MyDugsiStart learning

Surah Sad in Amharic: translation and audio

Surah 38 · ص · The Letter "Saad" · 88 verses

Surah Sad verse by verse: the Arabic with a recitation you can repeat, the transliteration, and the Amharic translation by Sadiq and Sani. For the meaning of every word, see Surah Sad word by word in English.

Verse 1

صٓ ۚ وَٱلْقُرْءَانِ ذِى ٱلذِّكْرِ

Transliteration sad wal-qur'āni dhī l-dhik'ri

Amharic ጸ. (ሷድ) የክብር ባለቤት በሆነው ቁርኣን እምላለሁ (ብዙ አማልክት አሉ እንደሚሉት አይደለም)፡፡

Verse 2

بَلِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ فِى عِزَّةٍ وَشِقَاقٍ

Transliteration bali alladhīna kafarū fī ʿizzatin washiqāqin

Amharic ይልቁንም እነዚያ የካዱት ሰዎች በትዕቢትና በክርክር ውስጥ ናቸው፡፡

Verse 3

كَمْ أَهْلَكْنَا مِن قَبْلِهِم مِّن قَرْنٍ فَنَادَوا۟ وَّلَاتَ حِينَ مَنَاصٍ

Transliteration kam ahlaknā min qablihim min qarnin fanādaw walāta ḥīna manāṣin

Amharic ከእነርሱ በፊት ከክፍለ ዘመናት ሕዝቦች ብዙን አጥፍተናል፡፡ (ጊዜው) የመሸሻና የማምለጫ ጊዜ ሳይሆንም (ለእርዳታ) ተጣሩ፡፡

Verse 4

وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ ٱلْكَـٰفِرُونَ هَـٰذَا سَـٰحِرٌ كَذَّابٌ

Transliteration waʿajibū an jāahum mundhirun min'hum waqāla l-kāfirūna hādhā sāḥirun kadhābun

Amharic ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም «ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው» አሉ፡፡

Verse 5

أَجَعَلَ ٱلْـَٔالِهَةَ إِلَـٰهًا وَٰحِدًا ۖ إِنَّ هَـٰذَا لَشَىْءٌ عُجَابٌ

Transliteration ajaʿala l-ālihata ilāhan wāḥidan inna hādhā lashayon ʿujābun

Amharic «አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው» (አሉ)፡፡

Verse 6

وَٱنطَلَقَ ٱلْمَلَأُ مِنْهُمْ أَنِ ٱمْشُوا۟ وَٱصْبِرُوا۟ عَلَىٰٓ ءَالِهَتِكُمْ ۖ إِنَّ هَـٰذَا لَشَىْءٌ يُرَادُ

Transliteration wa-inṭalaqa l-mala-u min'hum ani im'shū wa-iṣ'birū ʿalā ālihatikum inna hādhā lashayon yurādu

Amharic ከእነርሱም መኳንንቶቹ «ሂዱ፤ በአማልክቶቻችሁም (መግገዛት) ላይ ታገሱ፡፡ ይህ (ከእኛ) የሚፈለግ ነገር ነውና» እያሉ አዘገሙ፡፡

Verse 7

مَا سَمِعْنَا بِهَـٰذَا فِى ٱلْمِلَّةِ ٱلْـَٔاخِرَةِ إِنْ هَـٰذَآ إِلَّا ٱخْتِلَـٰقٌ

Transliteration mā samiʿ'nā bihādhā fī l-milati l-ākhirati in hādhā illā ikh'tilāqun

Amharic «ይህንንም በኋለኛይቱ ሃይማኖት አልሰማንም፡፡ ይህ ውሸትን መፍጠር እንጅ ሌላ አይደለም» (እያሉም)፡፡

Verse 8

أَءُنزِلَ عَلَيْهِ ٱلذِّكْرُ مِنۢ بَيْنِنَا ۚ بَلْ هُمْ فِى شَكٍّ مِّن ذِكْرِى ۖ بَل لَّمَّا يَذُوقُوا۟ عَذَابِ

Transliteration a-unzila ʿalayhi l-dhik'ru min bayninā bal hum fī shakkin min dhik'rī bal lammā yadhūqū ʿadhābi

Amharic «ከመካከላችን በእርሱ ላይ ቁርኣን ተወረደን?» (አሉ)፡፡ በእውነት እነርሱ ከግሳጼዬ (ከቁርኣን) በመጠራጠር ውስጥ ናቸው፡፡ በእርግጥም ቅጣቴን ገና አልቀመሱም፡፡

Verse 9

أَمْ عِندَهُمْ خَزَآئِنُ رَحْمَةِ رَبِّكَ ٱلْعَزِيزِ ٱلْوَهَّابِ

Transliteration am ʿindahum khazāinu raḥmati rabbika l-ʿazīzi l-wahābi

Amharic ይልቁንም የአሸናፊውና የለጋሱ ጌታህ የችሮታው መጋዘኖች እነርሱ ዘንድ ናቸውን?

Verse 10

أَمْ لَهُم مُّلْكُ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ۖ فَلْيَرْتَقُوا۟ فِى ٱلْأَسْبَـٰبِ

Transliteration am lahum mul'ku l-samāwāti wal-arḍi wamā baynahumā falyartaqū fī l-asbābi

Amharic ወይስ የሰማያትና የምድር የመካከላቸውም ንግሥና የእነርሱ ነውን? (ነው ቢሉ) በመሰላሎችም ይውጡ፡፡

Verse 11

جُندٌ مَّا هُنَالِكَ مَهْزُومٌ مِّنَ ٱلْأَحْزَابِ

Transliteration jundun mā hunālika mahzūmun mina l-aḥzābi

Amharic እዚያ ዘንድ ከአሕዛብ የሆኑ ተሸናፊ ሰራዊት ናቸው፡፡

Verse 12

كَذَّبَتْ قَبْلَهُمْ قَوْمُ نُوحٍ وَعَادٌ وَفِرْعَوْنُ ذُو ٱلْأَوْتَادِ

Transliteration kadhabat qablahum qawmu nūḥin waʿādun wafir'ʿawnu dhū l-awtādi

Amharic ከእነርሱ በፊት የኑሕ ሕዝቦች፣ ዓድም፣ የችካሎች ባለቤት የሆነው ፈርዖንም አስተባበሉ፡፡

Verse 13

وَثَمُودُ وَقَوْمُ لُوطٍ وَأَصْحَـٰبُ لْـَٔيْكَةِ ۚ أُو۟لَـٰٓئِكَ ٱلْأَحْزَابُ

Transliteration wathamūdu waqawmu lūṭin wa-aṣḥābu al'aykati ulāika l-aḥzābu

Amharic ሰሙድም፣ የሉጥ ሰዎችም፣ የአይከት ሰዎችም (አስተባበሉ)፡፡ እነዚህ አሕዛቦቹ ናቸው፡፡

Verse 14

إِن كُلٌّ إِلَّا كَذَّبَ ٱلرُّسُلَ فَحَقَّ عِقَابِ

Transliteration in kullun illā kadhaba l-rusula faḥaqqa ʿiqābi

Amharic ሁሉም መልክተኞቹን ያስዋሹ እንጅ ሌላ አይደሉም፡፡ ቅጣቴም ተረጋገጠባቸው፡፡

Verse 15

وَمَا يَنظُرُ هَـٰٓؤُلَآءِ إِلَّا صَيْحَةً وَٰحِدَةً مَّا لَهَا مِن فَوَاقٍ

Transliteration wamā yanẓuru hāulāi illā ṣayḥatan wāḥidatan mā lahā min fawāqin

Amharic እነዚህም ለእርሷ መመለስ የሌላትን አንዲትን ጩኸት እንጅ ሌላን አይጠባበቁም፡፡

Verse 16

وَقَالُوا۟ رَبَّنَا عَجِّل لَّنَا قِطَّنَا قَبْلَ يَوْمِ ٱلْحِسَابِ

Transliteration waqālū rabbanā ʿajjil lanā qiṭṭanā qabla yawmi l-ḥisābi

Amharic «ጌታችን ሆይ! ከምርመራው ቀን በፊት መጽሐፋችንን አስቸኩልልን» አሉም፡፡

Verse 17

ٱصْبِرْ عَلَىٰ مَا يَقُولُونَ وَٱذْكُرْ عَبْدَنَا دَاوُۥدَ ذَا ٱلْأَيْدِ ۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ

Transliteration iṣ'bir ʿalā mā yaqūlūna wa-udh'kur ʿabdanā dāwūda dhā l-aydi innahu awwābun

Amharic በሚሉት ነገር ላይ ታገስ፡፡ የኀይል ባለቤት የሆነውን ባሪያችንንም ዳውድን አውሳላቸው፡፡ እርሱ በጣም መላሳ ነውና፡፡

Verse 18

إِنَّا سَخَّرْنَا ٱلْجِبَالَ مَعَهُۥ يُسَبِّحْنَ بِٱلْعَشِىِّ وَٱلْإِشْرَاقِ

Transliteration innā sakharnā l-jibāla maʿahu yusabbiḥ'na bil-ʿashiyi wal-ish'rāqi

Amharic እኛ ተራራዎችን ከቀትር በኋላና በረፋድም ከእርሱ ጋር የሚያወድሱ ሲሆኑ ገራንለት፡፡

Verse 19

وَٱلطَّيْرَ مَحْشُورَةً ۖ كُلٌّ لَّهُۥٓ أَوَّابٌ

Transliteration wal-ṭayra maḥshūratan kullun lahu awwābun

Amharic በራሪዎችንም (አእዋፍን) የሚሰበሰቡ ሆነው (ገራንለት)፡፡ ሁሉም ለእርሱ (ማወደስ) የሚመላለስ ነው፡፡

Verse 20

وَشَدَدْنَا مُلْكَهُۥ وَءَاتَيْنَـٰهُ ٱلْحِكْمَةَ وَفَصْلَ ٱلْخِطَابِ

Transliteration washadadnā mul'kahu waātaynāhu l-ḥik'mata wafaṣla l-khiṭābi

Amharic መንግሥቱንም አበረታንለት፡፡ ጥበብንም ንግግርን መለየትንም ሰጠነው፡፡

Verse 21

۞ وَهَلْ أَتَىٰكَ نَبَؤُا۟ ٱلْخَصْمِ إِذْ تَسَوَّرُوا۟ ٱلْمِحْرَابَ

Transliteration wahal atāka naba-u l-khaṣmi idh tasawwarū l-miḥ'rāba

Amharic የተከራካሪዎቹም ወሬ መጥቶልሃልን? ምኩራቡን በተንጠላጠሉ ጊዜ፡፡

Verse 22

إِذْ دَخَلُوا۟ عَلَىٰ دَاوُۥدَ فَفَزِعَ مِنْهُمْ ۖ قَالُوا۟ لَا تَخَفْ ۖ خَصْمَانِ بَغَىٰ بَعْضُنَا عَلَىٰ بَعْضٍ فَٱحْكُم بَيْنَنَا بِٱلْحَقِّ وَلَا تُشْطِطْ وَٱهْدِنَآ إِلَىٰ سَوَآءِ ٱلصِّرَٰطِ

Transliteration idh dakhalū ʿalā dāwūda fafaziʿa min'hum qālū lā takhaf khaṣmāni baghā baʿḍunā ʿalā baʿḍin fa-uḥ'kum baynanā bil-ḥaqi walā tush'ṭiṭ wa-ih'dinā ilā sawāi l-ṣirāṭi

Amharic በዳውድ ላይም በገቡ ጊዜ ከእነርሱም በደነገጠ ጊዜ «አትፍራ፤ (እኛ) ከፊላችን በከፊሉ ላይ ወሰን ያለፈ ሁለት ተከራካሪዎች ነን፡፡ በመካከላችንም በእውነት ፍረድ፡፡ አታዳላም፡፡ ወደ

Verse 23

إِنَّ هَـٰذَآ أَخِى لَهُۥ تِسْعٌ وَتِسْعُونَ نَعْجَةً وَلِىَ نَعْجَةٌ وَٰحِدَةٌ فَقَالَ أَكْفِلْنِيهَا وَعَزَّنِى فِى ٱلْخِطَابِ

Transliteration inna hādhā akhī lahu tis'ʿun watis'ʿūna naʿjatan waliya naʿjatun wāḥidatun faqāla akfil'nīhā waʿazzanī fī l-khiṭābi

Amharic «ይህ ወንድሜ ነው፤ ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴቶች በጎች አሉት፡፡ ለኔም አንዲት ሴት በግ

Verse 24

قَالَ لَقَدْ ظَلَمَكَ بِسُؤَالِ نَعْجَتِكَ إِلَىٰ نِعَاجِهِۦ ۖ وَإِنَّ كَثِيرًا مِّنَ ٱلْخُلَطَآءِ لَيَبْغِى بَعْضُهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَقَلِيلٌ مَّا هُمْ ۗ وَظَنَّ دَاوُۥدُ أَنَّمَا فَتَنَّـٰهُ فَٱسْتَغْفَرَ رَبَّهُۥ وَخَرَّ رَاكِعًا وَأَنَابَ ۩

Transliteration qāla laqad ẓalamaka bisuāli naʿjatika ilā niʿājihi wa-inna kathīran mina l-khulaṭāi layabghī baʿḍuhum ʿalā baʿḍin illā alladhīna āmanū waʿamilū l-ṣāliḥāti waqalīlun mā hum waẓanna dāwūdu annamā fatannāhu fa-is'taghfara rabbahu wakharra rākiʿan wa-anāba

Amharic «ሴት በግህን ወደ በጎቹ (ለመቀላቀል) በመጠየቁ በእርግጥ በደለህ፡፡ ከተጋሪዎችም ብዙዎቹ ከፊላቸው በከፊሉ ላይ ወሰን ያልፋሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ብቻ ሲቀሩ፡፡ እነርሱም በጣም ጥቂቶች ናቸው» አለ፡፡ ዳውድም የፈተንነው መኾኑን ዐወቀ፡፡ ጌታውንም ምሕረትን ለመነ፡፡ ሰጋጅ ኾኖ ወደቀም፡፡ በመጸጸት ተመለሰም፡፡

Verse 25

فَغَفَرْنَا لَهُۥ ذَٰلِكَ ۖ وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلْفَىٰ وَحُسْنَ مَـَٔابٍ

Transliteration faghafarnā lahu dhālika wa-inna lahu ʿindanā lazul'fā waḥus'na maābin

Amharic ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ (ክብር) መልካም መመለሻም አለው፡፡

Verse 26

يَـٰدَاوُۥدُ إِنَّا جَعَلْنَـٰكَ خَلِيفَةً فِى ٱلْأَرْضِ فَٱحْكُم بَيْنَ ٱلنَّاسِ بِٱلْحَقِّ وَلَا تَتَّبِعِ ٱلْهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَضِلُّونَ عَن سَبِيلِ ٱللَّهِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌۢ بِمَا نَسُوا۟ يَوْمَ ٱلْحِسَابِ

Transliteration yādāwūdu innā jaʿalnāka khalīfatan fī l-arḍi fa-uḥ'kum bayna l-nāsi bil-ḥaqi walā tattabiʿi l-hawā fayuḍillaka ʿan sabīli l-lahi inna alladhīna yaḍillūna ʿan sabīli l-lahi lahum ʿadhābun shadīdun bimā nasū yawma l-ḥisābi

Amharic ዳውድ ሆይ! እኛ በምድር ላይ ምትክ አድርገንሃልና በሰዎች መካከል በእውነት ፍረድ፡፡ ዝንባሌሀንም አትከተል፤ከአላህ መንገድ ያሳሳትሃልና፡፡ እነዚያ ከአላህ መንገድ የሚሳሳቱ የምርመራውን ቀን በመርሳታቸው ለእነርሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፡፡

Verse 27

وَمَا خَلَقْنَا ٱلسَّمَآءَ وَٱلْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَـٰطِلًا ۚ ذَٰلِكَ ظَنُّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ۚ فَوَيْلٌ لِّلَّذِينَ كَفَرُوا۟ مِنَ ٱلنَّارِ

Transliteration wamā khalaqnā l-samāa wal-arḍa wamā baynahumā bāṭilan dhālika ẓannu alladhīna kafarū fawaylun lilladhīna kafarū mina l-nāri

Amharic ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!

Verse 28

أَمْ نَجْعَلُ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ كَٱلْمُفْسِدِينَ فِى ٱلْأَرْضِ أَمْ نَجْعَلُ ٱلْمُتَّقِينَ كَٱلْفُجَّارِ

Transliteration am najʿalu alladhīna āmanū waʿamilū l-ṣāliḥāti kal-muf'sidīna fī l-arḍi am najʿalu l-mutaqīna kal-fujāri

Amharic በእውነቱ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን?

Verse 29

كِتَـٰبٌ أَنزَلْنَـٰهُ إِلَيْكَ مُبَـٰرَكٌ لِّيَدَّبَّرُوٓا۟ ءَايَـٰتِهِۦ وَلِيَتَذَكَّرَ أُو۟لُوا۟ ٱلْأَلْبَـٰبِ

Transliteration kitābun anzalnāhu ilayka mubārakun liyaddabbarū āyātihi waliyatadhakkara ulū l-albābi

Amharic (ይህ) ወዳንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው)፡፡

Verse 30

وَوَهَبْنَا لِدَاوُۥدَ سُلَيْمَـٰنَ ۚ نِعْمَ ٱلْعَبْدُ ۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ

Transliteration wawahabnā lidāwūda sulaymāna niʿ'ma l-ʿabdu innahu awwābun

Amharic ለዳውድም ሱለይማንን ሰጠነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ! (ሱለይማን)፣ እርሱ መላሳ ነው፡፡

Verse 31

إِذْ عُرِضَ عَلَيْهِ بِٱلْعَشِىِّ ٱلصَّـٰفِنَـٰتُ ٱلْجِيَادُ

Transliteration idh ʿuriḍa ʿalayhi bil-ʿashiyi l-ṣāfinātu l-jiyādu

Amharic በእርሱ ላይ ከቀትር በኋላ በሦስት እግሮችና በአራተኛዋ ኮቴ ጫፍ የሚቆሙ ጮሌዎች ፈረሶች በተቀረቡለት ጊዜ (አስታውስ)፡፡

Verse 32

فَقَالَ إِنِّىٓ أَحْبَبْتُ حُبَّ ٱلْخَيْرِ عَن ذِكْرِ رَبِّى حَتَّىٰ تَوَارَتْ بِٱلْحِجَابِ

Transliteration faqāla innī aḥbabtu ḥubba l-khayri ʿan dhik'ri rabbī ḥattā tawārat bil-ḥijābi

Amharic አለም «እኔ (ፀሐይ) በግርዶ እስከ ተደበቀች ድረስ ከጌታዬ ማስታወስ ፋንታ ፈረስን መውደድን መረጥኩ፡፡»

Verse 33

رُدُّوهَا عَلَىَّ ۖ فَطَفِقَ مَسْحًۢا بِٱلسُّوقِ وَٱلْأَعْنَاقِ

Transliteration ruddūhā ʿalayya faṭafiqa masḥan bil-sūqi wal-aʿnāqi

Amharic «በእኔ ላይ መልሷት» (አለ) አጋዶችዋንና አንገቶችዋንም ማበስ ያዘ፡፡

Verse 34

وَلَقَدْ فَتَنَّا سُلَيْمَـٰنَ وَأَلْقَيْنَا عَلَىٰ كُرْسِيِّهِۦ جَسَدًا ثُمَّ أَنَابَ

Transliteration walaqad fatannā sulaymāna wa-alqaynā ʿalā kur'siyyihi jasadan thumma anāba

Amharic ሱለይማንንም በእርግጥ ፈተንነው፡፡ በመንበሩም ላይ አካልን ጣልን፡፡ ከዚያም በመጸጸት ተመለሰ፡፡

Verse 35

قَالَ رَبِّ ٱغْفِرْ لِى وَهَبْ لِى مُلْكًا لَّا يَنۢبَغِى لِأَحَدٍ مِّنۢ بَعْدِىٓ ۖ إِنَّكَ أَنتَ ٱلْوَهَّابُ

Transliteration qāla rabbi igh'fir lī wahab lī mul'kan lā yanbaghī li-aḥadin min baʿdī innaka anta l-wahābu

Amharic «ጌታዬ ሆይ! ለእኔ ማር፡፡ ከእኔ በኋላ ለአንድም የማይገባንም ንግሥና ስጠኝ፡፡ አንተ ለጋሱ አንተ ብቻ ነህና» አለ፡፡

Verse 36

فَسَخَّرْنَا لَهُ ٱلرِّيحَ تَجْرِى بِأَمْرِهِۦ رُخَآءً حَيْثُ أَصَابَ

Transliteration fasakharnā lahu l-rīḥa tajrī bi-amrihi rukhāan ḥaythu aṣāba

Amharic ነፋስንም በትእዛዙ ወደፈለገበት ስፍራ ልዝብ ኾና የምትፈስ ስትኾን ገራንለት፡፡

Verse 37

وَٱلشَّيَـٰطِينَ كُلَّ بَنَّآءٍ وَغَوَّاصٍ

Transliteration wal-shayāṭīna kulla bannāin waghawwāṣin

Amharic ሰይጣናትንም ገንቢዎችንና ሰጣሚዎችን ሁሉ (ገራንለት)፡፡

Verse 38

وَءَاخَرِينَ مُقَرَّنِينَ فِى ٱلْأَصْفَادِ

Transliteration waākharīna muqarranīna fī l-aṣfādi

Amharic ሌሎችንም በፍንጆች ተቆራኞችን (ገራንለት)፡፡

Verse 39

هَـٰذَا عَطَآؤُنَا فَٱمْنُنْ أَوْ أَمْسِكْ بِغَيْرِ حِسَابٍ

Transliteration hādhā ʿaṭāunā fa-um'nun aw amsik bighayri ḥisābin

Amharic «ይህ ስጦታችን ነው፡፡ ያለግምት ለግስ፤ ወይም ጨብጥ» (አልነው)፡፡

Verse 40

وَإِنَّ لَهُۥ عِندَنَا لَزُلْفَىٰ وَحُسْنَ مَـَٔابٍ

Transliteration wa-inna lahu ʿindanā lazul'fā waḥus'na maābin

Amharic ለእርሱም እኛ ዘንድ መቅረብ፤ መልካም መመለሻም በእርግጥ አልለው፡፡

Verse 41

وَٱذْكُرْ عَبْدَنَآ أَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُۥٓ أَنِّى مَسَّنِىَ ٱلشَّيْطَـٰنُ بِنُصْبٍ وَعَذَابٍ

Transliteration wa-udh'kur ʿabdanā ayyūba idh nādā rabbahu annī massaniya l-shayṭānu binuṣ'bin waʿadhābin

Amharic ባሪያችንን አዩብንም አውሳላቸው፡፡ «እኔ ሰይጣን በጉዳትና በስቃይ ነካኝ» ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ፡፡

Verse 42

ٱرْكُضْ بِرِجْلِكَ ۖ هَـٰذَا مُغْتَسَلٌۢ بَارِدٌ وَشَرَابٌ

Transliteration ur'kuḍ birij'lika hādhā mugh'tasalun bāridun washarābun

Amharic «በእግርህ (ምድርን) ምታ፡፡ ይህ ቀዝቃዛ መታጠቢያ መጠጥም ነው» (ተባለ)፡፡

Verse 43

وَوَهَبْنَا لَهُۥٓ أَهْلَهُۥ وَمِثْلَهُم مَّعَهُمْ رَحْمَةً مِّنَّا وَذِكْرَىٰ لِأُو۟لِى ٱلْأَلْبَـٰبِ

Transliteration wawahabnā lahu ahlahu wamith'lahum maʿahum raḥmatan minnā wadhik'rā li-ulī l-albābi

Amharic ለእርሱም ከእኛ ዘንድ ለችሮታ ባለአእምሮዎችንም ለመገሠጽ ቤተሰቦቹን ከእነርሱም ጋር መሰላቸውን ሰጠነው፡፡

Verse 44

وَخُذْ بِيَدِكَ ضِغْثًا فَٱضْرِب بِّهِۦ وَلَا تَحْنَثْ ۗ إِنَّا وَجَدْنَـٰهُ صَابِرًا ۚ نِّعْمَ ٱلْعَبْدُ ۖ إِنَّهُۥٓ أَوَّابٌ

Transliteration wakhudh biyadika ḍigh'than fa-iḍ'rib bihi walā taḥnath innā wajadnāhu ṣābiran niʿ'ma l-ʿabdu innahu awwābun

Amharic «በእጅህም ጭብጥ አርጩሜን ያዝ፡፡ በእርሱም (ሚስትህን) ምታ፡፡ ማላህንም አታፍርስ» (አልነው)፡፡ እኛ ታጋሸ ኾኖ አገኘነው፡፡ ምን ያምር ባሪያ እርሱ በጣም መላሳ ነው፡፡

Verse 45

وَٱذْكُرْ عِبَـٰدَنَآ إِبْرَٰهِيمَ وَإِسْحَـٰقَ وَيَعْقُوبَ أُو۟لِى ٱلْأَيْدِى وَٱلْأَبْصَـٰرِ

Transliteration wa-udh'kur ʿibādanā ib'rāhīma wa-is'ḥāqa wayaʿqūba ulī l-aydī wal-abṣāri

Amharic ባሮቻችንንም ኢብራሂምን፣ ኢስሐቅንና ያዕቆበንም፣ የኅይልና የማስተዋል ባለቤቶች የኾኑን አውሳላቸው፡፡

Verse 46

إِنَّآ أَخْلَصْنَـٰهُم بِخَالِصَةٍ ذِكْرَى ٱلدَّارِ

Transliteration innā akhlaṣnāhum bikhāliṣatin dhik'rā l-dāri

Amharic እኛ ጥሩ በኾነች ጠባይ መረጥናቸው፡፡ (እርሷም) የመጨረሻይቱን አገር ማስታወስ ናት፡፡

Verse 47

وَإِنَّهُمْ عِندَنَا لَمِنَ ٱلْمُصْطَفَيْنَ ٱلْأَخْيَارِ

Transliteration wa-innahum ʿindanā lamina l-muṣ'ṭafayna l-akhyāri

Amharic እነርሱም እኛ ዘንድ ከመልካሞቹ ምርጦች ናቸው፡፡

Verse 48

وَٱذْكُرْ إِسْمَـٰعِيلَ وَٱلْيَسَعَ وَذَا ٱلْكِفْلِ ۖ وَكُلٌّ مِّنَ ٱلْأَخْيَارِ

Transliteration wa-udh'kur is'māʿīla wal-yasaʿa wadhā l-kif'li wakullun mina l-akhyāri

Amharic ኢስማዒልንም፣ አልየሰዕንም፣ ዙልኪፍልንም አውሳ፡፡ ሁሉም ከበላጮቹ ናቸው፡፡

Verse 49

هَـٰذَا ذِكْرٌ ۚ وَإِنَّ لِلْمُتَّقِينَ لَحُسْنَ مَـَٔابٍ

Transliteration hādhā dhik'run wa-inna lil'muttaqīna laḥus'na maābin

Amharic ይህ መልካም ዝና ነው፡፡ ለአላህ ፈሪዎችም በእርግጥ ውብ የኾነ መመለሻ አላቸው፡፡

Verse 50

جَنَّـٰتِ عَدْنٍ مُّفَتَّحَةً لَّهُمُ ٱلْأَبْوَٰبُ

Transliteration jannāti ʿadnin mufattaḥatan lahumu l-abwābu

Amharic በሮቻቸው ለእነርሱ የተከፈቱ ሲኾኑ የመኖሪያ ገነቶች አሏቸው፡፡

Verse 51

مُتَّكِـِٔينَ فِيهَا يَدْعُونَ فِيهَا بِفَـٰكِهَةٍ كَثِيرَةٍ وَشَرَابٍ

Transliteration muttakiīna fīhā yadʿūna fīhā bifākihatin kathīratin washarābin

Amharic በእርሷ ውስጥ የተደገፉ ኾነው በውስጧ በብዙ እሸቶችና በመጠጥም ያዝዛሉ፡፡

Verse 52

۞ وَعِندَهُمْ قَـٰصِرَٰتُ ٱلطَّرْفِ أَتْرَابٌ

Transliteration waʿindahum qāṣirātu l-ṭarfi atrābun

Amharic እነርሱ ዘንድም ዓይኖቻቸውን (በባሎቻቸው ላይ) አሳጣሪዎች እኩያዎች (ሴቶች) አልሉ፡፡

Verse 53

هَـٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِيَوْمِ ٱلْحِسَابِ

Transliteration hādhā mā tūʿadūna liyawmi l-ḥisābi

Amharic ይህ ለምርመራው ቀን የምትቀጠሩት ተሰፋ ነው፡፡

Verse 54

إِنَّ هَـٰذَا لَرِزْقُنَا مَا لَهُۥ مِن نَّفَادٍ

Transliteration inna hādhā lariz'qunā mā lahu min nafādin

Amharic ይህ ሲሳያችን ነው፡፡ ለእርሱ ምንም ማለቅ የለውም፡፡

Verse 55

هَـٰذَا ۚ وَإِنَّ لِلطَّـٰغِينَ لَشَرَّ مَـَٔابٍ

Transliteration hādhā wa-inna lilṭṭāghīna lasharra maābin

Amharic ይህ (ለአማኞች ነው)፡፡ ለጠማሞችም በጣም የከፋ መመለሻ አላቸው፡፡

Verse 56

جَهَنَّمَ يَصْلَوْنَهَا فَبِئْسَ ٱلْمِهَادُ

Transliteration jahannama yaṣlawnahā fabi'sa l-mihādu

Amharic የሚገቧት ስትኾን ገሀነም (አለቻቸው)፡፡ ምንጣፊቱም ምንኛ ከፋች፡፡

Verse 57

هَـٰذَا فَلْيَذُوقُوهُ حَمِيمٌ وَغَسَّاقٌ

Transliteration hādhā falyadhūqūhu ḥamīmun waghassāqun

Amharic ይህ (ለከሓዲዎች ነው)፡፡ ይቅመሱትም፡፡ የፈላ ውሃና እዥ ነው፡፡

Verse 58

وَءَاخَرُ مِن شَكْلِهِۦٓ أَزْوَٰجٌ

Transliteration waākharu min shaklihi azwājun

Amharic ሌላም ከመሰሉ ዓይነቶች አልሉ፡፡

Verse 59

هَـٰذَا فَوْجٌ مُّقْتَحِمٌ مَّعَكُمْ ۖ لَا مَرْحَبًۢا بِهِمْ ۚ إِنَّهُمْ صَالُوا۟ ٱلنَّارِ

Transliteration hādhā fawjun muq'taḥimun maʿakum lā marḥaban bihim innahum ṣālū l-nāri

Amharic ይህ ከእናንተ ጋር በመጋፈጥ ገቢ ጭፍራ ነው፤ (ይባላሉ)፡፡ ለእነርሱ አይስፋቸው፡፡ እነርሱ እሳትን ገቢዎች ናቸውና (ይላሉ)፡፡

Verse 60

قَالُوا۟ بَلْ أَنتُمْ لَا مَرْحَبًۢا بِكُمْ ۖ أَنتُمْ قَدَّمْتُمُوهُ لَنَا ۖ فَبِئْسَ ٱلْقَرَارُ

Transliteration qālū bal antum lā marḥaban bikum antum qaddamtumūhu lanā fabi'sa l-qarāru

Amharic (ተከታዮቹ) ይላሉ «ይልቁን እናንተ አይስፋችሁ፡፡ እናንተ (ክህደቱን) ለእኛ አቀረባችሁት፡፡ መርጊያይቱም (ገሀነም) ከፋች፡፡»

Verse 61

قَالُوا۟ رَبَّنَا مَن قَدَّمَ لَنَا هَـٰذَا فَزِدْهُ عَذَابًا ضِعْفًا فِى ٱلنَّارِ

Transliteration qālū rabbanā man qaddama lanā hādhā fazid'hu ʿadhāban ḍiʿ'fan fī l-nāri

Amharic «ጌታችን ሆይ! ይህንን ያቀረበልንን ሰው በእሳት ውስጥ እጥፍን ቅጣት ጨምርለት» ይላሉ፡፡

Verse 62

وَقَالُوا۟ مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالًا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ ٱلْأَشْرَارِ

Transliteration waqālū mā lanā lā narā rijālan kunnā naʿudduhum mina l-ashrāri

Amharic ይላሉም «ለእኛ ምን አለን? ከመጥፎዎች እንቆጥራቸው የነበሩትን ሰዎች (እዚህ) አናይምሳ፡፡»

Verse 63

أَتَّخَذْنَـٰهُمْ سِخْرِيًّا أَمْ زَاغَتْ عَنْهُمُ ٱلْأَبْصَـٰرُ

Transliteration attakhadhnāhum sikh'riyyan am zāghat ʿanhumu l-abṣāru

Amharic «መቀለጃ አድርገን ያዝናቸውን? ወይስ ዓይኖቻችን ከእነሱ ዋለሉ?»

Verse 64

إِنَّ ذَٰلِكَ لَحَقٌّ تَخَاصُمُ أَهْلِ ٱلنَّارِ

Transliteration inna dhālika laḥaqqun takhāṣumu ahli l-nāri

Amharic ይህ በእርግጥ እምነት ነው፡፡ (እርሱም) የእሳት ሰዎች (የእርስ በእርስ) መካሰስ ነው፡፡

Verse 65

قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ مُنذِرٌ ۖ وَمَا مِنْ إِلَـٰهٍ إِلَّا ٱللَّهُ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّارُ

Transliteration qul innamā anā mundhirun wamā min ilāhin illā l-lahu l-wāḥidu l-qahāru

Amharic «እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ፡፡ ኀያል አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም» በላቸው፡፡

Verse 66

رَبُّ ٱلسَّمَـٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَمَا بَيْنَهُمَا ٱلْعَزِيزُ ٱلْغَفَّـٰرُ

Transliteration rabbu l-samāwāti wal-arḍi wamā baynahumā l-ʿazīzu l-ghafāru

Amharic «የሰማያትና የምድር በመካከላቸውም ያለው ሁሉ ጌታ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡»

Verse 67

قُلْ هُوَ نَبَؤٌا۟ عَظِيمٌ

Transliteration qul huwa naba-on ʿaẓīmun

Amharic በላቸው «እርሱ (ቁርኣን) ታላቅ ዜና ነው፡፡

Verse 68

أَنتُمْ عَنْهُ مُعْرِضُونَ

Transliteration antum ʿanhu muʿ'riḍūna

Amharic «እናንተ ከእርሱ ዘንጊዎች ናችሁ፡፡

Verse 69

مَا كَانَ لِىَ مِنْ عِلْمٍۭ بِٱلْمَلَإِ ٱلْأَعْلَىٰٓ إِذْ يَخْتَصِمُونَ

Transliteration mā kāna liya min ʿil'min bil-mala-i l-aʿlā idh yakhtaṣimūna

Amharic (በአደም ነገር) «በሚከራከሩ ጊዜ በላይኛው ሰራዊት ለእኔ ምንም ዕውቀት አልነበረኝም፡፡

Verse 70

إِن يُوحَىٰٓ إِلَىَّ إِلَّآ أَنَّمَآ أَنَا۠ نَذِيرٌ مُّبِينٌ

Transliteration in yūḥā ilayya illā annamā anā nadhīrun mubīnun

Amharic «ወደእኔም አስፈራሪ ገላጭ መኾኔ እንጂ ሌላ አይወረድልኝም» (በል)፡፡

Verse 71

إِذْ قَالَ رَبُّكَ لِلْمَلَـٰٓئِكَةِ إِنِّى خَـٰلِقٌۢ بَشَرًا مِّن طِينٍ

Transliteration idh qāla rabbuka lil'malāikati innī khāliqun basharan min ṭīnin

Amharic ጌታህ «ለመላእክት እኔ ሰውን ከጭቃ ፈጣሪ ነኝ ባለ ጊዜ» (አስታውስ)፡፡

Verse 72

فَإِذَا سَوَّيْتُهُۥ وَنَفَخْتُ فِيهِ مِن رُّوحِى فَقَعُوا۟ لَهُۥ سَـٰجِدِينَ

Transliteration fa-idhā sawwaytuhu wanafakhtu fīhi min rūḥī faqaʿū lahu sājidīna

Amharic «ፍጥረቱንም ባስተካከልኩና ከመንፈሴ በነፋሁበት ጊዜ ለእርሱ ሰጋጆች ኾናችሁ ውደቁ» (አልኩ)፡፡

Verse 73

فَسَجَدَ ٱلْمَلَـٰٓئِكَةُ كُلُّهُمْ أَجْمَعُونَ

Transliteration fasajada l-malāikatu kulluhum ajmaʿūna

Amharic መላእክትም መላውም ባንድነት ሰገዱ፡፡

Verse 74

إِلَّآ إِبْلِيسَ ٱسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ ٱلْكَـٰفِرِينَ

Transliteration illā ib'līsa is'takbara wakāna mina l-kāfirīna

Amharic ኢብሊስ ብቻ ሲቀር፡፡ ኮራ፤ ከከሓዲዎቹም ነበር፡፡

Verse 75

قَالَ يَـٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ

Transliteration qāla yāib'līsu mā manaʿaka an tasjuda limā khalaqtu biyadayya astakbarta am kunta mina l-ʿālīna

Amharic (አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡

Verse 76

قَالَ أَنَا۠ خَيْرٌ مِّنْهُ ۖ خَلَقْتَنِى مِن نَّارٍ وَخَلَقْتَهُۥ مِن طِينٍ

Transliteration qāla anā khayrun min'hu khalaqtanī min nārin wakhalaqtahu min ṭīnin

Amharic «እኔ ከእርሱ በላጭ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፤ ከጭቃም ፈጠርከው» አለ፡፡

Verse 77

قَالَ فَٱخْرُجْ مِنْهَا فَإِنَّكَ رَجِيمٌ

Transliteration qāla fa-ukh'ruj min'hā fa-innaka rajīmun

Amharic (አላህ) አለው «ከእርሷ ውጣ፤ አንተ የተባረርክ ነህና፡፡»

Verse 78

وَإِنَّ عَلَيْكَ لَعْنَتِىٓ إِلَىٰ يَوْمِ ٱلدِّينِ

Transliteration wa-inna ʿalayka laʿnatī ilā yawmi l-dīni

Amharic «እርግማኔም እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ባንተ ላይ ይኹን፡፡»

Verse 79

قَالَ رَبِّ فَأَنظِرْنِىٓ إِلَىٰ يَوْمِ يُبْعَثُونَ

Transliteration qāla rabbi fa-anẓir'nī ilā yawmi yub'ʿathūna

Amharic «ጌታዬ ሆይ! እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝም» አለ፡፡

Verse 80

قَالَ فَإِنَّكَ مِنَ ٱلْمُنظَرِينَ

Transliteration qāla fa-innaka mina l-munẓarīna

Amharic (አላህም) አለው «አንተ ከሚቆዩት ነህ፡፡»

Verse 81

إِلَىٰ يَوْمِ ٱلْوَقْتِ ٱلْمَعْلُومِ

Transliteration ilā yawmi l-waqti l-maʿlūmi

Amharic «እስከ ታወቀው ወቅት ቀን ድረስ፡፡»

Verse 82

قَالَ فَبِعِزَّتِكَ لَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ

Transliteration qāla fabiʿizzatika la-ugh'wiyannahum ajmaʿīna

Amharic (እርሱም) አለ «በአሸናፊነትህ ይኹንብኝ፤ በመላ አሳስታቸዋለሁ፡፡»

Verse 83

إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ ٱلْمُخْلَصِينَ

Transliteration illā ʿibādaka min'humu l-mukh'laṣīna

Amharic «ከእነርሱ ምርጥ የኾኑት ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡»

Verse 84

قَالَ فَٱلْحَقُّ وَٱلْحَقَّ أَقُولُ

Transliteration qāla fal-ḥaqu wal-ḥaqa aqūlu

Amharic (አላህ) አለው «እውነቱም (ከኔ ነው)፡፡ እውነትንም እላለሁ፡፡

Verse 85

لَأَمْلَأَنَّ جَهَنَّمَ مِنكَ وَمِمَّن تَبِعَكَ مِنْهُمْ أَجْمَعِينَ

Transliteration la-amla-anna jahannama minka wamimman tabiʿaka min'hum ajmaʿīna

Amharic ከአንተና ከእነርሱ ውስጥ ከተከተሉህ ባንድ ላይ ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ፡፡»

Verse 86

قُلْ مَآ أَسْـَٔلُكُمْ عَلَيْهِ مِنْ أَجْرٍ وَمَآ أَنَا۠ مِنَ ٱلْمُتَكَلِّفِينَ

Transliteration qul mā asalukum ʿalayhi min ajrin wamā anā mina l-mutakalifīna

Amharic በላቸው «በእርሱ ላይ ምንም ዋጋ አልጠይቃችሁም፤ እኔም ከተግደርዳሪዎቹ አይደለሁም፡፡

Verse 87

إِنْ هُوَ إِلَّا ذِكْرٌ لِّلْعَـٰلَمِينَ

Transliteration in huwa illā dhik'run lil'ʿālamīna

Amharic «እርሱ (ቁርኣን) ለዓለማት መገሠጫ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡

Verse 88

وَلَتَعْلَمُنَّ نَبَأَهُۥ بَعْدَ حِينٍۭ

Transliteration walataʿlamunna naba-ahu baʿda ḥīnin

Amharic «ትንቢቱንም (እውነት መኾኑን) ከጊዜ በኋላ በእርግጥ ታውቁታላችሁ፡፡»

Read Surah Sad in another language

All languages

All 114 surahs in Amharic: the Qur’an in Amharic.

Learn it in MyDugsi

Amharic translation: Sadiq and Sani, from Quran.com. Transliteration: Quran.com. Recitation: Mishary Alafasy, from EveryAyah.com. MyDugsi is a learning aid, not a replacement for a qualified teacher.