Amharic እርሱንና ሉጥንም ወደዚያች፤ በውስጧ ለዓለማት በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (በመውሰድ) አዳን፡፡
Verse 72
وَوَهَبْنَا لَهُۥٓ إِسْحَـٰقَ وَيَعْقُوبَ نَافِلَةً ۖ وَكُلًّا جَعَلْنَا صَـٰلِحِينَ
Transliteration wawahabnā lahu is'ḥāqa wayaʿqūba nāfilatan wakullan jaʿalnā ṣāliḥīna
Amharic ለእርሱም ኢስሐቅን ያዕቆብንም ተጨማሪ አድርገን ሰጠነው፡፡ ሁሉንም መልካሞች አደረግን፡፤
Verse 73
وَجَعَلْنَـٰهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا وَأَوْحَيْنَآ إِلَيْهِمْ فِعْلَ ٱلْخَيْرَٰتِ وَإِقَامَ ٱلصَّلَوٰةِ وَإِيتَآءَ ٱلزَّكَوٰةِ ۖ وَكَانُوا۟ لَنَا عَـٰبِدِينَ
Transliteration wajaʿalnāhum a-immatan yahdūna bi-amrinā wa-awḥaynā ilayhim fiʿ'la l-khayrāti wa-iqāma l-ṣalati waītāa l-zakati wakānū lanā ʿābidīna
Amharic በትዕዛዛችንም ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው፡፡ ወደእነሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን፡፡ ለእኛ ተገዢዎችም ነበሩ፡፡
Verse 74
وَلُوطًا ءَاتَيْنَـٰهُ حُكْمًا وَعِلْمًا وَنَجَّيْنَـٰهُ مِنَ ٱلْقَرْيَةِ ٱلَّتِى كَانَت تَّعْمَلُ ٱلْخَبَـٰٓئِثَ ۗ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمَ سَوْءٍ فَـٰسِقِينَ
Transliteration walūṭan ātaynāhu ḥuk'man waʿil'man wanajjaynāhu mina l-qaryati allatī kānat taʿmalu l-khabāitha innahum kānū qawma sawin fāsiqīna
Amharic ሉጥንም ፍርድንና ዕውቀትን ሰጠነው፡፡ ከዚያችም መጥፎ ሥራዎችን ትሠራ ከነበረችው ከተማ አዳንነው፡፡ እነሱ ክፉ ሰዎች አመጸኞች ነበሩና፡፡
Verse 75
وَأَدْخَلْنَـٰهُ فِى رَحْمَتِنَآ ۖ إِنَّهُۥ مِنَ ٱلصَّـٰلِحِينَ
Transliteration wa-adkhalnāhu fī raḥmatinā innahu mina l-ṣāliḥīna
Amharic በችሮታችንም ውስጥ አገባነው፡፡ እርሱ ከመልካሞቹ ነውና፡፡
Verse 76
وَنُوحًا إِذْ نَادَىٰ مِن قَبْلُ فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ فَنَجَّيْنَـٰهُ وَأَهْلَهُۥ مِنَ ٱلْكَرْبِ ٱلْعَظِيمِ
Transliteration wanūḥan idh nādā min qablu fa-is'tajabnā lahu fanajjaynāhu wa-ahlahu mina l-karbi l-ʿaẓīmi
Amharic ኑሕንም ከዚያ በፊት (ጌታውን) በጠራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ለእርሱም (ጥሪውን) ተቀበልነው፡፡ እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን፡፡
Verse 77
وَنَصَرْنَـٰهُ مِنَ ٱلْقَوْمِ ٱلَّذِينَ كَذَّبُوا۟ بِـَٔايَـٰتِنَآ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ قَوْمَ سَوْءٍ فَأَغْرَقْنَـٰهُمْ أَجْمَعِينَ
Transliteration wanaṣarnāhu mina l-qawmi alladhīna kadhabū biāyātinā innahum kānū qawma sawin fa-aghraqnāhum ajmaʿīna
Amharic ከነዚያም በታምራቶቻችን ከአስተባበሉት ሕዝቦች (ተንኮል) ጠበቅነው፡፡ እነሱ ክፉ ሕዝቦች አመጸኞች ነበሩና፡፡ ሁሉንም አሰጠምናቸውም፡፡
Verse 78
وَدَاوُۥدَ وَسُلَيْمَـٰنَ إِذْ يَحْكُمَانِ فِى ٱلْحَرْثِ إِذْ نَفَشَتْ فِيهِ غَنَمُ ٱلْقَوْمِ وَكُنَّا لِحُكْمِهِمْ شَـٰهِدِينَ
Transliteration wadāwūda wasulaymāna idh yaḥkumāni fī l-ḥarthi idh nafashat fīhi ghanamu l-qawmi wakunnā liḥuk'mihim shāhidīna
Amharic ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የሕዝቦቹ ፍየሎች ሌሊት በርሱ ውስጥ በተሰማሩ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ፍርዳቸውንም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡
Verse 79
فَفَهَّمْنَـٰهَا سُلَيْمَـٰنَ ۚ وَكُلًّا ءَاتَيْنَا حُكْمًا وَعِلْمًا ۚ وَسَخَّرْنَا مَعَ دَاوُۥدَ ٱلْجِبَالَ يُسَبِّحْنَ وَٱلطَّيْرَ ۚ وَكُنَّا فَـٰعِلِينَ
Transliteration fafahhamnāhā sulaymāna wakullan ātaynā ḥuk'man waʿil'man wasakharnā maʿa dāwūda l-jibāla yusabbiḥ'na wal-ṭayra wakunnā fāʿilīna
Amharic ለሱለይማንም (ትክክለኛይቱን ፍርድ) አሳወቅናት፡፡ ለሁሉም ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠን፡፡ ተራራዎችን ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲኾኑ ገራን፡፡ አእዋፍንም (እንደዚሁ ገራን)፡፡ ሠሪዎችም ነበርን፡፡
Verse 80
وَعَلَّمْنَـٰهُ صَنْعَةَ لَبُوسٍ لَّكُمْ لِتُحْصِنَكُم مِّنۢ بَأْسِكُمْ ۖ فَهَلْ أَنتُمْ شَـٰكِرُونَ
Transliteration waʿallamnāhu ṣanʿata labūsin lakum lituḥ'ṣinakum min basikum fahal antum shākirūna
Amharic የብረት ልብስንም ሥራ ለእናንተ ከጦራችሁ ትጠብቃችሁ ዘንድ አስተማርነው፡፡ እናንተ አመስጋኞች ናችሁን
Verse 81
وَلِسُلَيْمَـٰنَ ٱلرِّيحَ عَاصِفَةً تَجْرِى بِأَمْرِهِۦٓ إِلَى ٱلْأَرْضِ ٱلَّتِى بَـٰرَكْنَا فِيهَا ۚ وَكُنَّا بِكُلِّ شَىْءٍ عَـٰلِمِينَ
Transliteration walisulaymāna l-rīḥa ʿāṣifatan tajrī bi-amrihi ilā l-arḍi allatī bāraknā fīhā wakunnā bikulli shayin ʿālimīna
Amharic ለሱለይማንም ነፋስን በኀይል የምትነፍስ በትዕዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትፈስ ስትኾን (ገራንለት)፡፡ በነገሩ ሁሉም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡
Verse 82
وَمِنَ ٱلشَّيَـٰطِينِ مَن يَغُوصُونَ لَهُۥ وَيَعْمَلُونَ عَمَلًا دُونَ ذَٰلِكَ ۖ وَكُنَّا لَهُمْ حَـٰفِظِينَ
Transliteration wamina l-shayāṭīni man yaghūṣūna lahu wayaʿmalūna ʿamalan dūna dhālika wakunnā lahum ḥāfiẓīna
Amharic ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያም ሌላ ያለን ሥራ የሚሠሩን (ገራንለት)፡፡ ለእነሱም ተጠባባቂዎች ነበርን፡፡
Verse 83
۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ ٱلرَّٰحِمِينَ
Transliteration wa-ayyūba idh nādā rabbahu annī massaniya l-ḍuru wa-anta arḥamu l-rāḥimīna
Amharic አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
Verse 84
فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ فَكَشَفْنَا مَا بِهِۦ مِن ضُرٍّ ۖ وَءَاتَيْنَـٰهُ أَهْلَهُۥ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنْ عِندِنَا وَذِكْرَىٰ لِلْعَـٰبِدِينَ
Transliteration fa-is'tajabnā lahu fakashafnā mā bihi min ḍurrin waātaynāhu ahlahu wamith'lahum maʿahum raḥmatan min ʿindinā wadhik'rā lil'ʿābidīna
Amharic ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጉዳትም በእርሱ ላይ የነበረውን ሁሉ አስወገድን፡፡ ቤተሰቦቹንም ከእነሱም ጋር መሰላቸውን ከእኛ ዘንድ ለችሮታና ለተገዢዎች ለማስገንዘብ ሰጠነው፡፡
Verse 85
وَإِسْمَـٰعِيلَ وَإِدْرِيسَ وَذَا ٱلْكِفْلِ ۖ كُلٌّ مِّنَ ٱلصَّـٰبِرِينَ
Transliteration wa-is'māʿīla wa-id'rīsa wadhā l-kif'li kullun mina l-ṣābirīna
Amharic ኢስማዒልንም ኢድሪስንም ዙልኪፍልንም (አስታውስ)፡፡ ሁሉም ከታጋሾቹ ናቸው፡፡
Verse 86
وَأَدْخَلْنَـٰهُمْ فِى رَحْمَتِنَآ ۖ إِنَّهُم مِّنَ ٱلصَّـٰلِحِينَ
Transliteration wa-adkhalnāhum fī raḥmatinā innahum mina l-ṣāliḥīna
Amharic ከችሮታችንም ውስጥ አገባናቸው፡፡ እነሱ ከመልካሞቹ ናቸውና፡፡
Verse 87
وَذَا ٱلنُّونِ إِذ ذَّهَبَ مُغَـٰضِبًا فَظَنَّ أَن لَّن نَّقْدِرَ عَلَيْهِ فَنَادَىٰ فِى ٱلظُّلُمَـٰتِ أَن لَّآ إِلَـٰهَ إِلَّآ أَنتَ سُبْحَـٰنَكَ إِنِّى كُنتُ مِنَ ٱلظَّـٰلِمِينَ
Transliteration wadhā l-nūni idh dhahaba mughāḍiban faẓanna an lan naqdira ʿalayhi fanādā fī l-ẓulumāti an lā ilāha illā anta sub'ḥānaka innī kuntu mina l-ẓālimīna
Amharic የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡
Verse 88
فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ وَنَجَّيْنَـٰهُ مِنَ ٱلْغَمِّ ۚ وَكَذَٰلِكَ نُـۨجِى ٱلْمُؤْمِنِينَ
Transliteration fa-is'tajabnā lahu wanajjaynāhu mina l-ghami wakadhālika nunjī l-mu'minīna
Amharic ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡
Verse 89
وَزَكَرِيَّآ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرْنِى فَرْدًا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْوَٰرِثِينَ
Transliteration wazakariyyā idh nādā rabbahu rabbi lā tadharnī fardan wa-anta khayru l-wārithīna
Amharic ዘከሪያንም «ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ ሲል» ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
Verse 90
فَٱسْتَجَبْنَا لَهُۥ وَوَهَبْنَا لَهُۥ يَحْيَىٰ وَأَصْلَحْنَا لَهُۥ زَوْجَهُۥٓ ۚ إِنَّهُمْ كَانُوا۟ يُسَـٰرِعُونَ فِى ٱلْخَيْرَٰتِ وَيَدْعُونَنَا رَغَبًا وَرَهَبًا ۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَـٰشِعِينَ
Transliteration fa-is'tajabnā lahu wawahabnā lahu yaḥyā wa-aṣlaḥnā lahu zawjahu innahum kānū yusāriʿūna fī l-khayrāti wayadʿūnanā raghaban warahaban wakānū lanā khāshiʿīna
Amharic ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ለእርሱም የሕያን ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ኾነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡
Verse 91
وَٱلَّتِىٓ أَحْصَنَتْ فَرْجَهَا فَنَفَخْنَا فِيهَا مِن رُّوحِنَا وَجَعَلْنَـٰهَا وَٱبْنَهَآ ءَايَةً لِّلْعَـٰلَمِينَ
Transliteration wa-allatī aḥṣanat farjahā fanafakhnā fīhā min rūḥinā wajaʿalnāhā wa-ib'nahā āyatan lil'ʿālamīna
Amharic ያችንም ብልቷን የጠበቀቺውን በርሷም ውስጥ ከመንፈሳችን የነፋንባትን እርሷንም ልጅዋንም (እንደዚሁ) ለዓለማት ተዓምር ያደረግናትን (መርየምን አስታውስ)፡፡
Verse 92
إِنَّ هَـٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَٰحِدَةً وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
Transliteration inna hādhihi ummatukum ummatan wāḥidatan wa-anā rabbukum fa-uʿ'budūni
Amharic ይህች (ሕግጋት) አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፡፡ እኔም ጌታችሁ ነኝና ተገዙኝ፡፡
Verse 93
وَتَقَطَّعُوٓا۟ أَمْرَهُم بَيْنَهُمْ ۖ كُلٌّ إِلَيْنَا رَٰجِعُونَ
Transliteration wataqaṭṭaʿū amrahum baynahum kullun ilaynā rājiʿūna
Amharic በሃይማኖታቸውም ነገር በመካከላቸው ተለያዩ፡፡ ሁሉም ወደኛ ተመላሾች ናቸው፡፡
Verse 94
فَمَن يَعْمَلْ مِنَ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا كُفْرَانَ لِسَعْيِهِۦ وَإِنَّا لَهُۥ كَـٰتِبُونَ
Transliteration faman yaʿmal mina l-ṣāliḥāti wahuwa mu'minun falā kuf'rāna lisaʿyihi wa-innā lahu kātibūna
Amharic እርሱ ያመነ ኾኖ ከበጎ ሥራዎች ማንኛውንም የሚሠራም ሰው፤ ምንዳውን አይነፈግም፡፡ እኛም ለእርሱ መዝጋቢዎች ነን፡፡
Verse 95
وَحَرَٰمٌ عَلَىٰ قَرْيَةٍ أَهْلَكْنَـٰهَآ أَنَّهُمْ لَا يَرْجِعُونَ
Transliteration waḥarāmun ʿalā qaryatin ahlaknāhā annahum lā yarjiʿūna
Amharic ባጠፋናትም ከተማ ላይ እነሱ (ወደኛ) የማይመለሱ መኾናቸው እብለት ነው፤ (ይመለሳሉ)፡፡
Verse 96
حَتَّىٰٓ إِذَا فُتِحَتْ يَأْجُوجُ وَمَأْجُوجُ وَهُم مِّن كُلِّ حَدَبٍ يَنسِلُونَ
Transliteration ḥattā idhā futiḥat yajūju wamajūju wahum min kulli ḥadabin yansilūna
Amharic የእጁጅና መእጁጅም እነርሱ ከየተረተሩ የሚንደረደሩ ሲኾኑ (ግድባቸው) በተከፈተች ጊዜ፥
Verse 97
وَٱقْتَرَبَ ٱلْوَعْدُ ٱلْحَقُّ فَإِذَا هِىَ شَـٰخِصَةٌ أَبْصَـٰرُ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ يَـٰوَيْلَنَا قَدْ كُنَّا فِى غَفْلَةٍ مِّنْ هَـٰذَا بَلْ كُنَّا ظَـٰلِمِينَ
Transliteration wa-iq'taraba l-waʿdu l-ḥaqu fa-idhā hiya shākhiṣatun abṣāru alladhīna kafarū yāwaylanā qad kunnā fī ghaflatin min hādhā bal kunnā ẓālimīna
Amharic እውነተኛውም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ፥ ያን ጊዜ እነሆ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ዓይኖች ይፈጥጣሉ፡፡ «ዋ ጥፋታችን! ከዚህ (ቀን) በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን፤ በእውነትም በዳዮች ነበርን» (ይላሉ)፡፡
Verse 98
إِنَّكُمْ وَمَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ حَصَبُ جَهَنَّمَ أَنتُمْ لَهَا وَٰرِدُونَ
Transliteration innakum wamā taʿbudūna min dūni l-lahi ḥaṣabu jahannama antum lahā wāridūna
Amharic እናንተ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውም (ጣዖታት) የገሀነም ማገዶዎች ናችሁ፡፡ እናንተ ለእርሷ ወራጆች ናችሁ፡፡
Verse 99
لَوْ كَانَ هَـٰٓؤُلَآءِ ءَالِهَةً مَّا وَرَدُوهَا ۖ وَكُلٌّ فِيهَا خَـٰلِدُونَ
Transliteration law kāna hāulāi ālihatan mā waradūhā wakullun fīhā khālidūna
Amharic እነዚህ (ጣዖታት) አማልክት በነበሩ ኖሮ አይገቧዋትም ነበር፡፡ ግን ሁሉም በእርሷ ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
Verse 100
لَهُمْ فِيهَا زَفِيرٌ وَهُمْ فِيهَا لَا يَسْمَعُونَ
Transliteration lahum fīhā zafīrun wahum fīhā lā yasmaʿūna
Amharic ለእነርሱ በእርሷ ውስጥ መንሰቅሰቅ አላቸው፡፡ እነርሱም በውስጧ (ምንንም) አይሰሙም፡፡
Verse 101
إِنَّ ٱلَّذِينَ سَبَقَتْ لَهُم مِّنَّا ٱلْحُسْنَىٰٓ أُو۟لَـٰٓئِكَ عَنْهَا مُبْعَدُونَ
Transliteration inna alladhīna sabaqat lahum minnā l-ḥus'nā ulāika ʿanhā mub'ʿadūna
Amharic እነዚያ ከእኛ መልካሟ ቃል ለእነርሱ ያለፈችላቸው እነዚያ ከርሷ የተራቁ ናቸው፡፡
Verse 102
لَا يَسْمَعُونَ حَسِيسَهَا ۖ وَهُمْ فِى مَا ٱشْتَهَتْ أَنفُسُهُمْ خَـٰلِدُونَ
Transliteration lā yasmaʿūna ḥasīsahā wahum fī mā ish'tahat anfusuhum khālidūna
Amharic ድምጽዋን አይሰሙም፡፡ እነርሱም ነፍሶቻቸው በሚሹት ነገር ውስጥ ዘውታሪዎች ናቸው፡፡
Verse 103
لَا يَحْزُنُهُمُ ٱلْفَزَعُ ٱلْأَكْبَرُ وَتَتَلَقَّىٰهُمُ ٱلْمَلَـٰٓئِكَةُ هَـٰذَا يَوْمُكُمُ ٱلَّذِى كُنتُمْ تُوعَدُونَ
Transliteration lā yaḥzunuhumu l-fazaʿu l-akbaru watatalaqqāhumu l-malāikatu hādhā yawmukumu alladhī kuntum tūʿadūna
Amharic ታላቁ ድንጋጤ አያስተክዛቸውም፡፡ መላእክትም ይህ ያ ትቀጠሩ የነበራችሁት ቀናችሁ ነው፤ እያሉ ይቀበሏቸዋል፡፡
Verse 104
يَوْمَ نَطْوِى ٱلسَّمَآءَ كَطَىِّ ٱلسِّجِلِّ لِلْكُتُبِ ۚ كَمَا بَدَأْنَآ أَوَّلَ خَلْقٍ نُّعِيدُهُۥ ۚ وَعْدًا عَلَيْنَآ ۚ إِنَّا كُنَّا فَـٰعِلِينَ
Transliteration yawma naṭwī l-samāa kaṭayyi l-sijili lil'kutubi kamā badanā awwala khalqin nuʿīduhu waʿdan ʿalaynā innā kunnā fāʿilīna
Amharic ለመጽሐፎች የኾኑ ገጾች እንደሚጠቀለሉ ሰማይን የምንጠቀልልበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ የመጀመሪያን ፍጥረት እንደ ጀመርን እንመልሰዋለን፡፡ (መፈጸሙ) በእኛ ላይ የኾነን ቀጠሮ ቀጠርን፡፡ እኛ (የቀጠርነውን) ሠሪዎች ነን፡፡
Verse 105
وَلَقَدْ كَتَبْنَا فِى ٱلزَّبُورِ مِنۢ بَعْدِ ٱلذِّكْرِ أَنَّ ٱلْأَرْضَ يَرِثُهَا عِبَادِىَ ٱلصَّـٰلِحُونَ
Transliteration walaqad katabnā fī l-zabūri min baʿdi l-dhik'ri anna l-arḍa yarithuhā ʿibādiya l-ṣāliḥūna
Amharic ምድንም መልካሞቹ ባሮቼ ይወርሷታል ማለትን ከመጽሐፉ (ከተጠበቀው ሰሌዳ) በኋላ በመጽሐፎቹ በእርግጥ ጽፈናል፡፡
Verse 106
إِنَّ فِى هَـٰذَا لَبَلَـٰغًا لِّقَوْمٍ عَـٰبِدِينَ
Transliteration inna fī hādhā labalāghan liqawmin ʿābidīna
Amharic በዚህ (ቁርኣን) ውስጥ ለተገዢዎች ሕዝቦች በቂነት አልለ፡፡
Verse 107
وَمَآ أَرْسَلْنَـٰكَ إِلَّا رَحْمَةً لِّلْعَـٰلَمِينَ
Transliteration wamā arsalnāka illā raḥmatan lil'ʿālamīna
Amharic (ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም፡፡
Verse 108
قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَٰحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
Transliteration qul innamā yūḥā ilayya annamā ilāhukum ilāhun wāḥidun fahal antum mus'limūna
Amharic «ያ ወደኔ የሚወረደው አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን» በላቸው፡፡
Verse 109
فَإِن تَوَلَّوْا۟ فَقُلْ ءَاذَنتُكُمْ عَلَىٰ سَوَآءٍ ۖ وَإِنْ أَدْرِىٓ أَقَرِيبٌ أَم بَعِيدٌ مَّا تُوعَدُونَ
Transliteration fa-in tawallaw faqul ādhantukum ʿalā sawāin wa-in adrī aqarībun am baʿīdun mā tūʿadūna
Amharic እምቢም ቢሉ (በማወቅ) በእኩልነት ላይ ኾነን (የታዘዝኩትን) አስታውቅኋችሁ፡፡ «የምትስፈራሩበትም ነገር ቅርብ ወይም ሩቅ መኾኑን አላውቅም፤» በላቸው፡፡
Verse 110
إِنَّهُۥ يَعْلَمُ ٱلْجَهْرَ مِنَ ٱلْقَوْلِ وَيَعْلَمُ مَا تَكْتُمُونَ
Transliteration innahu yaʿlamu l-jahra mina l-qawli wayaʿlamu mā taktumūna
Amharic እርሱ ከንግግር ጩኸትን ያውቃል፡፡ የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል፡፡
Verse 111
وَإِنْ أَدْرِى لَعَلَّهُۥ فِتْنَةٌ لَّكُمْ وَمَتَـٰعٌ إِلَىٰ حِينٍ
Transliteration wa-in adrī laʿallahu fit'natun lakum wamatāʿun ilā ḥīnin
Amharic እርሱም (ቅጣትን ማቆየት) ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጠቃቀሚያ እንደሆነም አላውቅም፤ (በላቸው)፡፡
Verse 112
قَـٰلَ رَبِّ ٱحْكُم بِٱلْحَقِّ ۗ وَرَبُّنَا ٱلرَّحْمَـٰنُ ٱلْمُسْتَعَانُ عَلَىٰ مَا تَصِفُونَ
Transliteration qāla rabbi uḥ'kum bil-ḥaqi warabbunā l-raḥmānu l-mus'taʿānu ʿalā mā taṣifūna
Amharic «ጌታዬ ሆይ! በእውነት ፍረድ፤ ጌታችንም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በምትሉት ነገር ላይ መታገዣ ነው» አለ፡፡
Read Surah Al-Anbya in another language
- English (word by word)
- Albanian
- Amazigh
- Assamese
- Azerbaijani
- Bambara
- Bangla
- Bosnian
- Bulgarian
- Chechen
- Chinese
- Czech
- Dari
- Dhivehi
- Dutch
- Finnish
- French
- German
- Gujarati
- Hausa
- Hebrew
- Hindi
- Indonesian
- Italian
- Japanese
- Kannada
- Kazakh
- Khmer
- Kinyarwanda
- Korean
- Kurdish
- Luganda
- Malay
- Malayalam
- Maranao
- Marathi
- Nepali
- Norwegian
- Oromo
- Pashto
- Persian
- Polish
- Portuguese
- Romanian
- Russian
- Sindhi
- Sinhala
- Somali
- Spanish
- Swahili
- Swedish
- Tagalog
- Tajik
- Tamil
- Tatar
- Telugu
- Thai
- Turkish
- Ukrainian
- Urdu
- Uyghur
- Uzbek
- Vietnamese
- Yao
- Yoruba
All 114 surahs in Amharic: the Qur’an in Amharic.
Amharic translation: Sadiq and Sani, from Quran.com. Transliteration: Quran.com. Recitation: Mishary Alafasy, from EveryAyah.com. MyDugsi is a learning aid, not a replacement for a qualified teacher.