MyDugsiStart learning

Surah Al-Jathiyah in Amharic: translation and audio

Surah 45 · الجاثية · The Crouching · 37 verses

Surah Al-Jathiyah verse by verse: the Arabic with a recitation you can repeat, the transliteration, and the Amharic translation by Sadiq and Sani. For the meaning of every word, see Surah Al-Jathiyah word by word in English.

Verse 1

حمٓ

Transliteration hha-meem

Amharic ሐ.መ (ሓ ሚም)፡፡

Verse 2

تَنزِيلُ ٱلْكِتَـٰبِ مِنَ ٱللَّهِ ٱلْعَزِيزِ ٱلْحَكِيمِ

Transliteration tanzīlu l-kitābi mina l-lahi l-ʿazīzi l-ḥakīmi

Amharic የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊ ጥበበኛ ከኾነው አላህ ነው፡፡

Verse 3

إِنَّ فِى ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ لَـَٔايَـٰتٍ لِّلْمُؤْمِنِينَ

Transliteration inna fī l-samāwāti wal-arḍi laāyātin lil'mu'minīna

Amharic በሰማያትና በምድር ውስጥ ለምእምናን ሁሉ (ለችሎታው) እርገጠኛ ምልክቶች አልሉ፡፡

Verse 4

وَفِى خَلْقِكُمْ وَمَا يَبُثُّ مِن دَآبَّةٍ ءَايَـٰتٌ لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ

Transliteration wafī khalqikum wamā yabuthu min dābbatin āyātun liqawmin yūqinūna

Amharic እናንተንም በመፍጠር ከተንቀሳቃሽም (በምድር ላይ) የሚበትነውን ሁሉ (በመፍጠሩ) ለሚያረጋግጡ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡

Verse 5

وَٱخْتِلَـٰفِ ٱلَّيْلِ وَٱلنَّهَارِ وَمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلسَّمَآءِ مِن رِّزْقٍ فَأَحْيَا بِهِ ٱلْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا وَتَصْرِيفِ ٱلرِّيَـٰحِ ءَايَـٰتٌ لِّقَوْمٍ يَعْقِلُونَ

Transliteration wa-ikh'tilāfi al-layli wal-nahāri wamā anzala l-lahu mina l-samāi min riz'qin fa-aḥyā bihi l-arḍa baʿda mawtihā wataṣrīfi l-riyāḥi āyātun liqawmin yaʿqilūna

Amharic በሌሊትና መዓልት መተካካትም፣ ከሲሳይም (ከዝናም) አላህ ከሰማይ ባወረደው በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው በማድረጉ፣ ነፋሶችንም (በያቅጣጫቸው) በማዘዋወሩ ለሚያውቁ ሕዝቦች ማስረጃዎች አልሉ፡፡

Verse 6

تِلْكَ ءَايَـٰتُ ٱللَّهِ نَتْلُوهَا عَلَيْكَ بِٱلْحَقِّ ۖ فَبِأَىِّ حَدِيثٍۭ بَعْدَ ٱللَّهِ وَءَايَـٰتِهِۦ يُؤْمِنُونَ

Transliteration til'ka āyātu l-lahi natlūhā ʿalayka bil-ḥaqi fabi-ayyi ḥadīthin baʿda l-lahi waāyātihi yu'minūna

Amharic እነዚህ ባንተ ላይ በውነት የምናነባቸው ሲኾኑ የአላህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከአላህና ከማስረጃዎቹም ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?

Verse 7

وَيْلٌ لِّكُلِّ أَفَّاكٍ أَثِيمٍ

Transliteration waylun likulli affākin athīmin

Amharic ውሸታም ኀጢአተኛ ለኾነ ሁሉ ወዮለት፡፡ (ጥፋት ተገባው)፡፡

Verse 8

يَسْمَعُ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ تُتْلَىٰ عَلَيْهِ ثُمَّ يُصِرُّ مُسْتَكْبِرًا كَأَن لَّمْ يَسْمَعْهَا ۖ فَبَشِّرْهُ بِعَذَابٍ أَلِيمٍ

Transliteration yasmaʿu āyāti l-lahi tut'lā ʿalayhi thumma yuṣirru mus'takbiran ka-an lam yasmaʿhā fabashir'hu biʿadhābin alīmin

Amharic የአላህን አንቀጾች በእርሱ ላይ የሚነበቡለት ሲኾኑ ይሰማል፡፡ ከዚያም የኮራ ሲኾን እንዳልሰማት ኾኖ (በክሕደቱ ላይ) ይዘወትራል፡፡ በአሳማሚም ቅጣት አብስረው፡፡

Verse 9

وَإِذَا عَلِمَ مِنْ ءَايَـٰتِنَا شَيْـًٔا ٱتَّخَذَهَا هُزُوًا ۚ أُو۟لَـٰٓئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

Transliteration wa-idhā ʿalima min āyātinā shayan ittakhadhahā huzuwan ulāika lahum ʿadhābun muhīnun

Amharic ከአንቀጾቻችንም አንዳችን ባወቀ ጊዜ መሳለቂያ አድርጎ ይይዛታል፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አልላቸው፡፡

Verse 10

مِّن وَرَآئِهِمْ جَهَنَّمُ ۖ وَلَا يُغْنِى عَنْهُم مَّا كَسَبُوا۟ شَيْـًٔا وَلَا مَا ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوْلِيَآءَ ۖ وَلَهُمْ عَذَابٌ عَظِيمٌ

Transliteration min warāihim jahannamu walā yugh'nī ʿanhum mā kasabū shayan walā mā ittakhadhū min dūni l-lahi awliyāa walahum ʿadhābun ʿaẓīmun

Amharic ከፊታቸውም ገሀነም አልለች፡፡ የሰበሰቡትም ሀብት ከእነርሱ ላይ ምንንም አይመልስላቸውም፡፡ ከአላህ ሌላም ረዳቶች አድርገው የያዙዋቸው (አይጠቅሟቸውም)፡፡ ለእነርሱም ታላቅ ቅጣት አልላቸው፡፡

Verse 11

هَـٰذَا هُدًى ۖ وَٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَـٰتِ رَبِّهِمْ لَهُمْ عَذَابٌ مِّن رِّجْزٍ أَلِيمٌ

Transliteration hādhā hudan wa-alladhīna kafarū biāyāti rabbihim lahum ʿadhābun min rij'zin alīmun

Amharic ይህ (ቁርኣን) መሪ ነው፡፡ እነዚያም በጌታቸው አንቀጾች የካዱት ለእነርሱ ከብርቱ ቅጣት የኾነ አሳማሚ ስቃይ አልላቸው፡፡

Verse 12

۞ ٱللَّهُ ٱلَّذِى سَخَّرَ لَكُمُ ٱلْبَحْرَ لِتَجْرِىَ ٱلْفُلْكُ فِيهِ بِأَمْرِهِۦ وَلِتَبْتَغُوا۟ مِن فَضْلِهِۦ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

Transliteration al-lahu alladhī sakhara lakumu l-baḥra litajriya l-ful'ku fīhi bi-amrihi walitabtaghū min faḍlihi walaʿallakum tashkurūna

Amharic አላህ ያ ባሕርን በውስጡ ታንኳዎች በፈቃዱ እንዲንሻለሉበት ከችሮታውም እንድትፈልጉበት እንድታመሰግኑትም ለእናነተ የገራላችሁ ነው፡፡

Verse 13

وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِى ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَمَا فِى ٱلْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ ۚ إِنَّ فِى ذَٰلِكَ لَـَٔايَـٰتٍ لِّقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

Transliteration wasakhara lakum mā fī l-samāwāti wamā fī l-arḍi jamīʿan min'hu inna fī dhālika laāyātin liqawmin yatafakkarūna

Amharic ለናንተም በሰማያት ያለውንና በምድርም ያለውን ሁሉ በመላ ከእርሱ ሲኾን የገራላችሁ ነው፡፡ በዚህ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ተዓምራት አልለበት፡፡

Verse 14

قُل لِّلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ يَغْفِرُوا۟ لِلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ أَيَّامَ ٱللَّهِ لِيَجْزِىَ قَوْمًۢا بِمَا كَانُوا۟ يَكْسِبُونَ

Transliteration qul lilladhīna āmanū yaghfirū lilladhīna lā yarjūna ayyāma l-lahi liyajziya qawman bimā kānū yaksibūna

Amharic ለእነዚያ ለአመኑት ሰዎች (ምሕረት አድርጉ) በላቸው፡፡ ለእነዚያ የአላህን ቀኖች ለማይፈሩት ይምራሉና፡፡ ሕዝቦችን ይሠሩት በነበሩት ነገር ይመነዳ ዘንድ (ምሕረት አድርጉ በላቸው)፡፡

Verse 15

مَنْ عَمِلَ صَـٰلِحًا فَلِنَفْسِهِۦ ۖ وَمَنْ أَسَآءَ فَعَلَيْهَا ۖ ثُمَّ إِلَىٰ رَبِّكُمْ تُرْجَعُونَ

Transliteration man ʿamila ṣāliḥan falinafsihi waman asāa faʿalayhā thumma ilā rabbikum tur'jaʿūna

Amharic መልካምን የሠራ ሰው ለነፍሱ ነው፡፡ ያከፋም ሰው በእርሷ ላይ ነው፡፡ ከዚያም ወደ ጌታችሁ

Verse 16

وَلَقَدْ ءَاتَيْنَا بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ ٱلْكِتَـٰبَ وَٱلْحُكْمَ وَٱلنُّبُوَّةَ وَرَزَقْنَـٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَـٰتِ وَفَضَّلْنَـٰهُمْ عَلَى ٱلْعَـٰلَمِينَ

Transliteration walaqad ātaynā banī is'rāīla l-kitāba wal-ḥuk'ma wal-nubuwata warazaqnāhum mina l-ṭayibāti wafaḍḍalnāhum ʿalā l-ʿālamīna

Amharic ለእስራኤል ልጆችም መጽሐፍንና ሕግን፣ ነቢይነትንም በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡ ከመልካም ሲሳዮችም ለገስንላቸው፡፡ በዓለማት ላይም አበለጥናቸው፡፡

Verse 17

وَءَاتَيْنَـٰهُم بَيِّنَـٰتٍ مِّنَ ٱلْأَمْرِ ۖ فَمَا ٱخْتَلَفُوٓا۟ إِلَّا مِنۢ بَعْدِ مَا جَآءَهُمُ ٱلْعِلْمُ بَغْيًۢا بَيْنَهُمْ ۚ إِنَّ رَبَّكَ يَقْضِى بَيْنَهُمْ يَوْمَ ٱلْقِيَـٰمَةِ فِيمَا كَانُوا۟ فِيهِ يَخْتَلِفُونَ

Transliteration waātaynāhum bayyinātin mina l-amri famā ikh'talafū illā min baʿdi mā jāahumu l-ʿil'mu baghyan baynahum inna rabbaka yaqḍī baynahum yawma l-qiyāmati fīmā kānū fīhi yakhtalifūna

Amharic ከትዕዛዝም ግልጾችን ሰጠናቸው፡፡ ዕውቀቱም ከመጣላቸው በኋላ በመካከላቸው ለምቀኝነት እንጅ ለሌላ አልተለያዩም፡፡ ጌታህ በትንሣኤ ቀን በዚያ በእርሱ ይለያዩበት በነበሩት ነገር በመካከላቸው በእርግጥ ይፈርዳል፡፡

Verse 18

ثُمَّ جَعَلْنَـٰكَ عَلَىٰ شَرِيعَةٍ مِّنَ ٱلْأَمْرِ فَٱتَّبِعْهَا وَلَا تَتَّبِعْ أَهْوَآءَ ٱلَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ

Transliteration thumma jaʿalnāka ʿalā sharīʿatin mina l-amri fa-ittabiʿ'hā walā tattabiʿ ahwāa alladhīna lā yaʿlamūna

Amharic ከዚያም ከነገሩ (ከሃይማኖት) በትክክለኛይቱ ሕግ ላይ አደረግንህ፡፡ ስለዚህ ተከተላት፡፡ የእነዚያንም የማያውቁትን ሕዝቦች ዝንባሌዎች አትከተል፡፡

Verse 19

إِنَّهُمْ لَن يُغْنُوا۟ عَنكَ مِنَ ٱللَّهِ شَيْـًٔا ۚ وَإِنَّ ٱلظَّـٰلِمِينَ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَآءُ بَعْضٍ ۖ وَٱللَّهُ وَلِىُّ ٱلْمُتَّقِينَ

Transliteration innahum lan yugh'nū ʿanka mina l-lahi shayan wa-inna l-ẓālimīna baʿḍuhum awliyāu baʿḍin wal-lahu waliyyu l-mutaqīna

Amharic እነርሱ ከአላህ (ቅጣት) ምንንም ከአንተ አይገፈትሩልህምና፡፡ በደለኞም ከፊላቸው የከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ አላህም የጥንቁቆቹ ረዳት ነው፡፡

Verse 20

هَـٰذَا بَصَـٰٓئِرُ لِلنَّاسِ وَهُدًى وَرَحْمَةٌ لِّقَوْمٍ يُوقِنُونَ

Transliteration hādhā baṣāiru lilnnāsi wahudan waraḥmatun liqawmin yūqinūna

Amharic ይሀ (ቁርኣን) ለሰዎች የልብ ብርሃኖች ነው፡፡ ለሚያረጋግጡም ሕዝቦች መሪና እዝነት ነው፡፡

Verse 21

أَمْ حَسِبَ ٱلَّذِينَ ٱجْتَرَحُوا۟ ٱلسَّيِّـَٔاتِ أَن نَّجْعَلَهُمْ كَٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ سَوَآءً مَّحْيَاهُمْ وَمَمَاتُهُمْ ۚ سَآءَ مَا يَحْكُمُونَ

Transliteration am ḥasiba alladhīna ij'taraḥū l-sayiāti an najʿalahum ka-alladhīna āmanū waʿamilū l-ṣāliḥāti sawāan maḥyāhum wamamātuhum sāa mā yaḥkumūna

Amharic እነዚያ ኀጢአቶችን የሠሩ ሕይወታቸውም ሞታቸውም ትክክል ሲኾን እንደእነዚያ እንደ አመኑትና መልካሞችን እንደሠሩት ልናደርጋቸው ይጠረጥራሉን? (አይጠርጥሩ)፡፡ የሚፈርዱት ምንኛ ከፋ!

Verse 22

وَخَلَقَ ٱللَّهُ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ بِٱلْحَقِّ وَلِتُجْزَىٰ كُلُّ نَفْسٍۭ بِمَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ

Transliteration wakhalaqa l-lahu l-samāwāti wal-arḍa bil-ḥaqi walituj'zā kullu nafsin bimā kasabat wahum lā yuẓ'lamūna

Amharic አላህም ሰማያትንና ምድርን (ለችሎታው እንደሚያመለክትባቸውና) ነፍስም ሁሉ በሠራችው ሥራ ትምመነዳ ዘንድ በትክክል ፈጠረ፡፡ እነርሱም አይበደሉም፡፡

Verse 23

أَفَرَءَيْتَ مَنِ ٱتَّخَذَ إِلَـٰهَهُۥ هَوَىٰهُ وَأَضَلَّهُ ٱللَّهُ عَلَىٰ عِلْمٍ وَخَتَمَ عَلَىٰ سَمْعِهِۦ وَقَلْبِهِۦ وَجَعَلَ عَلَىٰ بَصَرِهِۦ غِشَـٰوَةً فَمَن يَهْدِيهِ مِنۢ بَعْدِ ٱللَّهِ ۚ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ

Transliteration afara-ayta mani ittakhadha ilāhahu hawāhu wa-aḍallahu l-lahu ʿalā ʿil'min wakhatama ʿalā samʿihi waqalbihi wajaʿala ʿalā baṣarihi ghishāwatan faman yahdīhi min baʿdi l-lahi afalā tadhakkarūna

Amharic ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን፣ አላህም ከዕውቀት ጋር ያጠመመውን፣ በጆሮውና በልቡ ላይም ያተመበትን፣ በዓይኑም ላይ ሺፋን ያደረገበትን ሰው አየህን! ታዲያ ከአላህ በኋላ የሚያቀናው ማነው? አትገሠጹምን?

Verse 24

وَقَالُوا۟ مَا هِىَ إِلَّا حَيَاتُنَا ٱلدُّنْيَا نَمُوتُ وَنَحْيَا وَمَا يُهْلِكُنَآ إِلَّا ٱلدَّهْرُ ۚ وَمَا لَهُم بِذَٰلِكَ مِنْ عِلْمٍ ۖ إِنْ هُمْ إِلَّا يَظُنُّونَ

Transliteration waqālū mā hiya illā ḥayātunā l-dun'yā namūtu wanaḥyā wamā yuh'likunā illā l-dahru wamā lahum bidhālika min ʿil'min in hum illā yaẓunnūna

Amharic እርሷም (ሕይወት) የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡ «እንሞታለን፤ ሕያውም እንኾናለን፡፡ ከጊዜም (ማለፍ) በስተቀር ሌላ አያጠፋንም» አሉ፡፡ ለእነርሱም በዚህ (በሚሉት) ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ እነርሱ የሚጠራጠሩ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡

Verse 25

وَإِذَا تُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ ءَايَـٰتُنَا بَيِّنَـٰتٍ مَّا كَانَ حُجَّتَهُمْ إِلَّآ أَن قَالُوا۟ ٱئْتُوا۟ بِـَٔابَآئِنَآ إِن كُنتُمْ صَـٰدِقِينَ

Transliteration wa-idhā tut'lā ʿalayhim āyātunā bayyinātin mā kāna ḥujjatahum illā an qālū i'tū biābāinā in kuntum ṣādiqīna

Amharic አንቀጾቻችንም ግልጾች ኾነው በእነርሱ ላይ በተነበቡላቸው ጊዜ ክርክራቸው «እውነተኞች እንደ ኾናችሁ አባቶቻችንን አምጡ» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡

Verse 26

قُلِ ٱللَّهُ يُحْيِيكُمْ ثُمَّ يُمِيتُكُمْ ثُمَّ يَجْمَعُكُمْ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْقِيَـٰمَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَلَـٰكِنَّ أَكْثَرَ ٱلنَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

Transliteration quli l-lahu yuḥ'yīkum thumma yumītukum thumma yajmaʿukum ilā yawmi l-qiyāmati lā rayba fīhi walākinna akthara l-nāsi lā yaʿlamūna

Amharic «አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፤ ከዚያም ይገድላችኋል፣ ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፡፡ በእርሱ ጥርጥር የለበትም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም» በላቸው፡፡

Verse 27

وَلِلَّهِ مُلْكُ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۚ وَيَوْمَ تَقُومُ ٱلسَّاعَةُ يَوْمَئِذٍ يَخْسَرُ ٱلْمُبْطِلُونَ

Transliteration walillahi mul'ku l-samāwāti wal-arḍi wayawma taqūmu l-sāʿatu yawma-idhin yakhsaru l-mub'ṭilūna

Amharic የሰማያትና የምድር ግዛት የአላህ ብቻ ነው፡፡ ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን ያን ጊዜ አጥፊዎች ሁሉ ይከስራሉ፡፡

Verse 28

وَتَرَىٰ كُلَّ أُمَّةٍ جَاثِيَةً ۚ كُلُّ أُمَّةٍ تُدْعَىٰٓ إِلَىٰ كِتَـٰبِهَا ٱلْيَوْمَ تُجْزَوْنَ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Transliteration watarā kulla ummatin jāthiyatan kullu ummatin tud'ʿā ilā kitābihā l-yawma tuj'zawna mā kuntum taʿmalūna

Amharic ሕዝብንም ሁሉ ተንበርካኪ ኾና ታያታለህ፡፡ ሕዝብ ሁሉ ወደ መጽሐፏ ትጥጠራለች፡፡ «ዛሬ ትሠሩት የነበራችሁትን ነገር ትመነዳላችሁ» (ይባላሉ)፡፡

Verse 29

هَـٰذَا كِتَـٰبُنَا يَنطِقُ عَلَيْكُم بِٱلْحَقِّ ۚ إِنَّا كُنَّا نَسْتَنسِخُ مَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

Transliteration hādhā kitābunā yanṭiqu ʿalaykum bil-ḥaqi innā kunnā nastansikhu mā kuntum taʿmalūna

Amharic ይህ መጽሐፋችን ነው፡፡ በእናንተ ላይ በእውነት ይናገራል፡፡ እኛ ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን እናስገለብጥ ነበርን (ይባላሉ)፡፡

Verse 30

فَأَمَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ فَيُدْخِلُهُمْ رَبُّهُمْ فِى رَحْمَتِهِۦ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ ٱلْفَوْزُ ٱلْمُبِينُ

Transliteration fa-ammā alladhīna āmanū waʿamilū l-ṣāliḥāti fayud'khiluhum rabbuhum fī raḥmatihi dhālika huwa l-fawzu l-mubīnu

Amharic እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩትማ ጌታቸው በእዝነቱ ውስጥ ያገባቸዋል፡፡ ይህ እርሱ ግልጽ የኾነ ማግኘት ነው፡፡

Verse 31

وَأَمَّا ٱلَّذِينَ كَفَرُوٓا۟ أَفَلَمْ تَكُنْ ءَايَـٰتِى تُتْلَىٰ عَلَيْكُمْ فَٱسْتَكْبَرْتُمْ وَكُنتُمْ قَوْمًا مُّجْرِمِينَ

Transliteration wa-ammā alladhīna kafarū afalam takun āyātī tut'lā ʿalaykum fa-is'takbartum wakuntum qawman muj'rimīna

Amharic እነዚያም የካዱትማ (ለእነርሱ ይባላሉ) «አንቀጾቼ በእናንተ ላይ ይነበቡ አልነበሩምን? ኮራችሁም፡፡ ከሓዲዎች ሕዝቦችም ነበራችሁ፡፡»

Verse 32

وَإِذَا قِيلَ إِنَّ وَعْدَ ٱللَّهِ حَقٌّ وَٱلسَّاعَةُ لَا رَيْبَ فِيهَا قُلْتُم مَّا نَدْرِى مَا ٱلسَّاعَةُ إِن نَّظُنُّ إِلَّا ظَنًّا وَمَا نَحْنُ بِمُسْتَيْقِنِينَ

Transliteration wa-idhā qīla inna waʿda l-lahi ḥaqqun wal-sāʿatu lā rayba fīhā qul'tum mā nadrī mā l-sāʿatu in naẓunnu illā ẓannan wamā naḥnu bimus'tayqinīna

Amharic «የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፡፡ ሰዓቲቱም በእርሷ (መምጣት) ጥርጥር የለም፡፡» በተባለ ጊዜም «ሰዓቲቱ ምን እንደ ኾነች አናውቅም፡፡ መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጅ ሌላ አይደለንም፡፡ እኛም አረጋጋጮች አይደለንም» አላችሁ፡፡

Verse 33

وَبَدَا لَهُمْ سَيِّـَٔاتُ مَا عَمِلُوا۟ وَحَاقَ بِهِم مَّا كَانُوا۟ بِهِۦ يَسْتَهْزِءُونَ

Transliteration wabadā lahum sayyiātu mā ʿamilū waḥāqa bihim mā kānū bihi yastahziūna

Amharic የሠሩዋቸውም ኀጢአቶች ለእነርሱ ይገለጹላቸዋል፡፡ ያም በእርሱ ይሳለቁበት የነበሩት ቅጣት በእነርሱ ላይ ይወርድባቸዋል፡፡

Verse 34

وَقِيلَ ٱلْيَوْمَ نَنسَىٰكُمْ كَمَا نَسِيتُمْ لِقَآءَ يَوْمِكُمْ هَـٰذَا وَمَأْوَىٰكُمُ ٱلنَّارُ وَمَا لَكُم مِّن نَّـٰصِرِينَ

Transliteration waqīla l-yawma nansākum kamā nasītum liqāa yawmikum hādhā wamawākumu l-nāru wamā lakum min nāṣirīna

Amharic «ይህንንም ቀናችሁን መገናኘትን እንደ ረሳችሁ ዛሬ እንረሳችኋለን፡፡ (እንተዋችኋለን)፡፡ መኖሪያችሁም እሳት ናት፡፡ ለእናንተም ከረዳቶች ምንም የላችሁም» ይባላል፡፡

Verse 35

ذَٰلِكُم بِأَنَّكُمُ ٱتَّخَذْتُمْ ءَايَـٰتِ ٱللَّهِ هُزُوًا وَغَرَّتْكُمُ ٱلْحَيَوٰةُ ٱلدُّنْيَا ۚ فَٱلْيَوْمَ لَا يُخْرَجُونَ مِنْهَا وَلَا هُمْ يُسْتَعْتَبُونَ

Transliteration dhālikum bi-annakumu ittakhadhtum āyāti l-lahi huzuwan wagharratkumu l-ḥayatu l-dun'yā fal-yawma lā yukh'rajūna min'hā walā hum yus'taʿtabūna

Amharic ይህ እናንተ የአላህን አንቀጾች መቀለጃ አድርጋችሁ በመያዛችሁና ቅርቢቱም ሕይወት ስለአታለለቻችሁ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ዛሬ ከእርሷ አይወጥጡም፤ እነርሱም በወቀሳ አይታለፉም፡፡

Verse 36

فَلِلَّهِ ٱلْحَمْدُ رَبِّ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَرَبِّ ٱلْأَرْضِ رَبِّ ٱلْعَـٰلَمِينَ

Transliteration falillahi l-ḥamdu rabbi l-samāwāti warabbi l-arḍi rabbi l-ʿālamīna

Amharic ምስጋናም ለአላህ ለሰማያት ጌታ ለምድርም ጌታ ለዓለማት ጌታ የተገባው ነው፡፡

Verse 37

وَلَهُ ٱلْكِبْرِيَآءُ فِى ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ ۖ وَهُوَ ٱلْعَزِيزُ ٱلْحَكِيمُ

Transliteration walahu l-kib'riyāu fī l-samāwāti wal-arḍi wahuwa l-ʿazīzu l-ḥakīmu

Amharic ኩራትም በሰማያትም በምድርም ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም አሸነፊው ጥበበኛው ነው፡፡

Read Surah Al-Jathiyah in another language

All languages

All 114 surahs in Amharic: the Qur’an in Amharic.

Learn it in MyDugsi

Amharic translation: Sadiq and Sani, from Quran.com. Transliteration: Quran.com. Recitation: Mishary Alafasy, from EveryAyah.com. MyDugsi is a learning aid, not a replacement for a qualified teacher.